uk
Feedback
ግጥም ብቻ 📘

ግጥም ብቻ 📘

Відкрити в Telegram

✔በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን። ✔ @getem @serenity13@wegoch @Words19@seiloch @shiyach_bicha@zefenbicha @leul_mekonnen1

Показати більше
2025 рік у цифрахsnowflakes fon
card fon
65 764
Підписники
-324 години
-397 днів
-30130 день
Архів дописів
------------------------ የለት ተቀን ስራ ድግግሞሽ ብዛት፣ ጥሩም ቢሆን መጥፎ ያሳለፍነዉ ግዚያት፣ አንድ አንዴ በፌሽታ በደስተ መፍለቅለቅ፣ ደግሞ ሌላ ግዜ በእንባ መንሰቅሰቅ፣ ለዚ ዉጣ ውረድ ባናገኝ ተማጽኖ፣ ምንም እንኳን እድል ቢኖረዉም ተጽኖ፣ ከሁሉም ሚሻለዉ ከሚመጣዉ ክስረት፣ ከሴጣንም በላይ ልማድን ነዉ መፍራት። @getem @getem @paappii
Показати все...
31👍 14🔥 4😢 1🤩 1
የኔ ሳቅ . . ሁሉም ለየብቻዉ              እንደተለያየ የኔ ሳቅ ለብቻው               ከኔ ጋራ ቆየ አየሁት ሰማሁት           ሁሉን ተረዳሁት ሳቄን ለማርከሻ              ቢቸግር ጠጣሁት              ቢቸግር በላሁት              እንደ ጎሽ ጠላ              እንደ 'ባር ማሽላ ሳቄን ለማርከሻ               ከነገዉ መድረሻ               መረጥኩት ጠላሁት                ይስቃል እንዲሉኝ               ጥርሴን ተነቀስኩት @topazionnn @getem @getem
Показати все...
37🔥 4😢 4👍 2😱 1
      "ይጠፋል" --------------------------- ፀጉሬን ሽበት ወሮት ፊቴም ቢጨማደድ፣ የወጣትነቴ ወዛናው ቢጠፋ ምን ቢመስል አመድ፣ ክንዴም አቅመ ቢስ ወኔዬም የከዳኝ፣ ያለኝ ጥቂት እድሜ ያለኩኝ አለም በቃኝ፣ እርጅና እንደ ከንፈር ቢመጣ አሞጥሙጦ፣ እንዴት ብወድሽ ነዉ አንቺን ባሰብኩ ቁጥር፣ ሚጠፋው ደንግጦ። @getem @getem @paappii
Показати все...
38👍 11😱 1
Repost from N/a
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ሰላም ወዳጆች ዛሬ 9:30 አራት ኪሎ በዋልያ ቡክስ አዳራሽ የወዳጄ የኪሩቤልን መፅሐፍ እናስመርቃለን። የምትችሉ እዛው እንገናኝ። ማስታወሻ የኔን ምስል እዚ ውስጥ ፈልጎ ላገኘ የመጀመሪያው ሰው መፅሐፉን እሸልማለሁ...😅🙏
Показати все...
18
ጥርሷ ሰዋሪ ሳቋ ነዳፊ ፤ ከንፈሯ ገዳይ ዐይኗ ገራፊ ፤ ፀጉሯ ሐመልማል ልብሷ ደመና ፤ ገላዋ አበባ ቃናዋ ናና ፤ ልክ እንደ ሰንደል ልክ እንደ ብርጉድ ፤ የቀመሷት ለት የምታስብል ጉድ ! ከሰማይ በቀር የምድር አፈር የማይመጥናት ፤ ከመለዓክ በቀር በሳር በቅጠል የማይመስሏት ፤ ልጅማ ልጅ ናት ! ጨረቃ ኮኮብ የሚሰግዱላት አበቦች ከዱር የሚያረግዱላት ፤ የሚገድሉላት የሚሞቱላት ከአንቺ ጋ አድሬ ሲነጋ ልሙት የሚዘፍኑላት ፤ ልጅማ ልጅ ናት ! ሲሻት በምድር ሲሻት በሰማይ የምታበራ ፤ ነፍስ የምታስት ስትስቅ ስትኮራ ፤ እንኳን ለአዘቦት ለክት ለዓመት ባል የሚሸሽጓት ፤ እንኳን በፀሐይ ሌት በጨረቃ በሩቅ የሚያውቋት ፤ ልጅማ ልጅ ናት ! እንኳን ቁሞ ሃጅ ሙቶ የተኛን ታሳብዳለች ፤ እንኳን የሰው ዘር ባህሩን ወንዙን ታስረግዳለች ፤ ከፍቅር በቀር ሌላ አይችላትም ፤ ከራሷ በቀር የቱም አበባ አይመጥናትም ፤ የምድር ዕንቁ ናት የምድር አበባ ፤ እንዲሁ ታይታ ዐይን የምትገባ ፤ እንዲሁ ታይታ ቀን ታፈካለች ፤ በዐይኖቿ ብቻ ውኃን ወደ ወይን ትቀይራለች ፤ ለባህር ዛጎል ለሰማይ ኮኮብ ለምድር አደይ ናት ፤ እንኳንስ ቁሜ ስሞት ከጎኔ ትብቀል የሚሏት ፤ ልጅማ ልጅ ናት ከአንድ እኔ በቀር ሌላ የሰው ዘር የማይመጥናት ። by Tewodros Kassa @getem @getem @paappii
Показати все...
59👍 12😁 5🔥 4👎 1
------- ቀን -------- ቀን ቀንን አርግዞ ቀን እየወለደ፣ አንድ ቀን ሌላን ቀን አልፎት እየሄደ፤ በቀናት መካከል ቀናት ተደራርቦ፣ የቀናት ክምችት የቀናት ርብራቦ፤ ቀናቶች ስንቆጥር ቀናት ስንመነዝር፣ ቀናት ስንዘራዝር ቀናቶች ስንገብር፤ ቀኖች እያሰብን ዝክር ስናዋጣ፣ ቀንን ሳንጠቀም ምፅአት ቀን መጣ። @getem @getem @paappii
Показати все...
53👍 11🔥 5👎 1😁 1
ሁሉም ይለወጣል በአበባ ይተካል ሸክሙም ቀንበሩም፤ ዘንበል ይሉልኛል ድንግዝግዝ ቀናቶች፡ ችክ እንዳሉ አይቀሩም። አምናለሁኝ እኮ፡ በኔ ላይ ይሆናል ፍፁም የማይሆነው! ፤ እኔን የጨነቀኝ፡ እንዴት አድርጌ ነው የማመሰግነው ?። By @mikiyas_feyisa @getem @getem @paappii
Показати все...
56🎉 1
አልጋዬ የምኞት በሀር ወዝሽ የፈሰሰበት ማጀቴ የፈኖስ ብርሀን ሳቅሽ የደመቀበት የጂጂ የመውደድ ዜማ ተቃቅፈን የደነስንበት ጎዳናው የተጓዝንበት #አንቺን_ያስታውሰኛል! ¹ የታክሲው ጥግ ላይ ወንበር ከፍተሽ የምተገቢው በር የቡና የዕጣን አውዱ የቤተስክያን አጸዱ የጧፏ ደቂቅ ብልጭታ ያስቀደስንበት ቦታ #አንቺን_ያስታውሰኛል! ² የትኩስ መቃብር ሽታ የተቆፈረ አፈር ድንኳን የተጣለበት ሰፈር የአበባ እቅፎች መቃብር ግርጌ የረገፉ የዕድር ጥሩንባዋች ሞት የሚለፍፉ #አንቺን_ያስታውሰኛል! #የአብስራ_ሳሙኤል @YabisraSamuel @getem @getem @getem
Показати все...
27😢 1
ቦግ.....እልም . . ጭላንጭል ብርሃን በጽልመት ተከባ፤ ቦግ...እልም ስትል ስትወጣ ስትገባ፤ አለች እንዳይሏት በርታ ትጠፋለች፤ ከሰመችም ሲሏት ከሩቅ ትታያለች፤ ቦግ.......እልም፤ ጭልም......ጭልምልም፤ ብልጭ.....ድርግም፤ የኔም ህይወት እንዲሁ...... አይሆንላት ተሸነፈች፤ አይሳካም ተሰበረች፤ አበቃላት ወድቃ ቀረች፤ ብለዉ ሲናገሩኝ.......... የሩቋ ወጋገን ጎልታ 'ምትታየኝ፤ በተነሳሁ ቁጥር ወደኔ 'ምትቀርበኝ፤ ጠፍታ የማትጠፋዉ ያቺ ብርሃን ነኝ። .............................. በዔደን ታደሰ @topazionnn @getem @getem
Показати все...
32👍 9🔥 5
#የገጣሚው_ማስታወሻ የገነባነው በጀንበር ዕድሜ ለምን ፈረሰ ይከርማል ያልነው ባዶ አስቀርቶን የት ገሰገሰ ስለምን በዛ ሀዘን መከራው!? ሰውስ ከስቃይ| ምንድን ነው ያፈራው? ብለን ብንጠይቅ ይሆናል! እንጂ መልስ አይገኝም እኔም ለመኖር ይነጋል የሚል ተስፋ የለኝም! ብቻ ግን አሁን ልቤም ጨለማ ስለለመደ ወደ'ሚያምነው ተራመደ "አቀበት ካሉኝ ገደል ነው ካሉኝ" ድልድይ ሰራው "ቀጠፍነው" ሲሉኝ በጥፍ አፈራው የዘመን አዘቅት ነፍሴን ሲዳፋት መገፋት ሳይሆን| መረሳት ከፋት! ¹ እናም አደራ  ወደጨለማው ስትማትሩ የጊዜ ቋጥኝ ምንም ቢከብደው ሲጋፋ የኖረ አንድ ገጣሚ እዚህ ነበረ!። #የአብስራ_ሳሙኤል @YabisraSamuel @getem @getem @getem
Показати все...
21🤩 2🔥 1
ቅዳጅ ሃሳቦች ለመድብል ያልጣፈው ቀርቶ ባጭር ጉዞ አያለሁ ወረቀት ቅዳጅ ሃሳብ ይዞ፡፡ ለመድፋት ሲኳትን ጭራሽ ሲፈርስበት ሃሳብ በምጥ ወልዶ በኖ ሲጠፋበት፤ ከግጥም ጥመኛው ከዛ ከአብሮ አደጌ እልፍ ቅዳጅ አለ ከማረፊያው ግርጌ፡፡ የሀሳብ ቁርጥራጭ የወረቀት ቅዳጅ ፍቅር የተራበ ያጣ ዘመድ ወዳጅ የሚጮህ ዝምታ በእንባ የታጀበ በጉንጭ ሸራ ላይ በዕድሜ የነተበ፤ እልፍ ሀሳብ ይዞ ጠጥቶ አዋራ ሰሚ በሌለበት በጩኸት ሚጣራ ከዛ ከሱሰኛው ከአብሮ አደጌ ጓዳ ጉም መሳይ ህልሙ በራሱ የተቀዳ አያለሁ ዘወትር ጭምድድ ወረቀቶች በጅምር የቀሩ ቅንጥብጣብ ትንቢቶች፡፡            By @Abuugida @getem @getem @getem
Показати все...
22👍 5
ትዝታ ወልዴ✍ @Tizita21 @getem
Показати все...
እንዳማታፍቅረኝ_በምን_አወክ_@Tizitawolde_poems1.mp32.40 MB
8🔥 3
‎#Akka_Qossaatti ‎ ‎ባካል ግብር ሳንገናኝ ‎ያይንን ውሃ ሳንረዳ ‎ቴሌግራም አስተዋውቆን ‎ሳንተያይ እንደባዳ ‎እንዳፍለኞች ሳናወራ ‎ሳታቀብጠኝ ሳላቀብጣት ‎ድብርት ቢጤ እየጫራ ‎ሳላገኛት እሷን ማጣት ‎ውለን አድረን መጨቃጨቅ ‎መተራረብ ለፍቅር ቃል ‎ኢመንት ነው መተያየት ‎መቀራረብ ብዙ ያዘልቃል ‎ ‎ከጎኔ እንዳለች ሰው ‎ሳይሰማኝ ሩቅ ያለሽ ‎አጠገቤ እንዳለሽ ‎ተቃርበሺው ይህን ቀልቤን ‎Waggaan tokko akka qossaatti darbe ‎ ‎ሳይታወቀኝ ሳይታወቅሽ ‎ቀናት ወርን እየተደገፈ ‎እንደ ቀልድ ‎እንደ ዋዛ አንድ አመት አለፈ። ‎ ‎ እንኳን አደረሰን🍾 ለኔና ላንቺ ብቻ😁 ‎ ‎ ዮኒ ‎      ኣታን @yonatoz @getem @getem @getem
Показати все...
35👍 5😁 3🎉 2
እናቴ 🥰 . . . ቢጨላልም ንጋት ቀኗ፤ ሲደካክም ወገብ ጎኗ፤ ማጀት ቤቷ ቢጎድልባት፤ ስቃይ ችግር ቢደቁሳት፤ በሀዘን ጊዜ በደስታዋ፤ አይከደን ሁሌም ጥርስዋ፤ ብትከፋ ምን ቢያደማት፤ ፈገግታ ነዉ የሚቀድማት። ...................................... በዔደን ታደሰ @topazionnn @getem @getem
Показати все...
89😢 8👍 2
ሰማሽ በመስኮቴ እውነት ገባው መሰል| በግ ይለፈልፋል የሰቆቃ ድምጹ| ለነፍሴ ይቀርባል መልሶም ይጠፋል ልቤም ከረሀቡ በላይ የበጉን እሪታ ማዳመጥ ቢያቅተው መሞረዱን አይተው! የዘንድሮ መውደድ| ከአምሮት ያላለፈ የዘንድሮ ፍቅር| ከሆድ ያልገዘፈ "እኔን" ብሎ አረደው እያክለፈለፈ!። #የአብስራ ሳሙኤል @YabisraSamuel @getem @getem @getem
Показати все...
27🔥 5😢 1
▵∘∘∘∘∘▴∘⊙⊙⊙⊙⊙⊙⊙⊙⊙ ስንወቃቀስ እድሜያችን ሸሸ ስንገፋፋ ቀናችን መሸ በመውደድ አጥቢያ በቦረቅንበት የመለያየት ሰርዶ በቀለ ፍቅራችን በቂም እየጠለሸ ¹ (በርግጥ...) ሄጃለው ካልሺኝ አትመለሺም እኔም እንዳምናው አልጠብቅሽም ማነው ባለበት ያልተቀየረ ? ከጊዜ ጋራ ውሎ እያደረ! መዋደድ ማለት ትናንት መምስል ፍጹም አይደለም! ዛሬ ላይ ሆነም ትናንትን ማለም ከህይወት ጋር ሰርክ እያደሩ ለጋ ህልሞቼ ደጅሽ ነበሩ ² (እናም...) ያመነው እውነት ከሚነጥለን በመለያየት ከምንከፋ ህይወት አንዴ ናት ጨበጥናት ስንል የምትጠፋ ተይው ክስሽን አናሸንፍም ድል አንረታ ከልቡ በላይ ዳኛ የለውም ወዶ የተረታ ³ (ደግሞም...) ካለኔ በዕንባ መኖርሽን አልፎ ሄጅ ንፋስ ነገረኝ አውቃለሁ እንደምትወጂኝ ጥላቻሽ እንደማይሽረኝ ከኔም ዘንድ መተይሽ ባየሽው የመኖር ምኞቴ ረግፏል ሄጃለሁ ካልሺኝ ጀመሮ ክንፎቼ ላባ ተገፏል አድባሩም አውዱም አስጠላኝ ወዳጆች ካልኳቸው ሸሸሁ ዋልሽበት ባሉኝ እየዋልኩ በራፍሽን ስከል አመሸሁ ⁴ (እናም...) በመሸ ቀን በሌት ጀንበር  ስንካስስ ባስረፈድነው  በሰከነ ህያው ፍቅር  ስንራራቅ ባበረድነው… የቀረንን ነጣላ እድሜ  እንኑራት በፈገግታ  አረፍ ብዬ ልጠብቅሽ  ከትናንቱ ከአምናው ቦታ! #የአብስራ_ሳሙኤል @YabisraSamuel @getem @getem @getem
Показати все...
40👍 3
‎ናተይ ኩሉ ‎ መዋደዳችንን እስካመነው ድረስ ‎ ነይ ኪዳን እንሰር በቃል እንታነፅ እቲ ዓውዲ ስድራቤት ዘይኮነስ አንዳችም ጥም ‎ ፍቅር ካለ ሀገር አለ በኢትዮጵያ ተስፋ አንቆርጥም ድሕሪ ሓደ ቦታ ኣብ ኣቦ ዕዳ ‎ በደማችን እርቅ ይወርዳል መዓልቲ ሞት ግንባር ሓዳ ‎ናተይ ከሉ ‎ እንዋደድ የለ....እንፋቀር የለ ‎ ልክ እንዳምናው እንደበስቲያ ትላንትና ዘይንጡፍ ኣይኮነን: ዝተፈላለየ ፍቕሪ አሉንና ‎ አንቺን ከኔ ቢያርቁሽም ቢነጥሉሽ ከብሌኔ ‎ ተስፋ አትቁረጪ ፍቅሬ ‎            ተስፋ አልቆርጥም እኔ ‎ ነገንም እንኑር ዛሬም አለንና      ‎ ሐደ እንሁንና ዮኒ     ኣታን  @yonatoz @getem @getem @getem
Показати все...
24
-------- ብልግና -------- በኛ ሀገር ቀመር በኛ ሀገር ፎርሙላ፣ ብልግና ተብሎ ሚሰጠዉ እዎቅና፤ ለእንደ እኛ አይነት ምስኪን ውግዝ ሲሆን ክልክል፣ ለባለ ገንዘቦች፣ ተከታይ ላላቸዉ ማራግ ነው ያለ እክል። @getem @getem @paappii
Показати все...
38😁 11🔥 1🤩 1
,          ( ደጅሽ ፀናሁ )      ለለመነ ሁሉ ለጠዬቀ ሁሉ ይሰጣል ስለሚል የክርስቶስ ቃሉ በርሽን አንኳኳሁ መጣሁ ልለምንሽ ዳግም ደጅሽ ፀናሁ ቆምኩና ከጎንሽ እኔማ ወዳጅሽን እኔንማ አፍቃሪሽ ጭንቅና ህመሜን ቀርበሽ ብታይልይ ድንገት እግዚሔር ፈቅዶ ልብሽ ቢራራልይ            ሱባኤ ገብቼ አርባ ቀን አርባ ሌት በስምሽ ላፀልይ       አወ እገባለሁ አወ እፀልያለሁ ብትመጭም ባትመጭም እውነት እልሻለሁ        በስምሽ ደግሼ ገና እዘክራለሁ ይልቅ አቡዬና ስላሴን በሩን ተሳልመሽ   ጧፍና ሻማሽን መዕባሽን ሰተሽ ዳግም ለእመብርሃን ጧፍን ተስለሽ ከፍቅራችን ፅዋ መተሽ ተቋደሽ By Habtamu dama @getem @getem @getem
Показати все...
37👍 7🔥 4😁 2
◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌ ያው እንደምታውቂው ሀገርሽ ሀገሬው እንቆቅልሽ ለምዶ ሀገር ልስጥሽ ይላል ለመልሱ ተሰዶ ውል አልባ ጥያቄ ምላሽ አልባ ምኞት እንደ አደይ ይፈልቃል መፈለጉን እንጂ ማግኘቱን ማን ያውቃል? ° ያው እንደምታውቂው አንቺም እንቆቅልሽ ለጉድ ትወጃለሽ እንቆቅልህ . . . ምን አውቅልሽ? ፩ (ጥያቄ) ከለምለም ሰርዶ ከጤዛው ተማሪ እረኛ ተኝቷል የአይኖቹን መክደን ጠብቆም ተኩላውም በጎቹን በልቷል የኔታም ከዋርካው ግርጌ ይሄንን እያጣመሩ እንዲህ የሚል ቅኔ አስተማሩ: ፪(መልሱ) በጉም! እረኛ አለኝ ብሎ ጠባቂን አመነ የተኩላ እራት ሆነ (እናም ተማሪ ሆይ) ጠባቂ አለኝ ብለህ አዳኝ አለኝ ብለህ ከእሳት አታመልጥም ይልቅስ ለትግሉ ሰይፍህን አዘጋጅ ክንድህን አፈርጥም! @getem @getem @getem
Показати все...
17👍 4