ግጥም ብቻ 📘
Открыть в Telegram
✔በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን። ✔ @getem @serenity13 ✔ @wegoch @Words19 ✔ @seiloch @shiyach_bicha ✔ @zefenbicha @leul_mekonnen1
Больше2025 год в цифрах

65 775
Подписчики
-324 часа
-397 дней
-30130 день
Архив постов
"በቅርቡ ከሚወጣው መፅሐፌ ቅምሻ" ❤🙏
ወገቤ ላይ ታላቅ ቁስል
የቁስል ሞት ታመኛለች፣
በስቅታ አፋፍ ሆኜ
ትንሽ መኖር ታምረኛለች
ትንሽ መኖር እያማረኝ
በሞት እቅፍ ሳለሁ እንኳ
የስኳር ማንኪያ ያህል
ኑሮ ራሱ ጣፋጭ ሹካ
ቁስል ሁሉ እከክ ወርሶኝ
በሞት መሃል ሳጣጥር፣
ትንሽ መኖር ታምረኛለች
ትንሽ ትንፋሽ ለመስከር፣
ጥይት ሁሉ ወርዶብኝ
ሰውነቴን ቢበሳሳም፣
ትንሽ መኖር ታሳሳለች
ከሞት ወሲብ ከመሳሳም፣
ትንሽ መኖር ስጭኝ ባክሽ
መኖር ባፌ ጉልበት ልሳም፣
ባክህ ቁስሌ መኖር ስጠኝ
ህመም እንኳ አይደንቀኝም፣
ትንሽ እንኳ መኖር ከቻልኩ
ጠባሳህም አይገለኝም፣
ትንሽ መኖር አማምሮኛል
ለነብሰጡር በሞት ደጅ ፣
ትንሽ ልኑር ባክህ አልሙት
ብወድቅ እንኳ በሰው እጅ፣
ትንሽ ብቻ መኖር መኖር
የአምሮቴን ትንሽ እድል፣
ትንሽ ህመም ለቀቅ አርገኝ
ኗሬለሁ ብዬ እንድል፣
'
'
@geez_mulat 🦘
ግዕዝ ሙላት
@getem
@getem
@getem
❤ 81🔥 6🎉 3
Показать все...
❤ 23👍 2😱 1
, ( ጨረቃ ነሽ ወይ ፀሀይ )
አንዲት ፍሬ ልጅ ሞትን ምታስንቂ
በውድቅት ለሊት
ደውል ሆነሽ መተሽ ሰውን ምታነቂ
ጨረቃ ነሽ ወይስ ፀሀይ ከሩቅ አብረቅራቂ
ብርድ እና ሙቀትን የሆንሽ አስታራቂ
በድቅድቅ ጨለማ ያለን በጠራሞት
ነጥቀሽ የምታዎጭ በዕድን ስጋን ከሞት
ጨረቃ ነሽ ወይስ ፀሀይ ንገሪኝ አንቺዬ
ለምጀው እንድኖር ሀሩርና ቁሩን እንደምንም ቺዬ
ጨረቃ ነሽ ወይስ ፀሀይ ንገሪኝ አንቺዬ
ከዬትኛው ስነ ፍጥረት ልመድብሽ
ከጨረቃ ከክዋከብት ከፀሀይ ጋር ልደርብሽ
ጨረቃ ነሽ ወይስ ፀሀይ ንገሪኝ አለሜ
አንቺን የሳልኩበት ሳይጠፋ ቀለሜ
እኔማ እኔማ
አንቺ ካልነገርሽኝ አልፅፍ ቃላትን
አልገነባም ጎጆን የሚፈርስ ቤትን
ስንቴ የሰራሁት ቤቴ ፈርሶ አልቆ
አለም አንቺን ሚሞቅ በእኔ ላይ ተሳልቆ
ጨረቃ ነሽ ወይስ ፀሀይ ???????
By Habtish
@getem
@getem
@getem
❤ 24👍 15
ቤት እማ ጨዋ ነሽ፣
እንኳን ሌላ ሌላ እኔንም አታይም፣
ግን እድሜ ለሱሱ፣
ወተሽ ወዳጅ ካየሽ አታልፊም አትተይም።
የሸመገለን ወንድ፣
በሰለቸ ዐይንሽ ዕያየሽ ወጠምሻ፣
የሱን መድሃኒት፣
አርገሽ ለቀን ያዝሽው የኔን ማስታገሻ።
By @eyadermoges
@getem
@getem
@paappii
❤ 33
Фото недоступноПоказать в Telegram
📍GHOST VOTE .
Ghost'ን vote እናድርግ
Ghosty’f sagalee kennaa
ጎስት'ነ ድምጺ ሃቡሉ
Ghost'ya keettidaa aayize
ጎስት vot አምሮዊ
Vote for Ghost
Vote por Ghost
投票给阿比伊,صوّتوا لأبيي
- ለጎስት ቮት ! 👇 🙏
https://www.tca2025.com/category/21
SHARE @getem
❤ 22👎 19😁 14
ከለታት ባንዱ ቀን
ህይወት ግቧን አውቀን
ኖረን ኖረን መጥቀን
በንባ ውዝፍ ስቀን
ከለታት ባንዱ ለት
ገፋንና ብረት
ቡጢ ተሰናዝረን በእጃችን ውጥረት
ግባችን ልንመታ ግብን አስተካክለን
አስቆጣሪ ጀግና በኛ ስም ወክለን
አክለን
በጥድፊያ
በልፊያ
ሰዓት አቀባብለን
ጊዜ ተቀባብለን
አንድ ሁኑ ስንባል ለየግል ተቆጥረን
ተዋደድን ብለን ካንገት ተወጣጥረን
ተመንጥረን
እንዳልሳቅን
አለቀስን
ፌዝ እንዳልያዝን በልባችን
ይበለን የታባታችን
ኖረን ኖረን መጥቀን
በንባ ውዝፍ ስቀን
አዙሮ
አዙሮ
ጊዜ ጣለን ከቀን።
ዮኒ
ኣታን @yonatoz
@getem
@getem
@getem
❤ 31🔥 9👍 5🤩 1
ገና እሰክርሻለው
.................................
አለሜ ዞረብኝ
አለምሽን ጠጥቼ፣
አንቺን እንዳልሰክር
የሚያስቆም አጥቼ፤
አንቺን መንገዳገድ
አንቺን መፈራረጥ፣
ትቦው ስር ተኝቶ
ነፍስሽን ማዳመጥ፤
ሚያነሳኝም የለ ስሜ በአንቺ ጠፍቷል
ከአፋቸው ትችትን ብያኔን ለምዶታል!
.
#ተስፋን ቆራረጥኩት እብደቱ ተስማማኝ
#እምነትንም ጣልኩት ጤናን ስላስጠማኝ
#ፍቅርሽን ግን....
ልቤም ሊፍቅ ዳዳው
ውሳኔን አጣለት
ዘላለም ይመስል
ላይጠፋ ማለለት!
እንዴት አልስከርሽ
እንዴትስ አልጩህሽ
እንደሌላው አትፈርጂም
ዝም እኮ ነው መልስሽ!
ዝም..
ቁዝም...!
ጭጭ....
ረጭ....፣
ትዝታን አስታውሶ
ሰክሮ መነጫነጭ!
ሁከት...፣
ጩኸት....!
የውስጥን አፍኖ
ላይን ማሰቃየት!
(ገና እሰክርሻለው)
By @Weyblann
@getem
@getem
@getem
❤ 25👍 10🔥 4👎 2😢 2😁 1
ሁለቱም ይኑሩ!
(የሞገሴ ልጅ)
አለመተዋወቅ..
አለመቀራረብ..
አለመነጋገር..
አለመደራረብ፤
ዶግማ ይሁን እና-
ብዙ ይራራቁ፣
አይነፋፈቁ፣
አይተዋወቁ፤
አንድ አይሁኑ እንጂ-
ችግር እንዳይመጣ፣
ኁለቱም ይኑሩ፣
ዐይን’ና ሚጥሚጣ።
By @eyadermoges
@getem
@getem
@paappii
❤ 39👍 7🤩 4🔥 2😁 1
ሞልታ ለማትሞላ ለዚች ድንቡሎ አለም
መታገል ነው እንጂ መነፋረቅ የለም
ቻለው ችግርህን እጅ አትስጥ ለማንም
የደከምን ለታ ይብሳል ህመምም
ላገደመ ሁሉ ብሶትን አታውጋው
እራስህ ላንተ ኑር
ቃልን ውጠህ ዝጋው።
ቧልተኛ ነው ሁሉም
አይኑርህ አንድ ሰው
የሚገፋህ ካለ
ክንድህን አጉርሰው።
አርግፍለት ጥርሱን
አቅምሰው የጅን ጥም
"መታገል ነው እንጂ
መነፋረቅ የለም" ይላል ይሄ ግጥም።
ዮኒ
ኣታን @yonatoz
@getem
@getem
@getem
❤ 62👍 18😱 7🔥 6🤩 5
ሰማሽ ወይ...
ያደለው ለሃገር - ጥይቱን ይጠጣል፣
ያላደለው ደግሞ - ቢራ ያማርጣል፤
ያገኘ ላምላኩ - እጁን ይዘረጋል፣
ተስፋ ያጣ ሃገር - ጥሎ ይጠረጋል፤
ታዳጊው ጎርምሶ - ለትዳር ይታጫል፣
ያመለጠው ኖሮ - በትላንት ይቆጫል፤
ኁሉም የየራሱን - እያነሳ ጣለው፣
ያንችን እና የኔን..........እኔስ ምን ልበለው?
By @eyadermoges
@getem
@getem
@getem
❤ 53👍 20🔥 8😱 4😢 4
ለምን ትመጫለሽ?
ወና መሆን ለምዷል
ባይተዋር ነው ሆዴ
ትራስ አቅፎ ማደር
ለምዶበታል ክንዴ።
ገላዬ ቀዝቅዟል
ልቤ ተሰቅዟል
እንስት ላለማመን
ዜሮ ነኝ ስተመን
ብትመጭም ከንቱ ነው
መመለስሽ ምንም
ስታወሪ አልስቅም
በእንባሽ አልቆዝምም
በድን ነኝ አልድንም ።
ለምን ትመጫለሽ?
የለሁም በድሮ
ሌላ ነኝ ዘንድሮ
ግዴ አይደለም ነገ
አትገርመኝም ጀንበር
ብራና ክረምቱ …
ቢዛወር ዓመቱ
ጨፍሬ አልደክርም
አልመታም አታሞ
ዓመት አንድ ቀን ነው
ለከሸፈ ታሞ ።
ለምን ትመጫለሽ ?
መምጣትሽ እንደ ቧልት
መመለስሽ ምንም ...
፡
ይህንን እያልኩኝ
ብናገር ብገጥምም
ስትመጪ ስዳበስ
በጣት በመዳፍሽ
ያልኩትን ዘንግቼ
አዲስ ሰው ሆንኩልሽ።
አትሄጂም አይደለ ?🙄
By (ሚካኤል አ)
@getem
@getem
@paappii
❤ 61😁 11👍 9🔥 5🤩 3
