ግጥም ብቻ 📘
Відкрити в Telegram
✔በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን። ✔ @getem @serenity13 ✔ @wegoch @Words19 ✔ @seiloch @shiyach_bicha ✔ @zefenbicha @leul_mekonnen1
Показати більше2025 рік у цифрах

65 764
Підписники
-324 години
-397 днів
-30130 день
Архів дописів
Показати все...
❤ 31👍 27🤩 4
የልብ ልሳኑ ስሜትና ቅፅበት
ማሰብ፣ማመዛዘን የአይምሮ አንደበት
(ሆነና ነገሩ)
ሲሰናዳ አፍቃሪ
ፍቅር ባቢሎን ላይ አርማውን ሊሰቅል
ጊዜ አምላክ ሲፈርድ
ልብና አይምሮ ቋንቋቸው ለየቅል
By @Absari_seven
@getem
@getem
❤ 31🔥 6👍 5
Показати все...
👍 57❤ 50😁 29🔥 6😱 3😢 1🎉 1
Repost from ሥዕል ብቻ ©
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ART EXHIBITION
WITHOUT WORDS
solo Exposition by HANI MIKIYAS
At STUDIO 11
Don't Miss this
Date: 19n September
Time: 5-10pm
Location: Bole, Next to Ambassador Hotel
Zemilo Hotel, 1stFloor
@seiloch
❤ 11😱 1
ጭር እንዳለ ቀን
ዝም እንዳለ ሌት
በጥባጭ ህጻን ልጅ
እንደሌለው ቤት
ቆሌ እንደራቀው አዚማም ሀሙስ
እንደ ጫት ድባብ
እንደ ቡና ሱስ
ቅር ቅር አልሽኝ...
ማተብ እንዳጣ ራቁት አንገት
እንደ ዋዜማ እንደ አዲስአመት
( ሆቴል እንደተከበረ አውዳመት... )
ቅር ቅር አልሽኝ...
ውዱዕ ሳያደርግ እንደሰገደ
እያመነታ እንደፈረደ
ሳይሰናበት ርቆ እንደ ሄደ ።
ቅር ቅር አልሽኝ...
እንደ መሰልጠን
በትዝታ ላይ እንደመጨከን
እንደ ሩቅ ሀገር
የማይለመድ እንግዳ ነገር
ቅር ቅር አልሽኝ...
ጨርሰው እንዳልቆረጧት ጥፍር
እንዳላፈረጧት ትንሽዬ ብጉር
በጥርስ መሐከል እንደ ገባች ስጋ
እየናፈቅሽኝ
እያጓጓሽኝ
አልዋጥ አልሽኝ ።
ቅር ቅር አልሽኝ ...
by Hab HD
@getem
@getem
@paappii
❤ 65👍 16🔥 2😁 2🎉 2😱 1
በማያልቅ ሩጫ
በማይበርድ ፍጥጫ
መርጋት በሌለበት
መዋተት.....
ሁልጊዜ መጣደፍ
በቁስአለም መክነፍ
እፍፍፍፍ......
በጎዶሎ ፅዋ
በሰባራ ፎሌ
ደጋግሞ መጨለፍ
መንጠፍ........
መኖር እንዲ ሆኖ
ያለረፍት መክነፍ
መሞት ሆኗል ማረፍ።
By @poetkidus
@getem
@getem
@getem
❤ 45👍 16🔥 3🤩 1
ከጭፈራው መሐል
አበባዮሽ እያልን ስንዞር ከየቤቱ፣
ቄጠማ ተይዞ ተለብሶ የክቱ።
ጨዋታዉ ሲደራ የከበሮዉ ድልቂያ፣
የድምድምታዉ ጩኸት ሆኖ ፈንጠዝያ።
ከጭፈራዉ መሐል ስትወርድ በእስክስታ፣
መቀነት ታጥቄ ሳይህ በስርቅታ።
በነፋስ ሽዉታ አይናችን ተጋጭቶ፣
በሴኮንድ እይታ ልባችን አዉግቶ።
ፀሐይ ስታበስር የድል ብስራት ዜማ፣
እስክስታዉ ሰደደን ወደ ፍቅር ማማ።
በዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
@getem
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
❤ 45🔥 5😁 3👎 2
ቄጠማ ሆነብኝ እግሬ| አቃተኝ ነፍሴን ማበርታት
በይግባኝ ሸንጎ ገጥሜህ
---በአርምሞህ ቃሌን በመርታት
ስታውቀው የዓለም መልኩን አጨኀኝ ለመከራ ቁር
ክፍት ነው ደጄን አትቆርቁር!።
°
በል ግባ እንደ አብርሃም ቤት
ጓዳዬን ማጀቴን ቃኘው
ሰባራ ሸክላዬን ጥጄ
በምኞት ሆዴን ሳሞኘው
አረፍ በል ከሳር ፍራሼ
አይመች ለገላ አይመጥን
ሳለቅስ ሳነባ አድራለሁ
ውል አልባ ህልሜን ስወጥን
በል ባርካት ደሳሳ ዳሴን
በፍቅርህ መሰረት አጽናት
ካልሆነም ስጋን አፍርሰህ
የዛለች ነፍሴን አድናት!።
°
ተመልክት የዓለም መልኩን
ተለምዷል ወድቆ መረሳት
ጎዳናው ዕንባ ጠገበ
ይፋጃል ዕግርን እንደ እሳት!!!
ስታውቀው የዓለም መልኩን አጨኀን ለመከራ ቁር
ክፍት ነው ደጄን አትቆርቁር!።
#የአብስራ_ሳሙኤል
@YabisraSamuel
@getem
@getem
@getem❤ 54😢 8🔥 7🎉 3
Показати все...
❤ 48👍 8😱 3🔥 1
ጷግሜ
.
.
'ያመት ማካታቻ የቀናት ጭማሪ፤
የተስፋን ፀዳል ንጋት አብሳሪ፤
በሩፋኤል ጠበል ከበራችን ወተን፤
የዝናቡ ወጨፎ ብርዱ ሳይበግረን፤
በጉጉት ስንጠብቅ እስኪደርስ ቀኑ፤
አደይዋ እስክትፈካ ሲለወጥ ዘመኑ፤
በአዲሱ ልብሳችን እጅጉን ተዉበን፤
አበባዮሽ ስንል የክቱን ለባብሰን፤
የልጅነት ጊዜ.....
በትዝታ አስጉዞ ሁሌም ይናፈቃል፤
እንደ እንቦሳ ጥጆች ዘወትር ያስቦርቃል።
.....................................
ዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
@getem
❤ 86🤩 6👍 2
ህይወት ግን ምንድ ነው?
ህይወት ግን ምንድ ነው
ከዉስብስቡ አለም ግንኙነት ያለው
እንደፈለገ የሚያስደስት የሚያሳዝነው
ህይወት ግን ምንድን ነው
ለብዙ ነገሮች ጥያቄ የሆነው
ከጥልቁ ባህር አጥልቆ ሚያስቀረው
ግን ህይወት ምንድን ነው???????
አልቅሶ አለመሳቅ አቶ አለማግኘት
አዝኖ አለመደሰት ነው አይደል? ህይወት 😊😊😊
Kal..... @pilopater
@getem
@getem
@getem
❤ 29👎 12👍 5🔥 1
ሥትገቢ ሥትወጪ-
ዐይኔ ተደሥቶ ልቤን የሚያሞቀው፣
ዝቅ በል ሥትይኝ፣
መውረዴ ተክቦ - ክብሬን የሚንቀው።
በመናኛ ቀልድሽ-
እንድያ የምሥቀው - ድዴ እሥኪሠበር፣
አሁን የማይገባኝ፣
ያን ሠሞን ግን ካንቺ - ምን ፈልጌ ነበር?
(የሞገሤ ልጅ)
By @eyadermoges
@getem
@getem
@getem
❤ 24😁 22🔥 4
[ #ለእሷ! ]
የመዋደዳችን አበቃ ምዕራፉ
የመገናኛችን ተዘጋ በራፉ
ለምለም ምኞታችን እንደ ጉም በነነ
ዘላለም ነው ያልነው ቅጽበታችን ሆነ።
━━━━━━━━━━━━━━━━━━
ያኔ
በመስታወት ጡቦች በታሰረ ብርሀን
ጎጆ'ችንን መልተን
ከገበታችን ላይ ፍቅርን ዘርግተን
መውደድ በትኩሱ የተቋደስንበት
ነፍሳችን ጥለን ህጻን የሆንበት
ዛሬ እንደ ትዝታ በምኞት ይገርፋል
አየሩ ንፋሱ "የለሽም" ብሎ ያልፋል ።
━・・・━ ★ ━・・・━
የለሽም የለሽም
የመስታወት ጡቡ ወድቆ ተሰበረ
ብርሀን ጸዳሉ ወዳንቺ በረረ
በስብርባሪ ውስጥ ጸጸት ብቻ ቀረ
በጊዜ ጠብታ ትዝታን ያዘለ. . .
✿
ይኀው እዛች'ጋ
የገጽሽ ሀመልማል ጽልመቱን ይቀዳል
ከሳቅ ከጭዋታሽ ብርሀን ይወለዳል
እንደ ጀንበር ውበት በማለዳው ይሄዳል።
ይኀው እዛች'ጋ
የዳናሽ ማህሌ' ሀዘኔን ሳያስረሳኝ
ኮልታፋ አንድበትሽ በፍቅር ሲያነሳኝ
ህይወት እንደ ምንጣፍ እየጠቀለለው
ከትዝታ መቅረዝ ሰብስቦ ሲጥለው ።
✿
ይኀው ወደ አንቺ ጋር
ዛሬም እንደ ትናንት ልቤ ይሰደዳል
ተስፋውን ሰንቆ ለምኞቱ ይሄዳል
ከንፋስ ከአየሩ ♡
ከዛፍ ከቅጠሉ ♡
የለሽም የለሽም
የሚል ኦና ቃላት በምጥ ይወለዳል!።
━━━━━━━━━━━━━━━━━━
#የአብስራ_ሳሙኤል
@YabisraSamuel
@getem
@getem
@getem
❤ 48👍 7🔥 4
