ግጥም ብቻ 📘
Kanalga Telegram’da o‘tish
✔በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን። ✔ @getem @serenity13 ✔ @wegoch @Words19 ✔ @seiloch @shiyach_bicha ✔ @zefenbicha @leul_mekonnen1
Ko'proq ko'rsatish2025 yil raqamlarda

65 764
Obunachilar
-324 soatlar
-397 kunlar
-30130 kunlar
Postlar arxiv
የኔ ሳቅ
.
.
ሁሉም ለየብቻዉ
እንደተለያየ
የኔ ሳቅ ለብቻው
ከኔ ጋራ ቆየ
አየሁት ሰማሁት
ሁሉን ተረዳሁት
ሳቄን ለማርከሻ
ቢቸግር ጠጣሁት
ቢቸግር በላሁት
እንደ ጎሽ ጠላ
እንደ 'ባር ማሽላ
ሳቄን ለማርከሻ
ከነገዉ መድረሻ
መረጥኩት ጠላሁት
ይስቃል እንዲሉኝ
ጥርሴን ተነቀስኩት
@topazionnn
@getem
@getem
❤ 37🔥 4😢 4👍 2😱 1
Repost from N/a
Photo unavailableShow in Telegram
ሰላም ወዳጆች ዛሬ 9:30 አራት ኪሎ በዋልያ ቡክስ አዳራሽ የወዳጄ የኪሩቤልን መፅሐፍ እናስመርቃለን።
የምትችሉ እዛው እንገናኝ።
ማስታወሻ የኔን ምስል እዚ ውስጥ ፈልጎ ላገኘ የመጀመሪያው ሰው መፅሐፉን እሸልማለሁ...😅🙏
❤ 18
ጥርሷ ሰዋሪ
ሳቋ ነዳፊ ፤
ከንፈሯ ገዳይ
ዐይኗ ገራፊ ፤
ፀጉሯ ሐመልማል
ልብሷ ደመና ፤
ገላዋ አበባ
ቃናዋ ናና ፤
ልክ እንደ ሰንደል
ልክ እንደ ብርጉድ ፤
የቀመሷት ለት የምታስብል ጉድ !
ከሰማይ በቀር
የምድር አፈር የማይመጥናት ፤
ከመለዓክ በቀር
በሳር በቅጠል የማይመስሏት ፤
ልጅማ ልጅ ናት !
ጨረቃ ኮኮብ የሚሰግዱላት
አበቦች ከዱር የሚያረግዱላት ፤
የሚገድሉላት
የሚሞቱላት
ከአንቺ ጋ አድሬ ሲነጋ ልሙት የሚዘፍኑላት ፤
ልጅማ ልጅ ናት !
ሲሻት በምድር
ሲሻት በሰማይ የምታበራ ፤
ነፍስ የምታስት ስትስቅ ስትኮራ ፤
እንኳን ለአዘቦት
ለክት ለዓመት ባል የሚሸሽጓት ፤
እንኳን በፀሐይ
ሌት በጨረቃ በሩቅ የሚያውቋት ፤
ልጅማ ልጅ ናት !
እንኳን ቁሞ ሃጅ
ሙቶ የተኛን ታሳብዳለች ፤
እንኳን የሰው ዘር
ባህሩን ወንዙን ታስረግዳለች ፤
ከፍቅር በቀር
ሌላ አይችላትም ፤
ከራሷ በቀር
የቱም አበባ አይመጥናትም ፤
የምድር ዕንቁ ናት
የምድር አበባ ፤
እንዲሁ ታይታ ዐይን የምትገባ ፤
እንዲሁ ታይታ ቀን ታፈካለች ፤
በዐይኖቿ ብቻ
ውኃን ወደ ወይን ትቀይራለች ፤
ለባህር ዛጎል
ለሰማይ ኮኮብ
ለምድር አደይ ናት ፤
እንኳንስ ቁሜ
ስሞት ከጎኔ ትብቀል የሚሏት ፤
ልጅማ ልጅ ናት
ከአንድ እኔ በቀር
ሌላ የሰው ዘር የማይመጥናት ።
by Tewodros Kassa
@getem
@getem
@paappii
❤ 59👍 12😁 5🔥 4👎 1
ሁሉም ይለወጣል
በአበባ ይተካል
ሸክሙም ቀንበሩም፤
ዘንበል ይሉልኛል
ድንግዝግዝ ቀናቶች፡
ችክ እንዳሉ አይቀሩም።
አምናለሁኝ እኮ፡
በኔ ላይ ይሆናል
ፍፁም የማይሆነው! ፤
እኔን የጨነቀኝ፡
እንዴት አድርጌ ነው
የማመሰግነው ?።
By @mikiyas_feyisa
@getem
@getem
@paappii
❤ 56🎉 1
አልጋዬ የምኞት በሀር ወዝሽ የፈሰሰበት
ማጀቴ የፈኖስ ብርሀን ሳቅሽ የደመቀበት
የጂጂ የመውደድ ዜማ
ተቃቅፈን የደነስንበት
ጎዳናው የተጓዝንበት
#አንቺን_ያስታውሰኛል!
¹
የታክሲው ጥግ ላይ ወንበር
ከፍተሽ የምተገቢው በር
የቡና የዕጣን አውዱ
የቤተስክያን አጸዱ
የጧፏ ደቂቅ ብልጭታ
ያስቀደስንበት ቦታ
#አንቺን_ያስታውሰኛል!
²
የትኩስ መቃብር ሽታ የተቆፈረ አፈር
ድንኳን የተጣለበት ሰፈር
የአበባ እቅፎች መቃብር ግርጌ የረገፉ
የዕድር ጥሩንባዋች ሞት የሚለፍፉ
#አንቺን_ያስታውሰኛል!
#የአብስራ_ሳሙኤል
@YabisraSamuel
@getem
@getem
@getem
❤ 27😢 1
ቦግ.....እልም
.
.
ጭላንጭል ብርሃን በጽልመት ተከባ፤
ቦግ...እልም ስትል ስትወጣ ስትገባ፤
አለች እንዳይሏት በርታ ትጠፋለች፤
ከሰመችም ሲሏት ከሩቅ ትታያለች፤
ቦግ.......እልም፤
ጭልም......ጭልምልም፤
ብልጭ.....ድርግም፤
የኔም ህይወት እንዲሁ......
አይሆንላት ተሸነፈች፤
አይሳካም ተሰበረች፤
አበቃላት ወድቃ ቀረች፤
ብለዉ ሲናገሩኝ..........
የሩቋ ወጋገን ጎልታ 'ምትታየኝ፤
በተነሳሁ ቁጥር ወደኔ 'ምትቀርበኝ፤
ጠፍታ የማትጠፋዉ ያቺ ብርሃን ነኝ።
..............................
በዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
@getem
❤ 32👍 9🔥 5
#የገጣሚው_ማስታወሻ
የገነባነው በጀንበር ዕድሜ ለምን ፈረሰ
ይከርማል ያልነው ባዶ አስቀርቶን የት ገሰገሰ
ስለምን በዛ ሀዘን መከራው!?
ሰውስ ከስቃይ| ምንድን ነው ያፈራው?
ብለን ብንጠይቅ
ይሆናል! እንጂ መልስ አይገኝም
እኔም ለመኖር
ይነጋል የሚል ተስፋ የለኝም!
ብቻ ግን አሁን
ልቤም ጨለማ ስለለመደ
ወደ'ሚያምነው ተራመደ
"አቀበት ካሉኝ ገደል ነው ካሉኝ"
ድልድይ ሰራው
"ቀጠፍነው" ሲሉኝ በጥፍ አፈራው
የዘመን አዘቅት ነፍሴን ሲዳፋት
መገፋት ሳይሆን| መረሳት ከፋት!
¹
እናም አደራ
ወደጨለማው ስትማትሩ
የጊዜ ቋጥኝ ምንም ቢከብደው
ሲጋፋ የኖረ
አንድ ገጣሚ እዚህ ነበረ!።
#የአብስራ_ሳሙኤል
@YabisraSamuel
@getem
@getem
@getem❤ 21🤩 2🔥 1
ቅዳጅ ሃሳቦች
ለመድብል ያልጣፈው ቀርቶ ባጭር ጉዞ
አያለሁ ወረቀት ቅዳጅ ሃሳብ ይዞ፡፡
ለመድፋት ሲኳትን ጭራሽ ሲፈርስበት
ሃሳብ በምጥ ወልዶ በኖ ሲጠፋበት፤
ከግጥም ጥመኛው ከዛ ከአብሮ አደጌ
እልፍ ቅዳጅ አለ ከማረፊያው ግርጌ፡፡
የሀሳብ ቁርጥራጭ የወረቀት ቅዳጅ
ፍቅር የተራበ ያጣ ዘመድ ወዳጅ
የሚጮህ ዝምታ በእንባ የታጀበ
በጉንጭ ሸራ ላይ በዕድሜ የነተበ፤
እልፍ ሀሳብ ይዞ ጠጥቶ አዋራ
ሰሚ በሌለበት በጩኸት ሚጣራ
ከዛ ከሱሰኛው ከአብሮ አደጌ ጓዳ
ጉም መሳይ ህልሙ በራሱ የተቀዳ
አያለሁ ዘወትር ጭምድድ ወረቀቶች
በጅምር የቀሩ ቅንጥብጣብ ትንቢቶች፡፡
By @Abuugida
@getem
@getem
@getem
❤ 22👍 5
#Akka_Qossaatti
ባካል ግብር ሳንገናኝ
ያይንን ውሃ ሳንረዳ
ቴሌግራም አስተዋውቆን
ሳንተያይ እንደባዳ
እንዳፍለኞች ሳናወራ
ሳታቀብጠኝ ሳላቀብጣት
ድብርት ቢጤ እየጫራ
ሳላገኛት እሷን ማጣት
ውለን አድረን መጨቃጨቅ
መተራረብ ለፍቅር ቃል
ኢመንት ነው መተያየት
መቀራረብ ብዙ ያዘልቃል
ከጎኔ እንዳለች ሰው
ሳይሰማኝ ሩቅ ያለሽ
አጠገቤ እንዳለሽ
ተቃርበሺው ይህን ቀልቤን
Waggaan tokko akka qossaatti darbe
ሳይታወቀኝ ሳይታወቅሽ
ቀናት ወርን እየተደገፈ
እንደ ቀልድ
እንደ ዋዛ አንድ አመት አለፈ።
እንኳን አደረሰን🍾 ለኔና ላንቺ ብቻ😁
ዮኒ
ኣታን @yonatoz
@getem
@getem
@getem
❤ 35👍 5😁 3🎉 2
እናቴ 🥰
.
.
.
ቢጨላልም ንጋት ቀኗ፤
ሲደካክም ወገብ ጎኗ፤
ማጀት ቤቷ ቢጎድልባት፤
ስቃይ ችግር ቢደቁሳት፤
በሀዘን ጊዜ በደስታዋ፤
አይከደን ሁሌም ጥርስዋ፤
ብትከፋ ምን ቢያደማት፤
ፈገግታ ነዉ የሚቀድማት።
......................................
በዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
@getem
❤ 89😢 8👍 2
ሰማሽ በመስኮቴ
እውነት ገባው መሰል| በግ ይለፈልፋል
የሰቆቃ ድምጹ| ለነፍሴ ይቀርባል
መልሶም ይጠፋል
ልቤም
ከረሀቡ በላይ
የበጉን እሪታ ማዳመጥ ቢያቅተው
መሞረዱን አይተው!
የዘንድሮ መውደድ| ከአምሮት ያላለፈ
የዘንድሮ ፍቅር| ከሆድ ያልገዘፈ
"እኔን" ብሎ አረደው እያክለፈለፈ!።
#የአብስራ ሳሙኤል
@YabisraSamuel
@getem
@getem
@getem
❤ 27🔥 5😢 1
▵∘∘∘∘∘▴∘⊙⊙⊙⊙⊙⊙⊙⊙⊙
ስንወቃቀስ እድሜያችን ሸሸ
ስንገፋፋ ቀናችን መሸ
በመውደድ አጥቢያ በቦረቅንበት
የመለያየት ሰርዶ በቀለ
ፍቅራችን በቂም እየጠለሸ
¹
(በርግጥ...)
ሄጃለው ካልሺኝ አትመለሺም
እኔም እንዳምናው አልጠብቅሽም
ማነው ባለበት ያልተቀየረ ?
ከጊዜ ጋራ ውሎ እያደረ!
መዋደድ ማለት
ትናንት መምስል ፍጹም አይደለም!
ዛሬ ላይ ሆነም ትናንትን ማለም
ከህይወት ጋር ሰርክ እያደሩ
ለጋ ህልሞቼ ደጅሽ ነበሩ
²
(እናም...)
ያመነው እውነት ከሚነጥለን
በመለያየት ከምንከፋ
ህይወት አንዴ ናት
ጨበጥናት ስንል የምትጠፋ
ተይው ክስሽን አናሸንፍም ድል አንረታ
ከልቡ በላይ ዳኛ የለውም ወዶ የተረታ
³
(ደግሞም...)
ካለኔ በዕንባ መኖርሽን
አልፎ ሄጅ ንፋስ ነገረኝ
አውቃለሁ እንደምትወጂኝ
ጥላቻሽ እንደማይሽረኝ
ከኔም ዘንድ መተይሽ ባየሽው
የመኖር ምኞቴ ረግፏል
ሄጃለሁ ካልሺኝ ጀመሮ
ክንፎቼ ላባ ተገፏል
አድባሩም አውዱም አስጠላኝ
ወዳጆች ካልኳቸው ሸሸሁ
ዋልሽበት ባሉኝ እየዋልኩ
በራፍሽን ስከል አመሸሁ
⁴
(እናም...)
በመሸ ቀን በሌት ጀንበር
ስንካስስ ባስረፈድነው
በሰከነ ህያው ፍቅር
ስንራራቅ ባበረድነው…
የቀረንን ነጣላ እድሜ
እንኑራት በፈገግታ
አረፍ ብዬ ልጠብቅሽ
ከትናንቱ ከአምናው ቦታ!
#የአብስራ_ሳሙኤል
@YabisraSamuel
@getem
@getem
@getem❤ 40👍 3
ናተይ ኩሉ
መዋደዳችንን እስካመነው ድረስ
ነይ ኪዳን እንሰር በቃል እንታነፅ
እቲ ዓውዲ ስድራቤት ዘይኮነስ አንዳችም ጥም
ፍቅር ካለ ሀገር አለ በኢትዮጵያ ተስፋ አንቆርጥም
ድሕሪ ሓደ ቦታ ኣብ ኣቦ ዕዳ
በደማችን እርቅ ይወርዳል መዓልቲ ሞት ግንባር ሓዳ
ናተይ ከሉ
እንዋደድ የለ....እንፋቀር የለ
ልክ እንዳምናው እንደበስቲያ ትላንትና
ዘይንጡፍ ኣይኮነን: ዝተፈላለየ ፍቕሪ አሉንና
አንቺን ከኔ ቢያርቁሽም ቢነጥሉሽ ከብሌኔ
ተስፋ አትቁረጪ ፍቅሬ
ተስፋ አልቆርጥም እኔ
ነገንም እንኑር ዛሬም አለንና
ሐደ እንሁንና
ዮኒ
ኣታን @yonatoz
@getem
@getem
@getem
❤ 24
, ( ደጅሽ ፀናሁ )
ለለመነ ሁሉ ለጠዬቀ ሁሉ
ይሰጣል ስለሚል የክርስቶስ ቃሉ
በርሽን አንኳኳሁ መጣሁ ልለምንሽ
ዳግም ደጅሽ ፀናሁ ቆምኩና ከጎንሽ
እኔማ ወዳጅሽን እኔንማ አፍቃሪሽ
ጭንቅና ህመሜን ቀርበሽ ብታይልይ
ድንገት እግዚሔር ፈቅዶ ልብሽ ቢራራልይ
ሱባኤ ገብቼ
አርባ ቀን አርባ ሌት በስምሽ ላፀልይ
አወ እገባለሁ አወ እፀልያለሁ
ብትመጭም ባትመጭም እውነት እልሻለሁ
በስምሽ ደግሼ ገና እዘክራለሁ
ይልቅ አቡዬና ስላሴን በሩን ተሳልመሽ
ጧፍና ሻማሽን መዕባሽን ሰተሽ
ዳግም ለእመብርሃን ጧፍን ተስለሽ
ከፍቅራችን ፅዋ መተሽ ተቋደሽ
By Habtamu dama
@getem
@getem
@getem
❤ 37👍 7🔥 4😁 2
◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌
ያው እንደምታውቂው
ሀገርሽ ሀገሬው እንቆቅልሽ ለምዶ
ሀገር ልስጥሽ ይላል ለመልሱ ተሰዶ
ውል አልባ ጥያቄ
ምላሽ አልባ ምኞት እንደ አደይ ይፈልቃል
መፈለጉን እንጂ ማግኘቱን ማን ያውቃል?
°
ያው እንደምታውቂው
አንቺም እንቆቅልሽ ለጉድ ትወጃለሽ
እንቆቅልህ . . . ምን አውቅልሽ?
፩ (ጥያቄ)
ከለምለም ሰርዶ ከጤዛው
ተማሪ እረኛ ተኝቷል
የአይኖቹን መክደን ጠብቆም
ተኩላውም በጎቹን በልቷል
የኔታም ከዋርካው ግርጌ
ይሄንን እያጣመሩ
እንዲህ የሚል ቅኔ አስተማሩ:
፪(መልሱ)
በጉም! እረኛ አለኝ ብሎ ጠባቂን አመነ
የተኩላ እራት ሆነ
(እናም ተማሪ ሆይ)
ጠባቂ አለኝ ብለህ
አዳኝ አለኝ ብለህ ከእሳት አታመልጥም
ይልቅስ ለትግሉ
ሰይፍህን አዘጋጅ ክንድህን አፈርጥም!
@getem
@getem
@getem❤ 17👍 4
