ru
Feedback
ግጥም ብቻ 📘

ግጥም ብቻ 📘

Открыть в Telegram

✔በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን። ✔ @getem @serenity13@wegoch @Words19@seiloch @shiyach_bicha@zefenbicha @leul_mekonnen1

Больше
2025 год в цифрахsnowflakes fon
card fon
65 764
Подписчики
-324 часа
-397 дней
-30130 день
Архив постов
( እወቅ ... ) ========= የትላንትህ ሞገስ ከመንደር ከቀዬው አዛውንት ሲጠፉ እወቅ ታሪኮችህ በሀሩር ጠውልገው እንደረጋገፉ ... ነገን የሚያበሩ ሕጻናት ረብሻ ሲናፈቅ በሀገሩ እወቅ ተስፋዎችህ ያለ አቅም ተጭነው እንደተሰበሩ ... እናማ አሁንህ ቢተልቅ ቢገዝፍ በጊዜ ሲተለም መቼም አትኮፈስ ከትላንት ያልመጣ ወደ ነገ ማይሄድ ብርቱ ' ዛሬ ' የለም !!! By @Kiyorna @getem @getem @getem
Показать все...
31👍 27🤩 4
የልብ ልሳኑ ስሜትና ቅፅበት ማሰብ፣ማመዛዘን የአይምሮ አንደበት (ሆነና ነገሩ) ሲሰናዳ አፍቃሪ ፍቅር ባቢሎን ላይ አርማውን ሊሰቅል ጊዜ አምላክ ሲፈርድ ልብና አይምሮ ቋንቋቸው ለየቅል By @Absari_seven @getem @getem
Показать все...
31🔥 6👍 5
ሚስጥረኛ ብዬ ሚስጥሬን ብነግርሽ፣ ሚስጥሩ ነው ብለሽ በሚስጥር ተናገርሽ፤ ያ ሚስጥር በሚስጥር ሲዞር ሲዞር ውሎ፣ በሚስጥር ነገሩኝ ሚስጥር ነው ተብሎ። @getem @getem @paappii
Показать все...
😁 130 58👍 12🔥 8👎 3
መስከረም ------------------------ አበቦች ለምልመው ፀሀይ ሳያት ደምቃ፣ በፍንጣቂዋ አደይ አበባ ፀድቃ፤ በየቦታዉ ደስታ በየቦታው ጥንዶች፣ ባጠገቤ ሲያልፉ ቆነጃጅት ሴቶች፤ አሻግሬ በሀሳብ እያየዉ ስገረም፣ ትዝ ትይኛለሽ ሲመጣ መስከረም። @getem @getem @paappii
Показать все...
64👍 5😢 5🤩 5🔥 3😁 2
ህፃን አዋቂ ሳይል በሚል ቀርጥፎ አኝኮ፣ ሰውን አታሎ ሚያሰቀር በመርዝ አንደበቱ ሰብኮ፤ ስለ አይኑ ብዛት ስለ ፈርጣማ እግሮቹ፣ የእሱን ክፋት ሀያልነት ስለ ትላልቅ እጆቹ፤ በሚል ተረት ተራቶች እያደግን ስለመጣን፣ በህይወት መስመር ጎዳና የፍቅርን ጣእም አጣን። @getem @getem @paappii
Показать все...
40👍 11🔥 7😁 5😢 3
አንዱ ለአገሩ ፤ አንዱ ለ'ርስቱ ፤ አንዱ ለልጁ ፤ አንዱ ለሚስቱ ፤ ጥይት ወልውሎ ፤ ጎራዴ ስሎ ፤ በዱር በገደል ይከታከታል ፤ ሲሻው ይገድላል ፤ ሲሻው ይሞታል ። እኔ ግን ወዲህ . . . ወይ አገር የለኝ ፤ ወይ ርስት የለኝ ፤ ወይ ልጅ አልወለድኩ ፤ ሚስት አላደለኝ ፤ ጎራዴ ሳልስል ፤ ጥይት ሳልገዛ ፤ በተኛሁበት ሀሳብ ገደለኝ ። By Tewodros kassa @getem @getem @paappii
Показать все...
👍 57 50😁 29🔥 6😱 3😢 1🎉 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
ART EXHIBITION WITHOUT WORDS solo Exposition by HANI MIKIYAS At STUDIO 11 Don't Miss this Date: 19n September Time: 5-10pm Location: Bole, Next to Ambassador Hotel Zemilo Hotel, 1stFloor @seiloch
Показать все...
11😱 1
የመሄድሽ ነገር፣ ምክንያቱ ባይገባኝ መጨከን ቢከብደው፣ አንቺን ላልል በቃኝ ስለት ገበው ለእግዜር፣ ለፈጠረን ጌታ ድንገት ካመጣልኝ፣ ለመክፈል ውለታ ስለት አስገብቼ፣ ስመጣ ከቤቴ ካንቺ ምትበልጠውን፣ በገኝ ከማጀቴ ይቺን አታሳጣኝ፣ ብዬ እየለመንኩኝ የቅድሙን ስለት፣ ተው ልለው ተሳልኩኝ። @getem @getem @paappii
Показать все...
😁 66 43🔥 7🤩 7😱 6
ጭር እንዳለ ቀን ዝም እንዳለ ሌት በጥባጭ ህጻን ልጅ እንደሌለው ቤት ቆሌ እንደራቀው አዚማም ሀሙስ እንደ ጫት ድባብ እንደ ቡና ሱስ ቅር ቅር አልሽኝ... ማተብ እንዳጣ ራቁት አንገት እንደ ዋዜማ እንደ አዲስአመት ( ሆቴል እንደተከበረ አውዳመት... ) ቅር ቅር አልሽኝ... ውዱዕ ሳያደርግ እንደሰገደ እያመነታ እንደፈረደ ሳይሰናበት ርቆ እንደ ሄደ ። ቅር ቅር አልሽኝ... እንደ መሰልጠን በትዝታ ላይ እንደመጨከን እንደ ሩቅ ሀገር የማይለመድ እንግዳ ነገር ቅር ቅር አልሽኝ... ጨርሰው እንዳልቆረጧት ጥፍር እንዳላፈረጧት ትንሽዬ ብጉር በጥርስ መሐከል እንደ ገባች ስጋ እየናፈቅሽኝ እያጓጓሽኝ አልዋጥ አልሽኝ ። ቅር ቅር አልሽኝ ... by Hab HD @getem @getem @paappii
Показать все...
65👍 16🔥 2😁 2🎉 2😱 1
በማያልቅ ሩጫ በማይበርድ ፍጥጫ መርጋት በሌለበት መዋተት..... ሁልጊዜ መጣደፍ በቁስአለም መክነፍ እፍፍፍፍ...... በጎዶሎ ፅዋ በሰባራ ፎሌ ደጋግሞ መጨለፍ መንጠፍ........ መኖር እንዲ ሆኖ ያለረፍት መክነፍ መሞት ሆኗል ማረፍ።            By @poetkidus @getem @getem @getem
Показать все...
45👍 16🔥 3🤩 1
(በዕምዓዕላፍ)             የማፍቀርን ያክል             መውደድን የሚያክል             ምን አለ ትክክል ? የፍቅር  ምትሀት   ካባውን ደርቦ በወዳጅ አይን ላይ  ማሳዬት አስውቦ             ገላ ኩንስንሱን              ደርቦ ሞገሱን ግዘፍ    ረቂቀ ስልቱ ማብቃት  ፍቅር ምትሀቱ                     እንከን የለሽ ውበት                     ፅንፍ የለሽ መለኮት እፁብ ድንቅ        ፍቅር  እምነታችን        መቅደሱ ገላችን        መሲህ ለምናችን       ህያው ናት ነፍሳችን                     ___እፁብ ድንቅ                                        እፁብ ድንቅ____ @getem @getem @getem
Показать все...
40👍 5🎉 1
ከጭፈራው መሐል አበባዮሽ እያልን ስንዞር ከየቤቱ፣ ቄጠማ ተይዞ ተለብሶ የክቱ። ጨዋታዉ ሲደራ የከበሮዉ ድልቂያ፣ የድምድምታዉ ጩኸት ሆኖ ፈንጠዝያ። ከጭፈራዉ መሐል ስትወርድ በእስክስታ፣ መቀነት ታጥቄ ሳይህ በስርቅታ። በነፋስ ሽዉታ አይናችን ተጋጭቶ፣ በሴኮንድ እይታ ልባችን አዉግቶ። ፀሐይ ስታበስር የድል ብስራት ዜማ፣ እስክስታዉ ሰደደን ወደ ፍቅር ማማ።            በዔደን ታደሰ @topazionnn @getem @getem 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
Показать все...
45🔥 5😁 3👎 2
    ኔ        ም! ሙሴን ስትሰጠው ባህርን ሚከፍል ለዳዊት ጠጠር ጎሊያድን የሚጥል ምን አል በሰጠኸኝ ለኔም ልዩ አቅም ቁስሏን ማድንበት ሀገሬን የሚጠቅም፡፡                        by   @Abuugida ᵗˢᵉᵍˢʰ @getem @getem @getem
Показать все...
78🔥 18👍 15🤩 2
ቄጠማ ሆነብኝ እግሬ| አቃተኝ ነፍሴን ማበርታት በይግባኝ ሸንጎ ገጥሜህ    ---በአርምሞህ ቃሌን በመርታት ስታውቀው የዓለም መልኩን አጨኀኝ ለመከራ ቁር ክፍት ነው ደጄን አትቆርቁር!። ° በል ግባ እንደ አብርሃም ቤት ጓዳዬን ማጀቴን ቃኘው ሰባራ ሸክላዬን ጥጄ በምኞት ሆዴን ሳሞኘው አረፍ በል ከሳር ፍራሼ አይመች ለገላ አይመጥን ሳለቅስ ሳነባ አድራለሁ ውል አልባ ህልሜን ስወጥን በል ባርካት ደሳሳ ዳሴን በፍቅርህ መሰረት አጽናት ካልሆነም ስጋን አፍርሰህ የዛለች ነፍሴን አድናት!። ° ተመልክት የዓለም መልኩን ተለምዷል ወድቆ መረሳት ጎዳናው ዕንባ ጠገበ ይፋጃል ዕግርን እንደ እሳት!!! ስታውቀው የዓለም መልኩን አጨኀን ለመከራ ቁር ክፍት ነው ደጄን አትቆርቁር!። #የአብስራ_ሳሙኤል @YabisraSamuel @getem @getem @getem
Показать все...
54😢 8🔥 7🎉 3
ዉስጤ ረቂቅ ነበር ፣ ጣፍጦ የጎመራ፣ ትልቅ ምትሀት ያለው፣ ማንንም ሚጠራ። አንቺ ደግሞ ጥሬ፣ ለመብሰል ሚቀርሽ፣ ገና ለጋ ቅጠል፣ የማይስብ ወዘናሽ። ምንም ብስል ቢሆን፣ አንድ ጣፋጭ ፍሬ ምንም ለምለም ቢሆን፣ ቢጣፍጥም ዛሬ። ግዜ፣ ቦታ፣ ምክንያት፣ ካልተገጣጠሙ ፍሬውም፣ ይረግፋል፣ ደስ አይልም ጣሙ። ፍሬሽ ፍሬ አፍርቶ፣ ቢጣፍጥም አድጎ፣ አንቺን ለማብሰል ስል፣ ለካስ መሬት ነበር ፣ የኔማ ጠዎልጎ። @getem @getem @paappii
Показать все...
48👍 8😱 3🔥 1
ጷግሜ . . 'ያመት ማካታቻ የቀናት ጭማሪ፤ የተስፋን ፀዳል ንጋት አብሳሪ፤ በሩፋኤል ጠበል ከበራችን ወተን፤ የዝናቡ ወጨፎ ብርዱ ሳይበግረን፤ በጉጉት ስንጠብቅ እስኪደርስ ቀኑ፤ አደይዋ እስክትፈካ ሲለወጥ ዘመኑ፤ በአዲሱ ልብሳችን እጅጉን ተዉበን፤ አበባዮሽ ስንል የክቱን ለባብሰን፤ የልጅነት ጊዜ..... በትዝታ አስጉዞ ሁሌም ይናፈቃል፤ እንደ እንቦሳ ጥጆች ዘወትር ያስቦርቃል። ..................................... ዔደን ታደሰ @topazionnn @getem @getem
Показать все...
86🤩 6👍 2
ህይወት ግን ምንድ ነው? ህይወት ግን ምንድ ነው ከዉስብስቡ አለም ግንኙነት ያለው እንደፈለገ የሚያስደስት የሚያሳዝነው ህይወት ግን ምንድን ነው ለብዙ ነገሮች ጥያቄ የሆነው ከጥልቁ ባህር አጥልቆ ሚያስቀረው ግን ህይወት ምንድን ነው??????? አልቅሶ አለመሳቅ አቶ አለማግኘት አዝኖ አለመደሰት ነው አይደል? ህይወት 😊😊😊 Kal..... @pilopater @getem @getem @getem
Показать все...
29👎 12👍 5🔥 1
ሥትገቢ ሥትወጪ- ዐይኔ ተደሥቶ ልቤን የሚያሞቀው፣ ዝቅ በል ሥትይኝ፣ መውረዴ ተክቦ - ክብሬን የሚንቀው። በመናኛ ቀልድሽ- እንድያ የምሥቀው - ድዴ እሥኪሠበር፣ አሁን የማይገባኝ፣ ያን ሠሞን ግን ካንቺ - ምን ፈልጌ ነበር? (የሞገሤ ልጅ) By @eyadermoges @getem @getem @getem
Показать все...
24😁 22🔥 4
አካልን ቢያስጠብቁት   በድካም ቢወቁት ልብ የጠበቀ ለታ ህመምና ዋይታ። ዮኒ      ኣታን @yonatoz @getem @getem @getem
Показать все...
13😢 9👍 1
[ #ለእሷ! ] የመዋደዳችን አበቃ ምዕራፉ የመገናኛችን ተዘጋ በራፉ ለምለም ምኞታችን እንደ ጉም በነነ ዘላለም ነው ያልነው ቅጽበታችን ሆነ። ━━━━━━━━━━━━━━━━━━ ያኔ በመስታወት ጡቦች በታሰረ ብርሀን  ጎጆ'ችንን መልተን ከገበታችን ላይ ፍቅርን ዘርግተን መውደድ በትኩሱ የተቋደስንበት ነፍሳችን ጥለን ህጻን የሆንበት ዛሬ እንደ ትዝታ በምኞት ይገርፋል አየሩ ንፋሱ "የለሽም" ብሎ ያልፋል ። ━・・・━ ★ ━・・・━ የለሽም የለሽም የመስታወት ጡቡ ወድቆ ተሰበረ  ብርሀን ጸዳሉ ወዳንቺ በረረ  በስብርባሪ ውስጥ ጸጸት ብቻ ቀረ በጊዜ ጠብታ ትዝታን ያዘለ.  .  . ✿ ይኀው እዛች'ጋ  የገጽሽ ሀመልማል ጽልመቱን ይቀዳል  ከሳቅ ከጭዋታሽ ብርሀን ይወለዳል እንደ ጀንበር ውበት በማለዳው ይሄዳል። ይኀው እዛች'ጋ የዳናሽ ማህሌ' ሀዘኔን ሳያስረሳኝ  ኮልታፋ አንድበትሽ በፍቅር ሲያነሳኝ ህይወት እንደ ምንጣፍ እየጠቀለለው  ከትዝታ መቅረዝ ሰብስቦ ሲጥለው ። ✿ ይኀው ወደ አንቺ ጋር  ዛሬም እንደ ትናንት ልቤ ይሰደዳል  ተስፋውን ሰንቆ ለምኞቱ ይሄዳል ከንፋስ ከአየሩ ♡  ከዛፍ ከቅጠሉ ♡ የለሽም የለሽም የሚል ኦና ቃላት በምጥ ይወለዳል!። ━━━━━━━━━━━━━━━━━━ #የአብስራ_ሳሙኤል @YabisraSamuel @getem @getem @getem
Показать все...
48👍 7🔥 4