ru
Feedback
Tikvah-University

Tikvah-University

Открыть в Telegram
2025 год в цифрахsnowflakes fon
card fon
352 825
Подписчики
-4824 часа
+967 дней
+1 45930 день
Архив постов
Фото недоступноПоказать в Telegram
#FellowshipOpportunity በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሜዲካል ኮሌጅ የውስጥ ደዌ ህክምና ትምህርት ክፍል ብቁ አመልካቾችን ለ2018 ዓ.ም Adult Nephrology Fellowship ፕሮግራም አወዳድሮ መቀበል ይፈልጋል። ለዚህ ዓመት ሦስት (3) የፌሎውሺፕ ዕድሎች መኖራቸውን ኮሌጁ ገልጿል። የማመልከቻ ጊዜ የሚያበቃው፦ ታህሳስ 06/2018 ዓ.ም የቅበላ መስፈርት፦ ➫ ከታወቀ የህክምና ትምህርት ተቋም በህክምና ዲግሪ ያለው ያላት, ➫ በ Internal medicine የሬዚደንሲ ፕሮግራም ያጠናቀቀ/ች፣ ➫ Internist ሆኖ/ሆና ለሁለት ዓመት ያገለገለ/ች፣ ➫ የቅበላ ምልመላ ሒደት የሚያጠናቅቁ፣ ➫ በኢትዮጵያ የውስጥ ደዌ ህክምና ለመስጠት ተመዝግቦ ፈቃድ ያለው/ያላት፣ ➫ ጥሩ አዕምሯዊና አካላዊ ጤና ያላት/ያለው፣ ➫ አጭር የፍላጎት መግለጫ ማስገባት፣ የማመልከቻ አማራጮች፦ ፍላጎት ያላችሁ አመለልካቾች በ Internal ህክምና ትምህርት ክፍል በአካል በመቅረብ ወይም በኢሜል አድራሻዎች ayantu17@yahoo.com / lejahamza@yahoo.com ማመልከት ይችላሉ፡፡ አመልካቾች ሊያሟሏቸው የሚገቡ፦ ➫ የማመልከቻ ደብዳቤ ➫ የቅርብ ጊዜ CV ➫ የትምህርት ማስረጃዎች (ዲግሪ እና የውጤት መግለጫ) ➫ ሁለት የድጋፍ ደብዳቤዎች ➫ የስፖንሰርሺፕ ደብዳቤ (በመንግሥት ስፖንሰር ለምትደረጉ) ➫ የድኅረ ምረቃ መግቢያ ፈተና (GAT) ውጤት ለበለጠ መረጃ፦ ➫ Dr. Ayantu Tesfaye 0911890635 ➫ Dr. Leja Hamza 0917804057 የፅሑፍ እና የቃል ፈተና የሚሰጥባቸው ጊዜያት በቀጣይ ይገለጻል የተባለ ሲሆን፤ ትምህርት ታህሳስ 06/2018 ዓ.ም ይጀመራል ተብሏል፡፡ @tikvahuniversity
Показать все...
100😱 5👎 2🙏 2
Фото недоступноПоказать в Telegram
የድረ-ገጽ እና የሞባይል መተግበሪያ ማበልፀግ (Full-Stack Website and Mobile Application Development) ስልጠና ምዝገባ ላይ ነን! 👉 ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና 👉 ፕሮግራሚንግ ትምህርቶችን አካቶ ከ UI/UX ዲዛይን ጋር የሚሰጥ 👉 Front-end እና Back-end በአንድ ላይ እስከ Deployment ያካተተ 👉 በተግባር ድረ-ገጾች እና ሞባይል መተግበሪያዎችን እያበለፀጉ የሚሰለጥኑበት ☎️ 0906777799 / 0906777755 አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ Telegram: https://t.me/sagetraininginstitute TikTok: https://www.tiktok.com/@sage_training_institute LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
Показать все...
36🥰 4👏 2🙏 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
#AAU #FacultyPromotions አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ16 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል፡፡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሥራ አመራር ቦርድ የ16 ምሁራንን የሙሉ ፕሮፌሰርነት የማዕረግ ዕድገት አፅድቋል፦ 1. ፕሮፌሰር አለሙ ሀይሉ አንሹ - በእንግሊዝኛ ቋንቋ ማስተማር 2. ፕሮፌሰር ዳዊት መኮንን ምህረቴ - በኤዱኬሽን 3. ፕሮፌሰር ማቴዎስ እንሰርሙ ጃለታ - በሳፕላይ ቼይን አስተዳደር 4. ፕሮፌሰር ጌታቸው አሰፋ ወ/ማርያም - በህግ 5. ፕሮፌሰር በቀለ መኮንን ንጉሱ - በፋይን አርትስ 6. ፕሮፌሰር ወንድወሰን አሞኘ ደጉ - በተላላፊ በሽታ ጥናት 7. ፕሮፌሰር ሳምሶን ገ/መድህን ገ/ስላሴ - በኅብረተሰብ ጤና ኒዩትሪሽን 8. ፕሮፌሰር ቸርነት አመንቴ ገፌ - በኮንዴንስድ ማተር ፊዚክስ 9. ፕሮፌሰር እንግዳወርቅ አሰፋ ጥላሁን - በአካባቢ ጥናት 10. ፕሮፌሰር ገረመው ሳህሉ ገብሬ - በውሃ አቅርቦት ምህንድስና 11. ፕሮፌሰር ለሙ ጎላሳ ወዬሳ - በሜዲካል ፓራሲቶሎጂ 12. ፕሮፌሰር አለምሰገድ ቤልዳዶስ አለሆ - በአርኪዮሎጂ 13. ፕሮፌሰር መርዕድ ተሰማ ገ/መድህን - በአናሊቲክ ኬሚስትሪ 14. ፕሮፌሰር እስጢፋኖስ ኤሌ ያያ - በኦርጋኒክ ኬሚስትሪ 15. ፕሮፌሰር ሚስጥረ ዎልዴ ገብሬ - በክሊኒካል ላቦራቶሪ ሳይንስ 16. ፕሮፌሰር በላይነህ መስፍን አሊ - በሶሊድ ስቴት ፊዚክስ በዚህ ዙር የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ የተሰጣቸው ምሁራን በሙሉ ወንዶች ናቸው። @tikvahuniversity
Показать все...
241👏 54👎 38👍 12😱 6🙏 3
Фото недоступноПоказать в Telegram
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ መደበኛ የአማርኛ መዝገበ ቃላት እያዘጋጀ ነው፡፡ ዩኒቨርሲቲው “የአማርኛ ልሳነ ዋሕድ መዝገበ ቃላት ዝግጅት ጥናት ንድፍ“ በሚል የውይይት መርሐግብር በቅርቡ አካሒዷል፡፡ በዩኒቨርሲቲው የሚዘጋጀው መዝገበ ቃላት ዘመኑን የዋጀ፣ ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ጋር የተቀመረ እና ዲጂታልንም ታሳቢ ያደረገ እንደሚሆን ተገልጿል፡፡ የመጀመሪያው የአማርኛ መዝገበ ቃላት እ.አ.አ. በ1698 ዓ.ም የታተመ ሲሆን፤ የከሣቴ ብርሃን አማርኛ መዝገበ ቃላትን ጨምሮ በተለያዩ ጊዚያት የአማርኛ ቋንቋ መዝገበ ቃላት ታትመዋል፡፡ የሳይንስና ቴክኖሎጂ እንግሊዝኛ አማርኛ መዝገበ ቃላት በቅርቡ በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ለህትመት መብቃቱ ይታወሳል፡፡ @tikvahuniversity
Показать все...
228👍 68👎 27👏 13🥰 10🙏 7😢 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
ራያ ዩኒቨርሲቲ ሁለት የፈጠራ እና የምርምር ዲጂታላይዜሽን ሥራዎች አስመርቋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው በተቋሙ መምህራንና ተመራማሪዎች የበለጸጉ ሁለት የቴክኖሎጂ ሽግግር ስራዎችን ይፋ አድርጓል፡፡ ግእዝን በሞባይል መማር የሚያስችል 'ፍኖተ-ግእዝ' የተሰኘ የሞባይል መተግበሪያ እና የምርምር ፖርታል በዩኒቨርሲው ይፋ የተደረጉ የቴክኖሎጂ ሽግግር ስራዎች ናቸው፡፡ ፍኖተ-ግእዝ የሞባይል መተግበሪያ የእጅ ስልክን በመጠቀም መሰረታዊ የግእዝ ቋንቋ ክህሎቶችን ለማበልፀግ የሚያግዝ የሞባይል አፕሊኬሽን መሆኑ ተገልጿል። የምርምር ፖርታሉ የዩኒቨርሲቲውን የምርምር ውጤቶች ዲጅታል ቋት፣ የምርምር መረጃዎች አስተዳደር ስርዓት እንዲሁም የዩኒቨርሲቲውን የሳይንስና ልማት ጆርናል (RJSD) አንድ ላይ የሚያጠቃልል ነው ተብሏል፡፡ @tikvahuniversity
Показать все...
59👍 8👏 6👎 2🙏 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
የግራፊክ ዲዛይን፣ ቪዲዮ ኤዲቲንግ፣ ሞሽን ግራፊክ እና ዲጂታል ማርኬቲንግ ስልጠና ምዝገባ ላይ ነን! 👉 ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና 👉 Advanced Graphic + Video Editing + Motion Graphic + Digital Marketing በአንድ ላይ 👉 ከ50 በላይ ፕሮጀክቶች ያሉት ☎️ 0906777799 / 0906777755 አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ የበለጠ ይጠብቁ ... 💥 ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 💥 Telegram: https://t.me/sagetraininginstitute TikTok: https://www.tiktok.com/@sage_training_institute LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
Показать все...
33🥰 6
እንኳን ደስ አላችሁ! 🎉💵 ሰኞ ህዳር 22/2018 ዓ.ም 14ኛው ዙር ዕድለኞች ዕጣ አወጣጥ በቲክቶክ እና በፌስቡክ ገፃችን ላይ በቀጥታ ስናስተላልፍ በነበረው መሰረት ቀጣዩ የ1,000,000 ብር ዕድለኞች ከጎንደር እና ከሆሳዕና ሆነዋል። ማን ያውቃል ቀጣይ እርስዎ ሊሆኑ ይችላሉ! የበሽ ጥቅል እየገዛን እንንበሽበሽ! 🥳🎉🎉 ሌሎች የ100 ብር አሸናፊዎች #Besh100Winner በመጠቀም ኮሜንት ላይ ወይም story ላይ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያን ታግ በማድረግ ያሳውቁን። 📲 የM-PESA መተግበሪያን አሁኑኑ ያውርዱ፦ https://onelink.to/ewsb22 የቴሌግራም ቦታችን 👉🏽 https://t.me/official_safaricomet_bot ወደ *777*0# ይደውሉ ወይም በM-PESA የበሽ ጥቅል ይግዙ! #SafaricomEthiopia #MPESASafaricom #furtheraheadtogether #besh
Показать все...
40👎 2
Фото недоступноПоказать в Telegram
#AdigratUniversity በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርት ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ታህሳስ 06 እና 07/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ ትምህርት ታህሳስ 08/2018 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል። ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ አራት መጠኑ 3x4 የሆነ የቅርብ ጊዜ ፎቶግራፍ፣ ➫ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣ ➫ ብሔራዊ መታወቂያ (Fayda)፣ ➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡ @tikvahuniversity
Показать все...
123👍 27👎 11😱 6🙏 6😢 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
ትምህርት ሚኒስቴር ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በላከው ሰርኩላር የስራ ዕድል ፈጠራ ልማት (CEED) ማዕከላት ያሉበትን ደረጃ ሪፖርት እነዲልኩ ጠይቋል፡፡ የመንግሥት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ2018 ዓ.ም የስራ ዕድል ፈጠራ ልማት (CEED) ማዕከላትን በማደራጀት ለተማሪዎች እና ሠራተኞች ተከታታይነት እና ተገቢነት ያላቸውን የማማከርና የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች እንዲሰጡ እንደሚጠበቅ ሚኒስቴሩ አስታውሷል፡፡ ስለሆነም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ባቋቋሙት ማዕከላት ስር እስካሁን የተሠሩ ስራዎችን ለመገምገም እንዲቻል፤ የተላከላችሁን የጉግል አድራሻ በመጠቀም የምታገኙትን መጠይቅ በመሙላት እስከ ህዳር 30/2018 ዓ.ም ድረስ በኢሜይል አድራሻ tamiratk95@gmail.com ሪፖርት እንድትልኩ ተብሏል፡፡ @tikvahuniversity
Показать все...
94👏 15👍 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
ሙሉ የሒሳብ መዝገብ አያያዝ (Modern Accountancy) ስልጠና ምዝገባ ላይ ነን! 👉 ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና 👉 መሠረታዊ የአካውንቲንግ እና ኦዲት አሰራር፣ ሙሉ የአካውንቲንግ ሒሳብ አሰራር በፒስቺሪ ተደግፎ እና የግብር አያያዝ ትምህርቶችን አካቶ የሚሰጥ 👉 ስልጠናው ከፒስቺሪ በተጨማሪ በ Excel፣ Word እና ተግባራዊ ዶክመንቶች ታግዞ የሚሰጥ ነው። የበለጠ ይጠብቁ ... 💥 ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 💥 ☎️ 0906777799 / 0906777755 አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ Telegram: https://t.me/sagetraininginstitute TikTok: https://www.tiktok.com/@sage_training_institute LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
Показать все...
47👍 3🥰 2🙏 2👏 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
#MaddaWalabuUniversity በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርት መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ታህሳስ 06 እና 07/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ ትምህርት ታህሳስ 08/2018 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል። ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ ከ8-12ኛ ክፍል ያሉ የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣ ➫ መጠኑ 3x4 የሆነ ፎቶግራፍ፣ ➫ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ፣ ➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ እና የትራስ ልብስ፡፡ @tikvahuniversity
Показать все...
137👎 21👍 20🥰 10😢 10🙏 7👏 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
#WallagaUniversity በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ለሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርት የተመደባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ታህሳስ 02 እና 03/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል። ትምህርት የሚጀምረው ታህሳስ 06/2018 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል፡፡ የምዝገባ ቦታ፡- ➫ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ጊምቢ ካምፓስ፣ ➫ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ወንዶች ከፊደል A-D እና ሴቶች ከፊደል A-H ሻምቡ ካምፓስ እንዲሁም የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ወንዶች ከፊደል E-Z እና ሴቶች ከፊደል I-Z ዋናው ግቢ ነቀምቴ ከተማ ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣ ➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ አራት መጠኑ 3x4 የሆነ ፎቶግራፍ፣ ➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ። @tikvahuniversity
Показать все...
91👎 5🥰 4👍 2😢 2👏 1🙏 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
በ2018 ዓ.ም ለሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርት ከሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ወደ ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ዝውውር ያመለከታችሁ ተማሪዎች በሙሉ መሀል ሜዳ ካምፓስ የተመደባችሁ መሆኑን ተቋሙ ገልጿል፡፡ በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርት ለመከታተል የተመደባችሁ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ታህሳስ 02 እና 03/2018 ዓ.ም መሆኑ ይታወቃል፡፡ @tikvahuniversity
Показать все...
😢 48 30👍 16👎 8🙏 7
#ጥቆማ ቶሞካ ቡና ኃ. የተ. የግል ማህበር ከኢፌዲሪ ቴከኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ጋር በጋራ በመሆን ቶሞካ ኮፊ አካዳሚን በኢንስቲትዩቱ ቅጥርግቢ ውስጥ ከፍቷል፡፡ አካዳሚው መስፈርቶችን የምታሟሉ አመልካቾችን አወዳድሮ ከታች በተዘረዘሩት የስልጠና ዘርፎች አጫጭር ስልጠናዎችን ከትምህርት ከፍያ #ነጻ በሆነ ሁኔታ ለመስጠት ይፈልጋል፡፡ የስልጠና ዘርፎች፦ ➫ ሪቴይል ሱፐርቫይዘር ➫ ሪቴይል ካሸር ➫ ሪቴይል ባሬስታ ተፈላጊ ሰልጣኞች ብዛት፦ ለእያንዳንዱ ዘርፍ 20 ሰልጣኞች የስልጠና ጊዜ ቆይታ፦ 60፣ 40 እና 20 ቀናት በምስሉ ላይ የተጠቀሱትን መመዘኛዎች የምታሟሉ አመልካቾች የተጠቀሱትን የትምህርት ማስረጃችሁን ዋናውንና ኮፒውን በመያዝ እስከ ህዳር 26/2018 ዓ.ም ላምበረት መናኸሪያ ጎን ባለው የፌዴራል የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ቅጥር ግቢ ውስጥ በሚገኘው የቶሞካ ኮፊ አካዳሚ በአካል በመገኘት መመዝገብ ትችላላችሁ ተብሏል፡፡ ስልጠናው ያለምንም ክፍያ የሚሰጥ ሲሆን፤ በስልጠና ጊዜ የምሳ አበል ይከፍላል፡፡ ከስልጠና በኋላ ለሚቀጠሩ ሙያተኞች ደመወዝ በድርጅቱ ስኬል መሰረት ይሆናል፡፡ ሰልጣኞች ስልጠናውን ካጠናቀቁ በኋላ ለተወሰነ ጊዜ ድርጅቱን ማገልገል ይጠበቅባቸዋል፡፡ ለተጨማሪ መረጃ፦ 0116684268 @tikvahuniversity
Показать все...
62👏 6
የፌደራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዮት የፋሽን አካዳሚና ላብራቶሪ ሥራ አስጀምሯል፡፡ አካዳሚው በፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ኢንስቲትዩት እና በማፊ ፋሽን ዲዛይን ትብብር (PPP) የተቋቋመ መሆኑ ተገልጿል፡፡ አካዳሚው በፋሽን ኢንዱስትሪው የወጣቶችን ተጠቃሚነት ለማሳደግ መደበኛ እና አጫጭር ስልጠና ለወጣቶች እንደሚሰጥ ተጠቁሟል፡፡ @tikvahuniversity
Показать все...
31😢 2🥰 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
የጋዜጠኝነት ስልጠና ምዝገባ ላይ ነን! በስልጠናው የተካተቱ፦ 👉 መሠረታዊ የጋዜጠኝነት መርሆች፣ የሚዲያ አይነቶች እና የጋዜጠኝነት ዓይነቶች 👉 የዜና አሰራር እና የቃለመጠይቅ አደራረግ 👉 የመዝናኛ ፕሮግራም ጋዜጠኝነት፣ የፕሮግራም ዝግጅት፣ የማስታወቂያ አሰራር እና የዶክመንተሪ ዝግጅት 👉 የሞባይል ጋዜጠኝነት እና የዩቲዩብ ጋዜጠኝነት ☎️ 0906777799 / 0906777755 አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ Telegram: https://t.me/sagetraininginstitute TikTok: https://www.tiktok.com/@sage_training_institute LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
Показать все...
43👏 4👎 2🥰 2🙏 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
#ጥቆማ በቡራዩ የሚገኘው የተሰጥኦና ተወህቦ (Gift & Talent) ማበልፀጊያ ትምህርት ቤት በ2018 ዓ.ም የላቀና የተለየ ተሰጥኦ ያላቸውን ግለሰቦች በመለየት መዝግቦ እውቅና በመስጠት በተለያዩ ዘርፎች ስልጠኛ ይሰጣል፡፡ የስልጠና ዘርፎች፦ ➫ ዲጂታልና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ➫ ሮቦቲክስ እና ኤሌክትሮኒክስ ➫ አስትሮኖሚ እና የጠፈር ቴክኖሎጂ ➫ ባዮ-ቴክኖሎጂ ➫ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ሂሳብ ትምህርት ቤቱ ስልጠና ለመስጠትና የተለያዩ ድጋፎችን ለማድረግ በርካታ ፕሮግራሞችን ቀርጾ ሳይንሳዊ የተሰጥኦ ምዘናዎችን በመስጠት ላይ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡ ከላይ በተዘረዘሩት ዘርፎች የተመዘገባችሁ ባለተሰጥኦዎች ቅዳሜ ህዳር 27 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ የሳይኮሜትሪ ምዘና ስለሚሰጥ በዕለቱ ተገኝታችሁ ምዘናውን እንድትወስዱ ትምህርት ቤቱ አሳስቧል፡፡ @tikvahuniversity
Показать все...
125👍 8🙏 7👎 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
#WolkiteUniversity በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርት ወደ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ታህሳስ 06 እና 07/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣ ➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ ሁለት መጠኑ 3x4 የሆነ ፎቶግራፍ፣ ➫ ብሔራዊ የፋይዳ መታወቂያ (National ID)፣ ➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ እና የትራስ ልብስ፡፡ @tikvahuniversity
Показать все...
173👍 101👎 38🙏 11👏 7🥰 4
Фото недоступноПоказать в Telegram
የቴክኒካል ስራዎች (Technical Skills) ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን። ስልጠናዎቹ 👉 Building Electrical Installation, CCTV Camera Installation and Security Solutions 👉 Computer Maintenance, Networking, Office Machine Maintenance and Home Appliance 👉 Mobile Maintenance   👉 Industrial Machine Installation and Maintenance ☎️   0906777799 / 0906777755 አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ Telegram: https://t.me/sagetraininginstitute TikTok: https://www.tiktok.com/@sage_training_institute LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
Показать все...
43🙏 7👍 3👎 2
Фото недоступноПоказать в Telegram
#AksumUniversity በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርት ወደ አክሱም ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ታህሳስ 06 እና 07/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ በተጠቀሱት ቀናት አክሱም ከተማ በሚገኘው የዩኒቨርሲቲው ዋናው ግቢ በአካል በመገኘት ሪፖርት እንድታደርጉ ተብሏል። ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣ ➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣ ➫ አራት 3x4 የሆነ የቅርብ ፎቶግራፍ፣ ➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ እና የትራስ ልብስ፡፡ @tikvahuniversity
Показать все...
161👎 35👍 11🙏 2👏 1