ar
Feedback
ግጥም ብቻ 📘

ግጥም ብቻ 📘

الذهاب إلى القناة على Telegram

✔በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን። ✔ @getem @serenity13@wegoch @Words19@seiloch @shiyach_bicha@zefenbicha @leul_mekonnen1

إظهار المزيد
2025 عام في الأرقامsnowflakes fon
card fon
65 766
المشتركون
-324 ساعات
-397 أيام
-30130 أيام
أرشيف المشاركات
ወግና ትዉፊት ------------------ የማይስማማ ቢሆንም ወግ አጥባቂ፣ ለገላጋይ አይሉት ለልጅ አዋቂ፤ ጥሩ ነዉ ቢባል ወይም ጠቃሚ፣ የማይለወጥ ሀሳቡ ቋሚ፣ ቢሆንም እንኳን በጥብቅ ባህል የኖረ በፊት፣ የቀን ጉዳይ ነዉ መሸራረፉ ወግና ትዉፊት። @getem @getem @paappii
إظهار الكل...
18👍 6🔥 2😱 1🎉 1
አባትህ ገዳይ ፥ እናትህ ገዳይ ላንተ 'ሚተርፍህ ፥ ድርብርብ ስቃይ ! የሀበሻ ጥል ፥ ከልጅ ወደ ልጅ ስለሚቀጥል ፣ .... መቃብር ምሶ ፥ ታሪክ አጣቅሶ ያገኘህ እንደሁ ፥ ያ'ምናው ተበዳይ በ'ድልህ እዘን ፥ የራስህ ጉዳይ ! By Habtamu Hadera @getem @getem @paappii
إظهار الكل...
46😁 15🔥 10😢 2
አሜን አለሜን ~~ ልበል አለሜን አየሁ ነግቶ ሆነሽ ከጎኔ፣ ነቅቼ ወፎች ተንጫጭተው ሳየው አይንሽን 'ባይኔ። ልበል አሜን አሜን ነግቶ ሆነሽ ከጎኔ፣ ፀሀይ ብርሀን ፈንጥቃ ሳየው አይንሽን 'ባይኔ። `````````````````````````` Sep. 16, 2021, 12:31 PM by Daniel @DannyShy @getem @getem @getem
إظهار الكل...
35👍 3👎 1
"በቅርቡ ከሚወጣው መፅሐፌ ቅምሻ" ❤🙏 ወገቤ ላይ ታላቅ ቁስል የቁስል ሞት ታመኛለች፣ በስቅታ አፋፍ ሆኜ ትንሽ መኖር ታምረኛለች ትንሽ መኖር እያማረኝ በሞት እቅፍ ሳለሁ እንኳ የስኳር ማንኪያ ያህል ኑሮ ራሱ ጣፋጭ ሹካ ቁስል ሁሉ እከክ ወርሶኝ በሞት መሃል ሳጣጥር፣ ትንሽ መኖር ታምረኛለች ትንሽ ትንፋሽ ለመስከር፣ ጥይት ሁሉ ወርዶብኝ ሰውነቴን ቢበሳሳም፣ ትንሽ መኖር ታሳሳለች ከሞት ወሲብ ከመሳሳም፣ ትንሽ  መኖር ስጭኝ ባክሽ መኖር ባፌ ጉልበት ልሳም፣ ባክህ ቁስሌ መኖር ስጠኝ ህመም እንኳ አይደንቀኝም፣ ትንሽ እንኳ መኖር ከቻልኩ ጠባሳህም አይገለኝም፣ ትንሽ መኖር አማምሮኛል ለነብሰጡር በሞት ደጅ ፣ ትንሽ ልኑር ባክህ አልሙት ብወድቅ እንኳ በሰው እጅ፣ ትንሽ ብቻ መኖር መኖር የአምሮቴን ትንሽ እድል፣ ትንሽ ህመም ለቀቅ አርገኝ ኗሬለሁ ብዬ እንድል፣ ' ' @geez_mulat 🦘 ግዕዝ ሙላት @getem @getem @getem
إظهار الكل...
81🔥 6🎉 3
የፍቅር ሙከራ --------------------- አንድ አንዱ ለፍቅር ይጀምራል በቃል፣ በአይኑ ተመልክቶ ፍላጎቱ ያልቃል፤ ሌላኛው ይለያል በትንሽ ደባብሶ፣ ነካክቶ ሳይቀምስ ይሄዳል ጨራርሶ፤ ያንቺ ግን ሙከራ ከሁሉም ይልቃል ከሁሉም ይብሳል፣ አብሮ መዋል አልፎ መተኛት ይደርሳል። @getem @getem @paappii
إظهار الكل...
38😁 20😱 13👍 4👎 3🔥 3
የመሰለው እዛ ሆነሽ እዛ ማዶ፣ መራራቁን ልቤ ለምዶ። የሚረሳሽ መስሎት ነበር፣ ሰዓት ሲነጉድ ቀን ሲመተር። እውነቱማ ምን ሆንኩ እስክል እኔን እኔ፣ መበደሉ በራሴ ልብ ጭካኔ። እቀዝፋለሁ ባሳብ ባህር፣ ምን እንደማገኝ ሳላቅ ተሳክቶልኝ ብሻገር። ሲመጣበት በትዝታ ሲያጉረመርም የናፍቆት ጉም፣ ይከፋኛል አይገልፀውም ልቤ አይችለው ልክ የለውም። By @DannyShy, 2:27 PM, Mon. Oct. 10, 2022 @getem @getem @getem
إظهار الكل...
23👍 2😱 1
,  (   ጨረቃ ነሽ ወይ ፀሀይ ) አንዲት ፍሬ ልጅ ሞትን ምታስንቂ         በውድቅት ለሊት ደውል ሆነሽ መተሽ ሰውን  ምታነቂ ጨረቃ ነሽ ወይስ ፀሀይ ከሩቅ አብረቅራቂ   ብርድ እና ሙቀትን የሆንሽ አስታራቂ በድቅድቅ ጨለማ ያለን በጠራሞት ነጥቀሽ የምታዎጭ በዕድን ስጋን ከሞት ጨረቃ ነሽ ወይስ ፀሀይ ንገሪኝ አንቺዬ ለምጀው እንድኖር ሀሩርና ቁሩን እንደምንም ቺዬ     ጨረቃ ነሽ ወይስ ፀሀይ ንገሪኝ አንቺዬ ከዬትኛው ስነ ፍጥረት ልመድብሽ ከጨረቃ ከክዋከብት ከፀሀይ ጋር ልደርብሽ   ጨረቃ ነሽ ወይስ ፀሀይ ንገሪኝ አለሜ    አንቺን የሳልኩበት ሳይጠፋ ቀለሜ                እኔማ   እኔማ አንቺ ካልነገርሽኝ አልፅፍ ቃላትን      አልገነባም ጎጆን  የሚፈርስ ቤትን ስንቴ የሰራሁት ቤቴ ፈርሶ አልቆ አለም አንቺን ሚሞቅ በእኔ ላይ ተሳልቆ         ጨረቃ ነሽ ወይስ ፀሀይ ??????? By Habtish @getem @getem @getem
إظهار الكل...
24👍 15
ቤት እማ ጨዋ ነሽ፣ እንኳን ሌላ ሌላ እኔንም አታይም፣ ግን እድሜ ለሱሱ፣ ወተሽ ወዳጅ ካየሽ አታልፊም አትተይም። የሸመገለን ወንድ፣ በሰለቸ ዐይንሽ ዕያየሽ ወጠምሻ፣ የሱን መድሃኒት፣ አርገሽ ለቀን ያዝሽው የኔን ማስታገሻ።  By @eyadermoges @getem @getem @paappii
إظهار الكل...
33
           ወዴት ነህ?🚶🏻 ለመኖር ለመሞት ሲመሽ ሚጣደፉ ተራማጅ እግሮች አያለሁ ከሰልፉ:: የፀሐይን መጥለቅ መሽኮርመም ጠብቀው በመውጣት በመውረድ መንገዱን አጣበው÷ ወዴት ማዝገማቸው አውቀው ያላወቁ ከተራማጅ መሃል ሰልፉን ሚያደምቁ÷ ብዙ እግሮች አሉ ወርደው የሚወጡ መፅደቅ ወይም መርከስ አንዱን የመረጡ::                By @Abuugida @getem @getem @paappii
إظهار الكل...
26👍 7
Photo unavailableShow in Telegram
📍GHOST VOTE . Ghost'ን vote እናድርግ Ghosty’f sagalee kennaa ጎስት'ነ ድምጺ ሃቡሉ Ghost'ya keettidaa aayize ጎስት vot አምሮዊ Vote for Ghost Vote por Ghost 投票给阿比伊,صوّتوا لأبيي       - ለጎስት ቮት ! 👇  🙏 https://www.tca2025.com/category/21 SHARE @getem
إظهار الكل...
22👎 19😁 14
‎ከለታት ባንዱ ቀን ‎ህይወት ግቧን አውቀን ‎ኖረን ኖረን መጥቀን ‎በንባ ውዝፍ ስቀን ‎ ‎ከለታት ባንዱ ለት ‎ገፋንና ብረት ‎ቡጢ ተሰናዝረን በእጃችን ውጥረት ‎ ‎ግባችን ልንመታ ግብን አስተካክለን ‎አስቆጣሪ ጀግና በኛ ስም ወክለን ‎አክለን ‎በጥድፊያ ‎በልፊያ ‎ሰዓት አቀባብለን ‎ጊዜ ተቀባብለን ‎አንድ ሁኑ ስንባል ለየግል ተቆጥረን ‎ተዋደድን ብለን ካንገት ተወጣጥረን ‎ተመንጥረን ‎እንዳልሳቅን ‎አለቀስን ‎ ፌዝ እንዳልያዝን በልባችን ‎ ይበለን የታባታችን ‎ ‎ኖረን ኖረን መጥቀን ‎በንባ ውዝፍ ስቀን ‎አዙሮ ‎አዙሮ ‎ጊዜ ጣለን ከቀን። ‎ ‎ዮኒ ‎     ኣታን @yonatoz @getem @getem @getem
إظهار الكل...
31🔥 9👍 5🤩 1
ከልቤ መዝገብ ሰርዤ በደንብ ደልዤ በደንብ ያጠፋሁው መስሎኝ ስኮራ ስሞኝ ከየትኛው ጥግ ከፀዳው ልቤ ብቅ ትይና 'ባሳብ ምናቤ እንደረሳሁሽ እኔ ብል 'ባምንም ልቤ ይከዳል ትዝ ትይኛለሽ ምን ደስ ቢለኝ ምን ቢከፋኝም      መስከረም 13/18 ዓ/ም @DannyShy @getem @getem @getem
إظهار الكل...
43😢 4👎 2🔥 1
ገና እሰክርሻለው ................................. አለሜ ዞረብኝ አለምሽን ጠጥቼ፣ አንቺን እንዳልሰክር የሚያስቆም አጥቼ፤      አንቺን መንገዳገድ      አንቺን መፈራረጥ፣      ትቦው ስር ተኝቶ      ነፍስሽን ማዳመጥ፤ ሚያነሳኝም የለ ስሜ በአንቺ ጠፍቷል ከአፋቸው ትችትን ብያኔን ለምዶታል!    .    #ተስፋን ቆራረጥኩት እብደቱ ተስማማኝ    #እምነትንም ጣልኩት ጤናን ስላስጠማኝ    #ፍቅርሽን ግን.... ልቤም ሊፍቅ ዳዳው   ውሳኔን አጣለት ዘላለም ይመስል    ላይጠፋ ማለለት! እንዴት አልስከርሽ   እንዴትስ አልጩህሽ እንደሌላው አትፈርጂም   ዝም እኮ ነው መልስሽ! ዝም.. ቁዝም...! ጭጭ.... ረጭ....፣ ትዝታን አስታውሶ ሰክሮ መነጫነጭ!                   ሁከት...፣                   ጩኸት....!                   የውስጥን አፍኖ                   ላይን ማሰቃየት! (ገና እሰክርሻለው)    By @Weyblann @getem @getem @getem
إظهار الكل...
25👍 10🔥 4👎 2😢 2😁 1
ኗሪ መስለሽኝ ነውኮ ያኮረፍኩሽ ላናግርህ ላውራህ ፥ ስትይ ዝም ያልኩሽ ። አንቺኮ አታፍሪም ይሄኔ ቂም ትይዥ ይሆናል በእኔ እባክሽ ላንዳፍታ ንቂልኝ እንደምወድሽ እወቂልኝ ። By Habtamu hadera @getem @getem @paappii
إظهار الكل...
50😢 33🔥 6👎 3
ጥርስሽ ሀዘን ጠሪ     ሳቅሽ መርዶን አርጂ ደስታ በእጄ ገባች     ጥለሽኝ ስትሄጂ፤ በበደል ላይ በደል     ሰርክ እየደራረብሽ ማስመሰልሽ ከፍቶ    ልቤን እያሳዘንሽ፤ ብዙ አመት ታገሰ፣ይሄ ቻዩ ሆዴ ወትሮም ቅን ነውና የህይወት መንገዴ፤ ሂጂ.. ሂጂ..!   አው ሂጂ እየደላሽ፣ ልክ እንደ እንደኔ አይነቱን   ባላሰበው መንገድ    አሳር እያበላሽ! ሂጂ By @Weyblann @getem @getem @getem
إظهار الكل...
67🔥 9👍 5
ሁለቱም ይኑሩ! (የሞገሴ ልጅ) አለመተዋወቅ.. አለመቀራረብ.. አለመነጋገር.. አለመደራረብ፤ ዶግማ ይሁን እና- ብዙ ይራራቁ፣ አይነፋፈቁ፣ አይተዋወቁ፤ አንድ አይሁኑ እንጂ- ችግር እንዳይመጣ፣ ኁለቱም ይኑሩ፣ ዐይን’ና ሚጥሚጣ። By @eyadermoges @getem @getem @paappii
إظهار الكل...
39👍 7🤩 4🔥 2😁 1
‎ሞልታ ለማትሞላ ለዚች ድንቡሎ አለም ‎መታገል ነው እንጂ መነፋረቅ የለም ‎ቻለው ችግርህን እጅ አትስጥ ለማንም ‎   የደከምን ለታ ይብሳል ህመምም ‎ላገደመ ሁሉ ብሶትን አታውጋው ‎እራስህ ላንተ ኑር ‎        ቃልን ውጠህ ዝጋው። ‎ቧልተኛ ነው ሁሉም ‎         አይኑርህ አንድ ሰው ‎የሚገፋህ ካለ ‎          ክንድህን አጉርሰው። ‎አርግፍለት ጥርሱን ‎      አቅምሰው የጅን ጥም ‎ "መታገል ነው እንጂ ‎መነፋረቅ የለም" ይላል ይሄ ግጥም። ‎ ‎ ዮኒ ‎     ኣታን @yonatoz@getem @getem @getem
إظهار الكل...
62👍 18😱 7🔥 6🤩 5
ሰማሽ ወይ... ያደለው ለሃገር - ጥይቱን ይጠጣል፣ ያላደለው ደግሞ - ቢራ ያማርጣል፤ ያገኘ ላምላኩ - እጁን ይዘረጋል፣ ተስፋ ያጣ ሃገር - ጥሎ ይጠረጋል፤ ታዳጊው ጎርምሶ - ለትዳር ይታጫል፣ ያመለጠው ኖሮ - በትላንት ይቆጫል፤ ኁሉም የየራሱን - እያነሳ ጣለው፣ ያንችን እና የኔን..........እኔስ ምን ልበለው? By @eyadermoges @getem @getem @getem
إظهار الكل...
53👍 20🔥 8😱 4😢 4
ካላንተ አልኖርም፤ ብኖርም አልደምቅም፤ እያልኩኝ ዘርዝሬ፤ ቃላትን መንጥሬ፤ አልሸነግልህም። በጣም እንዲገርምህ፤ እንደዉም ልንገርህ፤ ከተራራቅን ወዲህ... ካገኘሁት ጋራ፤ ካገኘሁት ስፍራ፤ ካገናኘኝ መንገድ፤ እንባዬ እስኪወርድ፤ ፈገግታ አበዛለሁ፤ ናፈቅኸኝ መሰለኝ... አብዝቼ እስቃለሁ። በዔደን ታደሰ @ediwub @getem @getem
إظهار الكل...
31👍 28🔥 10😢 4
ለምን ትመጫለሽ? ወና መሆን ለምዷል ባይተዋር ነው ሆዴ ትራስ አቅፎ ማደር ለምዶበታል ክንዴ። ገላዬ ቀዝቅዟል ልቤ ተሰቅዟል እንስት ላለማመን ዜሮ ነኝ ስተመን ብትመጭም ከንቱ ነው መመለስሽ ምንም ስታወሪ አልስቅም በእንባሽ አልቆዝምም በድን ነኝ አልድንም ። ለምን ትመጫለሽ? የለሁም በድሮ ሌላ ነኝ ዘንድሮ ግዴ አይደለም ነገ አትገርመኝም ጀንበር ብራና ክረምቱ … ቢዛወር ዓመቱ ጨፍሬ አልደክርም አልመታም አታሞ ዓመት አንድ ቀን ነው ለከሸፈ ታሞ ። ለምን ትመጫለሽ ? መምጣትሽ እንደ ቧልት መመለስሽ ምንም ... ፡ ይህንን እያልኩኝ ብናገር ብገጥምም ስትመጪ ስዳበስ በጣት በመዳፍሽ ያልኩትን ዘንግቼ አዲስ ሰው ሆንኩልሽ። አትሄጂም አይደለ ?🙄 By (ሚካኤል አ) @getem @getem @paappii
إظهار الكل...
61😁 11👍 9🔥 5🤩 3