uk
Feedback
TIKVAH-MAGAZINE

TIKVAH-MAGAZINE

Відкрити в Telegram

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። #ኢትዮጵያ ያግኙን +251913134524

Показати більше
2025 рік у цифрахsnowflakes fon
card fon
194 392
Підписники
-5024 години
-1767 днів
-81830 день
Архів дописів
Фото недоступнеДивитись в Telegram
‼️ ይፍጠኑ ‼️ በመሀል ሳር ቤት ቫቲካን ኢምባሲ አካባቢ ‼️ # ቴምር ሪልስቴት ከ8 በላይ ሳይቶችን ጥንቅቅ አድርገን አስረክበን አሁን ደግሞ ሳርቤት ቫቲካን ኢምባሲ አካባቢ ለሽያጭ ያወጣናቸው አፓርትመንቶች   ➤ 100% ለሚከፍሉ 35% ቅናሽ 👉 ባለ 2 መኝታ = 81ካሬ = 6ሚሊዮን 👉 ባለ 2 መኝታ = 106ካሬ = 7.9ሚሊዮን 👉 ባለ 3 መኝታ = 139ካሬ = 10.3ሚሊዮን 👉 ባለ 3 መኝታ = 152ካሬ = 11.3ሚሊዮን ➤ በ20% ቅድመ ክፍያ (በግንባታ ሂደት ለሚከፍሉ) 👉 81ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 9.3ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (1.8ሚሊዮን) 👉 106ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 12.1ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (2.4ሚሊዮን) 👉 139ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 15.9ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (3.1ሚሊዮን) ⩩ ቀሪውን 80%፤ በግንባታ ሂደት፤ ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት። ⩩ 30% እና ከዚያ በላይ ለሚከፍሉ፤ ከከፈሉት ላይ ከ15 -25% ቅናሽ አዘጋጅተናል። ለበለጠ መረጃ ይደውሉልን ☎️+251980782850
Показати все...
16👍 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
በናይጄሪያ ከ300 በላይ ተማሪዎች በታጣቁ ሰዎች ታግተው ተወሰዱ። በናይጀሪያ ኒጀር ግዛት ከሚገኝ የሁለተኛ ደረጃ የካቶሊክ ትምህርት ቤት 303 ተማሪዎችና 12 መምህራን በታጣቂዎች መወሰዳቸው ተዘግቧል። ባለፈው ሳምንት በናይጄሪያ 25 ተማሪዎች ተወስደው አንዷ ማምለጧና የቀሩት 24ቱ ያሉበት እንደማይታወቅ ተነግሯል። ለተማሪዎቹ መወሰድ ኃላፊነት የወሰደ አካል የሌለ ሲሆን የኒጀር ግዛት ያለ መንግስት ፈቃድ ትምህርት ቤቱ ዳግም በመከፈቱ ተማሪዎችና መምህራን መቅረት ለሚችል አደጋ ተጋርጠዋል ብሏል። በናይጄሪያ እየተስፋፋ የመጣውን የተማሪዎች ታግቶ መወሰድ ተከትሎም የሃገሪቱ ፕሬዚዳንት ቦላ ቲኑቡ በቡድን 20 አባል ሃገራት ስብሰባ ለመካፈል ወደ ደቡብ አፍሪካ ሊያደርጉት የነበረውን ጉዞ ሰርዘዋል። ዘገባው የአልጄዚራ ነው። @TikvahethMagazine
Показати все...
😢 44 24🤣 2👎 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
የሶማሊያ ካቢኔ የሴት ልጅ ግርዛትን የሚከለክል የህግ ማዕቀፍ አፅድቋል። የሶማሊያ ካቢኔ የሴት ልጅ ግርዛትን የሚከለክል ህግ ሲያፀድቅ ለሶማሊ ሴቶች ትልቅ ድል ነው ተብሏል። የሴት ልጅ ግርዛት በሶማሊያ ባህል ውስጥ ለረጅም ዘመናት የቆየ ጎጂ ባህል ሲሆን በካቢኔው የፀደቀው ማዕቀፍ ድርጊቱን ከመከልከል በተጨማሪ በወንጀል የሚያስጠይቅ አድርጎታል። እንደ ተመድ የህዝብ ፈንድ መረጃ ከሆነ በሶማሊያ ከሚገኙ ዕድሜያቸው ከ15-49 ዓመት ከሆኑ ሴቶች መካከል 98 በመቶዎቹ የሴት ልጅ ግርዛት የተፈፀመባቸው ናቸው። በአለም አቀፍ ደረጃ 230 ሚሊየን ሴቶች ለዚህ ጎጂ ተግባር የተጋለጡ ቢሆንም አሁንም ባለው የአረዳድ ችግር የተነሳ ድርጊቱ በአንዳንድ ቦታዎች መፈፀሙን ቀጥሏል። ዘገባው የHORN OBSERVER ነው። @TikvahethMagazine
Показати все...
54👏 23👍 5🤣 3🤔 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
የጃኮብ ዙማ ልጅ ለሩሲያ ጦርነት ከሁለት ሃገራት ወጣቶችን ትመለምላለች ተባለ። የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ ሴት ልጅ ዱዱዚሌ ዙማ ሩሲያ ከዩክሬን ጋር በምታደርገው ጦርነት ለሩሲያ ጦር ከደቡብ አፍሪካና ቦትስዋና ወጣት ወንዶችን ስትመለምል ነበር ተብሏል። የቀድሞ ፕሬዚዳንት ልጅ ለአባቷ የፖለቲካ ፓርቲ የጥበቃ ስልጠና ሊወስዱ ነው በሚል ስም 20 ወጣት ወንዶች ወደ ሩሲያ እንደላከች ሲገለፅ የወጣቶቹ ቤተሰቦችም ወጣቶቹ በሩሲያ ቋንቋ የተፃፈ ወታደራዊ ኮንትራት እንዲፈርሙ ከተደረገ በኋላ ወደ ጦር ግንባር እንደተላኩ ተናግረዋል። አንዳንዶቹ ወደ ሩሲያ ያቀኑት ወጣቶች ከባለፈው ነሐሴ ወር ጀምሮ ከቤተሰባቸው ጋር ያላቸው ግንኙነት መቆሙም ተገልጿል። ዩክሬን ባለፉት ሳምንታት ከ1400 የሚልቁ አፍሪካውያን ወጣቶች ለሩሲያ እየተዋጉ እንደሆነ ማስታወቋ የሚታወስ ሲሆን ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳም የደቡብ አፍሪካ ዜጎች እንዴት እንደተመለመሉ ምርመራ እንዲደረግ ማዘዛቸው ይታወሳል። መረጃው የDW ነው። @TikvahethMagazine
Показати все...
63😢 15💔 9👏 3🤣 3
Фото недоступнеДивитись в Telegram
የኬንያ መንግስት በባለፈው ተቃውሞ ወቅት ገንዘብ ከፍሎ ወጣቶችን ያስፈራራ ነበር ተባለ። የሰብዓዊ መብት ተቆራቋሪው አምነስቲ ኢንተርናሽናል በኬንያ በነበረው ተቃውሞ ወቅት መንግሰት ለተለያዩ ቡድኖች እየከፈለ ወጣቶችን ያስፈራራ እንደነበርና ሃሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩ ቡድኖችን አሰማርቶ እንደነበር አስታውቋል። በተቃውሞ ወቅትም ለማስፈራራት በሰው ሰራሽ አስተውሎት የተፈጠሩ ወሲባዊ ፎቶዎች ጥቅም ላይ ውለዋል ተብሏል። አንዳንድ ተቃዋሚዎች የመግደል ዛቻ እንደደረሰባቸውና የልጆቻቸው ስም ተልኮ ሲያስፈራሯቸው እንደነበር ገልፀው የልጆቻቸውን ትምህርተ ቤት ለመቀየር እንደተገደዱ ለአምነስቲ ተናግረዋል። በአምነስቲ ሪፖርትም የሚያስፈራሩት ቡድን አባላት የመንግስትን ሃሳብ ለማሰራጨትና በማህበራዊ ትስስር ገፆች በተለይ በኤክስ ተቃውሞውን የተመለከቱ ልጥፎችን ለማውረድ በቀን ከ25,000-50,000 የኬንያ ሽልንግ ይከፈላቸው እንደነበር ተገልጧል። የታክስ ጭማሪን አስታኮ በተፈጠረው ተቃውሞም ከ100 በላይ ሰዎች መገደላቸው ይታወሳል። ዘገባው ከቢቢሲ የተወሰደ ነው። @TikvahethMagazine
Показати все...
32😢 11🤣 2
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ሶማሊያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጃለች። በሶማሊያ የድርቅ ሁኔታው እየተባባሰ በመምጣቱና ለረሃብ የተጋለጡ ሰዎች ቁጥር በመጨመሩ ብሔራዊ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጇ ተነግሯል። ሶማሊያ ተቋማቷ፣ የሰብዓዊ ተቋማትና አለም አቀፍ አጋሮች የምግብ አቅርቦትን በማሻሻል፣ የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትን በማሻሻል እና ለዘለቄታው የአየር ንብረት ተፅዕኖን ለመከላከል አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስዱ ጠይቃለች። ከፊል ራስ ገዟ ፑንትላንድም 1 ሚሊየን ሰዎች በድርቁ ሊጠቁ እንደሚችል ገልፃ ማስጠንቀቂያ ሰጥታለች። ከባለፈው ጥቅምት ወር ጀምሮ በሶማሊያ የሚገኙ ከ4 ሚሊየን በላይ ሰዎች ለምግብ እጥረት ሲጋለጡ 2 ሚሊየን ያህሉ ህፃናት ናቸው። በሶማሊያ የድንበር አካባቢዎች ውሃና ግጦሽ በመጥፋቱም ሰዎች ወደ ኢትዮጵያ እና ኬንያ ድንበር አካባቢ ወጣ ገባ እያሉ እየኖሩ እንደሆነ ተሰምቷል። ኢጋድ ከቀናት በፊት በሶማሊያ፣ ኢትዮጵያ እና ኬንያ ያለው ድርቅ እየተባባሰ መምጣቱን ገልፆ ማስጠንቀቂያ እንደሰጠ ይታወሳል። ዘገባው የኒው አረብ ነው። @TikvahethMagazine
Показати все...
23😢 17🙏 3
Фото недоступнеДивитись в Telegram
🌟ብልሕ ነገዴ ገበያው በደራበት ሱቁን ይከፍታል!!! 🌟አያት ግራንድ ሞል ✨ 3000 የንግድ ሱቆች ✨በካሬ ከ126,500 ብር ጀምሮ ✨ከ 30 ካሬ እስከ 200 ካሬ አማራጮች ያለው ✨4 ክፍለ ከተሞችን አዋስኖ ሴሚሲ ሚካኤል ላይ ይገኛል 🌟 90% የደረሰ ሳይታችን በ 20% ቅድመ ክፍያ 🌟መሀል ከተማ ካዛንቺስ በካሬ 89,815 ብር በ 15% ቅድመ ክፍያ ዛሬውኑ የግልዎ ያርጉ!!! 💥ለበለጠ መረጃ በ 251977630693 በቀጥታ @ayat121921 በቴሌግራም በዋትሳፕ ይደውሉ
Показати все...
18🤝 2🤔 1🤬 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
"ከዓለም የወታደራዊ በጀት ከ1% በታች በሆነ በጀት ረሃብን በ2030 ማጥፋት ይቻላል" - የዓለም ምግብ ፕሮግራም የተመድ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ረሃብን በ2030 ለማጥፋት 93 ቢሊየን ዶላር በዓመት እንደሚያስፈልግና ይህም ባለፉት አስር ዓመታት ለወታደራዊ በጀት ወጪ ከተደረገው 21.9 ትሪሊየን ዶላር አንፃር  ከ1% በታች እንደሆነ ገልጿል። በተጨማሪ የዓለም ምግብ ፕሮግራም በ2026 በአለም አቀፍ ደረጃ 318 ሚሊየን ሰዎች ለረሃብ እንደሚጋለጡ ገልፆ፥ ይህም ከ2019 አንፃር በእጥፍ የጨመረ እንደሚሆን አስታውቋል። ባለፈው ዓመት 295 ሚሊየን ሰዎች ለከፋ ረሃብ የተጋለጡ ሲሆን ከቀደመው አመት ተጨማሪ 14 ሚሊየን ሰዎች መራባቸው ተገልጿል። የተመድ ምክትል ጸሐፊ አሚና መሐመድ ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች ምግብ እንደ የጦር መሳሪያነት እያገለገለ መሆኑንም ተናግረዋል። ምከትል ጸሐፊዋ ሀገራት ረሃብን ከማጥፋት ይልቅ ገንዘብ እያወጡ ያሉት ለወታደራዊ በጀት መሆኑን በመጥፎነት አንስተዋል። በ2026 የዓለም ምግብ ፕሮግራም 13 ቢሊየን ዶላር በጀት በመያዝ 110 ሚሊየን ሰዎችን ለመደገፍ እንዳቀደ ተገልጿል። ዘገባው ከአፍሪካ ኒውስ የተገኘ ነው። @TikvahethMagazine
Показати все...
95😢 47🕊 14🤔 6🤷‍♂ 5🙏 4👍 2🤯 2
Фото недоступнеДивитись в Telegram
"ከዓለም የወታደራዊ በጀት ከ1% በታች በሆነ በጀት ረሃብን በ2030 ማጥፋት ይቻላል" - የአለም ምግብ ፕሮግራም የተመድ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ረሃብን በ2030 ለማጥፋት 93 ቢሊየን ዶላር በዓመት እንደሚያስፈልግና ይህም ባለፉት አስር ዓመታት ለወታደራዊ በጀት ወጪ ከተደረገው 21.9 ትሪሊየን ዶላር አንፃር  ከ1% በታች እንደሆነ ገልጿል። በተጨማሪ የዓለም ምግብ ፕሮግራም በ2026 በአለም አቀፍ ደረጃ 318 ሚሊየን ሰዎች ለረሃብ እንደሚጋለጡ ገልፆ፥ ይህም ከ2019 አንፃር በእጥፍ የጨመረ እንደሚሆን አስታውቋል። ባለፈው ዓመት 295 ሚሊየን ሰዎች ለከፋ ረሃብ የተጋለጡ ሲሆን ከቀደመው አመት ተጨማሪ 14 ሚሊየን ሰዎች መራባቸው ተገልጿል። የተመድ ምክትል ጸሐፊ አሚና መሐመድ ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች ምግብ እንደ የጦር መሳሪያነት እያገለገለ መሆኑንም ተናግረዋል። ምከትል ጸሐፊዋ ሀገራት ረሃብን ከማጥፋት ይልቅ ገንዘብ እያወጡ ያሉት ለወታደራዊ በጀት መሆኑን በመጥፎነት አንስተዋል። በ2026 የዓለም ምግብ ፕሮግራም 13 ቢሊየን ዶላር በጀት በመያዝ 110 ሚሊየን ሰዎችን ለመደገፍ እንዳቀደ ተገልጿል። ዘገባው ከአፍሪካ ኒውስ የተገኘ ነው። @TikvahethMagazine
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
በድርቅ በተፈተነችው ኢራን የዘነበው ዝናብ የጎርፍ አደጋ አስከተለ። በምዕራብ ኢራን አካባቢዎች በጣለው ከባድ ዝናብ የጎርፍ አደጋ ሲከሰት የሃገሪቱ የሜትሮዎሎጂ ተቋም ኢራን ካሏት 31 ግዛቶች በ18ቱ ዝናብ ይዘንባል ብሎ እንደሚጠብቅና በስድስቱ ግዛቶች ጎርፍ እንደሚኖር አስጠንቅቋል። ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ኢራን የክላውድ ሲዲንግን በመጠቀም ዝናብ ለማዝነብ የሞከረች ሲሆን የጎርፍ አደጋው ተከሰተ የተባለውም የክላውድ ሲዲንጉ በተሞከረባቸው አካባቢዎች ስለመሆኑ ተዘግቧል። የኢራን የሜትሮዎሎጂ ተቋም መሪ የክላውድ ሲዲንግ ወጪው  ከፍተኛ መሆኑን አንስተው ከሱ የሚገኘው ዝናብም ኢራን ችግሯን ለመፍታት ከሚያስፈልጋት አንፃር ኢምንት መሆኑን ተናግረዋል። ዘገባው የሮይተርስ ነው። @TikvahethMagazine
Показати все...
68🤣 20😢 10👎 2
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ቻት ቦት (Chat Bot) ምንድን ነው ? ቴክኖሎጂን በመጠቀም ሰዎች ከሰዎች ጋር መልዕክት መለዋወጣቸው የተለመደ ነገር ነው። ከተወሰኑ ዓመታት በፊት በመጡ ለውጦች ደግሞ ሰዎች ከማሽን ጋር መልዕክት እንዲለዋወጡ አስችሏል። ይህም ድርጅቶች ተጠቃሚዎቻቸው በተደጋጋሚ ለሚጠይቋቸው ጥያቄዎች መልዕክት እንዲመልሱ ለማስቻል ቻት ቦቶችን ተጠቅመዋል። ይህም ለተወሰኑ ጥያቄዎች ወይም መርጠን ለምንልካቸው ጥያቄዎች በአንድ ጊዜ ለብዙ ሰዎች የተዘጋጀ ምላሽ መስጠት ያስችላል። አሁን ላይ እነዚህ ቻት ቦቶች  Generative AI የያዙ ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ ለሚጠየቁት ጥያቄዎች በሰለጠኑበት መረጃ ላይ ተመስርተው ምላሽ መስጠት አስችሏቸዋል። ኤ.አይ ቻት ቦት ለምን ይጠቅማል ? ድርጅቶች/ አገልግሎት አቅራቢዎች ያለማቋረጥ ከደንበኞቻቸው ጋር ለመገናኘት ይጠቅማቸዋል። ለሚጠየቀው ጥያቄምችም ፈጣን ምላሽ ይሰጣል። በርካታ ደንበኞችን በአንድ ጊዜም ያስተናግድልናል። በዚያው ልክ የሚሰጠው መረጃ ሙሉ ለሙሉ ትክክል ላይሆን ይችላል። #IsItAI? #Concepthub   #InterNews   #EU Via @Concepthubeth — Tikvah Magazine | @TikvahethMagazine
Показати все...
47
Фото недоступнеДивитись в Telegram
በህገወጥ መንገድ ወደ አረብ ሃገራት ሄደው ጉዳት ደርሶባቸው ከሚመለሱት መካከል አብዛኞቹ በኤችአይቪ እና ካንሰር እየተጠቁ ናቸው ተባለ። ባለፉት 20 አመታት ከስደት ተመላሾች፣ ጥቃት የደረሰባቸውን ሴቶችና አረጋውያንን በመደገፍ የሚታወቀው አጋር ኢትዮጵያ የተሰኘው ግብረ ሰናይ ተቋም ወደ አረብ ሃገራት ሄደው ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ተቋሙ ከሚመጡ ሰዎች አብዛኞቹ በኤችአይቪ እና ካንሰር የተጠቁ እንደሆኑ ገልጿል። የተቋሙ ኃላፊ ሄለን ዘገየ ተጠቂዎቹ ከካንሰር በብዛት የጡት፣ የእግር ካንሰርና ሌሎችም እንደሚገኝባቸውና በኤችአይቪ የሚያዙት የስደት ተመላሾች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን ገልጸዋል። ኢትዮጵያውያኑ በአሰቃቂ የስራ ሁኔታ ውስጥ መስራታቸው፣ የምግብ ሁኔታና ሌሎች ተደራራቢ ችግሮች ተጋላጭነታቸውን እየጨመረ ነው። ኃላፊዋ በቅርቡ አይኗን አጥታለች ተብላ ወደ ተቋሙ የመጣች ከ7 አመት በላይ በአረብ ሃገር የሰራች ልጅ ገላዋ ሲታጠብ ጡቷ አብጦ መገኘቱንና ሰውነቷ መጎዳቱን አንስተዋል። ይህችው ልጅ፥ ወደ ህክምና ተወስዳ ምርመራ ሲደረግላት የጭንቅላት ካንሰር እንደተገኘባት፣ ረፍዶ ስለነበር ሃኪሙ ለመኖር የቀራት ጥቂት ጊዜ እንደሆነ እንደነገራቸውና ከቤተሰቦቿ ጋር ወደ ሃገሯ አላማጣ ከተላከች ከአንድ ሳምንት በኋላ መሞቷን ተናግረዋል። የአጋር ኢትዮጽያ ኃላፊዋ አብዛኞቹ ደላሎች የቅርብ ቤተሰብ የሚባሉት አጎትና አክስት ስለሆኑ ተጎጂዎች እነሱን ለመክሰስም ሆነ ለመውቀስ እንደሚቸገሩ ተናግረዋል። መረጃው የሸገር ኤፍኤም ነው። @TikvahethMagazine
Показати все...
😢 122 49🤬 3💔 3👎 2
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ፖሊስ "የተመረዘ ምግብ በልተዉ" ነበር ያላቸው 7 የአንድ ቤተሰብ አባላት ህይወት ማለፉን ገለጸ። በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምስራቅ ጉራጌ ዞን መስቃን ወረዳ መሰረተ ወገራም ቀበሌ ዳሾ ቆቶ  ተብሎ በሚጠራዉ መንደር ህዳር 6 ቀን 2018 ዓ.ም ምሽት 1:00 ሰዓት አብረዉ እራት የተመገቡ 8 የቤተሰብ አባላት መካከል 7ቱ ህይወታቸው አልፏል። የክልሉ ፖሊስ የወንጀል መረጃ ኢንተለጀንስ ዳይሬክቶሬት ተወካይ ምክትል ኮማንደር ያለዉ ተመስገን እንደገለፁት በአብሮነት እራት እንደተመገቡ  ብዙም ሳይቆዩ ከፍተኛ ለሆነ ህመም መዳረጋቸዉን መረጃ የደረሳቸዉ  የአካባቢዉ ነዋሪዎች  የተጎጂዎችን ህይወት ለማትረፍ  ተረባርበዉ ወደ ሆስፒታል አድርሰዋቸዋል። ቢሆንም ከተጎዱ የቤተሰቡ አባላት ሦስቱ ማለትም የ5  ዓመቱ መንግስቱ ኃይሌ ፣የ7 ዓመቱ መክብነ ኃይሌ እና የ17 ዓመቱ  ተክሉ ኃይሌ የተባሉት ወንድማማቾች በዕለቱ ሆስፒታል እንደደረሱ ህይወታቸዉ አልፏል። የተቀሩ ተጎጂዎችን ህይወት በህክምና ለማትረፍ ሀኪሞች ያልተቋረጠ ጥረት ቢያደርጉም የ14 ዓመቷ መቅደስ ኃይሌ እና   የ15 ዓመቱ ገብሬ ኃይሌ የሁለቱን እህትና ወንድም ህይወት ማትረፍ ሳይቻል ቀርቶ ህዳር 7 ቀን 2018 ዓ.ም  ምሽት 11:00 ሰዓት ህይወታቸው አልፏል። የ1ዓመት ከ7 ወሩ ህፃን ሲሳይ ኃይሌ ህዳር  9 ቀን 2018 ዓ.ም ጥዋት 2:00 ሰዓት ላይ ህይወቱ ሲያልፍ የስድስቱ  ሟች ልጆች አባት የሆነዉ አቶ ኃይሌ አበራ ህዳር 10 ቀን 2018 ዓ.ም ለሊት ህይወታቸው አልፏል። ፖሊስ የባለቤቷንና የስድስት ልጆችዋን ህልፈት ለማወቅ ያልታደለችዉ ወይዘሮ ዳመነች ደንበል በሚኒሊክ ሆስፒታል [በጽኑ ህሙማን] ክፍል ዉስጥ ሆና በህክምና እየተረዳች እንደሆነ አስታውቋል። ተጎጂዎች የተመገቡት ምግብ የተመረዘዉ  በማንና እንዴት? የሚለዉን እዉነታ ለማረጋገጥና የተፈፀመዉን ድርጊት አጣርቶ እዉነታዉ ለማረጋገጥ ከምስራቅ ጉራጌ ዞን እና ከመስቃን ወረዳ  የተወጣጣ የምርመራ አጣሪ ግብረ ኃይል ተዋቅሮ ምርመራ መጀመሩ ተገልጿል። ኮማንደር ያለዉ ተመስገን የምርመራ ግብረ ኃይሉ በድርጊቱ የሌሎች እጅ ሊኖር ይችላል በሚል ጥርጣሬ  አስር ሰዎችን በቁጥጥር ስር  አዉሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን ገልፀዋል። ተጎጂዎች በዳግማዊ ምንሊክ ሆስፒታል ህክምና መከታተላቸውን የገለጸው ፖሊስ የሟቾች የአስክሬን ምርመራ ዉጤት እየተጠበቀ መሆኑንና ውጤቱም ስለጉዳዩ የተሻለ ፍንጭ የሚሰጥ መረጃ ሊገኝ እንደሚችል ጠብቋል።  መረጃው የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ነው። @TikvahethMagazine
Показати все...
😢 368💔 103 99🕊 6🤯 2💯 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
90 በመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የገንዘብ ልውውጥ የሚከናወነው በዲጂታል መንገድ ነው ተባለ። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ኤፍሬም መኩሪያ በባንኩ ከሚከናወነው የገንዘብ ልውውጥ ወይም ግብይት ውስጥ 90 በመቶ የሚሆነው የሚፈፀመው በዲጂታል መንገድ መሆኑንና ከቀደመው አመት አንፃር በ17% ብልጫ እንዳለው ተናግረዋል። ምክትል ፕሬዚደንቱ በ2017 በጀት አመት በኢትዮጵያ የፋይናንስ ተቋማት በዲጂታል መንገድ የተዘዋወረው ብር 17.7 ትሪሊየን ብር መሆኑን አንስተው ከዚህ ውስጥ 13 ትሪሊየኑ ወይም 73% ያህሉ በንግድ ባንክ በኩል መፈፀሙን ተናግረዋል። የዲጂታል ዝውውሮች እንደማደጋቸው ሁሉ የሳይበር ተጋላጭነትም እየጨመረ መሆኑን ያነሱት አቶ ኤፍሬም አሁን ላይ ግብይቶች ዲጂታል በመሆናቸው እየገጠማቸው ያለው ስጋት የሳይበር ጥቃትና የዲጂታል ማጭበርበር መሆኑን አንስተዋል። አቶ ኤፍሬም የሰው ሰራሽ አስተውሎትን በመጠቀም የሳይበር ስጋቶችን አስቀድሞ ለመለየት፣ ለመከላከል እና ምላሽ ለመስጠት ባንኩ እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል። ዘገባው የሸገር ኤፍኤም ነው። @TikvahethMagazine
Показати все...
51👎 14👍 5
Фото недоступнеДивитись в Telegram
‼️ ይፍጠኑ ‼️ በመሀል ሳር ቤት ቫቲካን ኢምባሲ አካባቢ ‼️ # ቴምር ሪልስቴት ከ8 በላይ ሳይቶችን ጥንቅቅ አድርገን አስረክበን አሁን ደግሞ ሳርቤት ቫቲካን ኢምባሲ አካባቢ ለሽያጭ ያወጣናቸው አፓርትመንቶች   ➤ 100% ለሚከፍሉ 35% ቅናሽ 👉 ባለ 2 መኝታ = 81ካሬ = 6ሚሊዮን 👉 ባለ 2 መኝታ = 106ካሬ = 7.9ሚሊዮን 👉 ባለ 3 መኝታ = 139ካሬ = 10.3ሚሊዮን 👉 ባለ 3 መኝታ = 152ካሬ = 11.3ሚሊዮን ➤ በ20% ቅድመ ክፍያ (በግንባታ ሂደት ለሚከፍሉ) 👉 81ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 9.3ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (1.8ሚሊዮን) 👉 106ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 12.1ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (2.4ሚሊዮን) 👉 139ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 15.9ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (3.1ሚሊዮን) ⩩ ቀሪውን 80%፤ በግንባታ ሂደት፤ ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት። ⩩ 30% እና ከዚያ በላይ ለሚከፍሉ፤ ከከፈሉት ላይ ከ15 -25% ቅናሽ አዘጋጅተናል። ለበለጠ መረጃ ይደውሉልን ☎️+251980782850
Показати все...
13
በግ መስለው ስፔን ሊገቡ የነበሩ 3 ስደተኞች ጉዳይ ... ተሸውደዋል ? ከሰሞኑ በተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያዎች 3 ስደተኞች በግ መስለው በአልጄሪያ በኩል ወደ ስፔን ሊገቡ ሲሉ ተያዙ የሚል መረጃ ሲሰራጭ ሰንብቷል። በርካቶችም ወሬውን ተቀባብለው ያሰራጩት ቢሆንም ነገሩ ግን እንደተዘገበው አይደለም። ምስሉ እንደተባለው ስደተኞች በግ መስለው ወደ ስፔን ሊገቡ ሲሉ የተያዙበት ሳይሆን ምስሉ ባለፈው ዓመት ታዋቂውን የካርቱን ፊልም "Shaun the sheep" ለማስመሰል ሰዎች በቲክቶክ ካጋሩት ቪዲዮ የተወሰደ ነው። ቪዲዮውም የተጋራው ባለፈው ዓመት ነበር። በተጨማሪም ከተባለው ነገር ጋር የተገናኘ በአልጄሪያም ሆነ በስፔን መንግስት የተሰጠ መግለጫ የሌለ ሲሆን ታማኝ የዜና አውታሮችም አልዘገቡትም። በአሁኑ ጊዜ የሀሰተኛ መረጃዎች ስርጭት በእጅጉን እየጨመረ ሲሆን ሁሉም መረጃን ከማጋራቱ በፊት ምንጩ ምንድን ነው ብሎ ማጣራት እንዳለበት ያሳየ ሁነት ሆኗል። 📹 ትክክለኛው የቲክቶክ ቪዲዮ @TikvahethMagazine
Показати все...
2.16 MB
🤣 302 94👍 25😢 7👎 5🔥 1
ከአስከፊው የሱዳን ጦርነት ጀርባ የውጪ ሀገራት ተሳትፎ ምን ይመስላል? ሱዳን ሁለቱ ጀነራሎች በሚመሯቸው ጦሮች የተነሳ የእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ ከገባችና የበርካቶች ህይወት መቀጠፍ ከጀመረ 31 ወራት ተሻግሯል። የሱዳንን ጦርነት ካባባሱ ነገሮች አንዱ የውጪ ሃገራት በጦርነቱ እጃቸውን ማስገባት ሲሆን የውጪ ኃይሎች ሁለቱንም ተፋላሚዎች በየጎራው መደገፍ የንጹሐንን ህይወት ስቃይ ውስጥ ከቷል። እንደ ግብፅና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ያሉ ሃገራት በሱዳን ጦርነት በጉልህ ቢነሱም ከ10 በላይ የአፍሪካ፣ የመካከለኛውን ምስራቅና እስያ ሃገራት በጦርነቱ እጃቸውን እንዳስገቡ ይነገራል። የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ሚና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቀጣናው ባሉ የልማትም ሆነ የግጭት ዜናዎች ስሟ የማይጠፋው የመሃመድ ቢንዛይዷ ሃገር የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በሱዳን ጉዳይ ስሟ መነሳት ከጀመረ ሰነባብቷል። ኤምሬቶች ሱዳን በ2009 ከቻድ ጋር የድንበር ግጭት ውስጥ ስትገባ ያሸማገለች ሲሆን ከአልበሽር መነሳት በኋላ ለነበረው የሽግግር ምክር ቤትም ድጋፍ ስታደርግ ነበር። የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መጀመሪያ አካባቢ በግጭቱ ገለልተኛ ነበረች ቢባልም በኋላ ላይ ለፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ድጋፍ ማድረግ መጀመሯ ይነሳል። በፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ በተፈፀሙ ወንጀሎችም በተባባሪነት በጦሩ በዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት የተከሰሰችው የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ከደቡብ አሜሪካ ጭምር ተዋጊዎችን እያሰለጠነች የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉን ትደግፋለች ተብላ ትከሰሳለች። የግብፅ እና ሳዑዲ አረቢያ ሚና ግብፅ በተደጋጋሚ ለሱዳን ጦር ድጋፍ እንደምታደርግ ሲነገር በተደጋጋሚም ከፍተኛ ባለስልጣናቷን ወደ ሱዳን እየላከችና የጦሩን መሪዎች በካይሮ እያስተናገደች ትገኛለች። ሌላኛዋ ሃገር ሳዑዲ አረቢያ ለጦሩ የፋይናንስና የሎጅስቲክስ ድጋፍ እንደምታደርግ ይታመናል የፈጥኖ ደራሽ ኃይል መሪ ጀነራል ዳጋሎ ግብፅ ለጦሩ የጦር መሳሪያ ድጋፍ ታደርጋለች ብለው ሲከሱ ቆይተዋል። ሀገራቱ በየዘርፋቸው ተፋላሚዎችን ከመደገፍ በተጨማሪ በሱዳን ባለው የወርቅ ንግድ እጅጉን አትራፊ እየሆኑ መጥተዋል። ለራሳቸው ጦርነት ውስጥ ያሉትና የሰነበቱት እንደ ሩሲያና ኢራን ያሉ ሃገራትም በየፊናቸው የድሮንና ወታደራዊ ድጋፎችን እያደረጉ ይገኛሉ። የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ ግብፅና ሩሲያ ኦማር አል በሽር ከስልጣን ሲወገዱ አራቱም ለሱዳን ጦር ድጋፍ ነበራቸው። ሩሲያ ከዩክሬን ጋር ውጊያ ውስጥ ብትሆንም በጦርነቱ ተሳታፊ እየሆነች ሲሆን አሜሪካ ሩሲያ የራሷን የፖለቲካ አላማ ለማሳካት ከሁለቱም ተፋላሚዎች ጋር ትሰራለች ስትል ትከሳታለች። በቅርቡም የሩሲያው ዋግነር ለፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ የሚሳኤል ድጋፍ አድርጓል የሚሉ ሪፖርቶች ወጥተው ነበር። ሁሉም በጦርነቱ ተሳታፊ የሆነ አካል የራሱ ጥቅሞች ያሉት ሲሆን የወርቅ ንግድ አለፍ ሲልም ከሰሃራ በታች ባለው አፍሪካና በአፍሪካ ቀንድ ተፅዕኗቸውን ለማሳደግ ተሳታፊ እንደሆኑ ይታመናል። Source: CNN, THE CONVERSATION , FPRI @TikvahethMagazine
Показати все...
79😢 25🤔 6💔 4👍 2👎 2👏 2
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ይዘት ፈጣሪው ኤ.አይ (Generative AI? ) ምንድን ነው ? ባለፉት 10 ዓመታት የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ድንቅ የፈጠራ ውጤት ሆኖ የሚታይ ቢሆንም በዚህ ልክ ለመስፋፋቱ ምክንያት በራሱ ይዘት መፍጠር የሚችለው ኤ.አይ (Generative AI) ይበልጡኑ እ.ኢ.አ 2022 የቻት ጂፒቲ መተዋወቅ ጋር የተያያዘ ነው። ለመሆኑ Generative AI ምንድን ነው ? ከዚህ ቀደም ሰዎች ኢንተርኔት ላይ የሚፈልጉት ነገር ለማግኘት ኢንተርኔትን በማሰስ (Web Browsing) ነው ይህም ይህም በፊት ያሉ ውጤቶችንና መረጃዎችን የምናገኝበት መንገድ ነው። Generative AI የምንለው ከዚህ ይለያል። ይህም ቀደም ያሉ ውጤቶችን ማምጣት ሳይሆን በሰዎች ጥያቄ ላይ መሰረት አድርጎ የተሰናሰለ አዲስ መልስ የሚሰጥ ነው። Generative AI መሰረት ያደረገው ምን ላይ ነው ? ሰዎች ለሚያቀርቧቸው ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት መሰረት የሚሆነው ቀድሞ ማሽኑን ለማሰልጠን የምንጠቀምበት ዳታ (የመረጃዎች ጥርቅም) ነው። ለዚህም በርካታ መረጃዎች ያስፈልጋሉ። እዚህ ላይ ማወቅ ያለብን የምናገኘው መልስ በዋነኝነት በሰለጠነበት የመረጃ ክምችት ላይ የተወሰነ በመሆኑ ሊሳሳትና ትክክለኛ መልስ ሊሰጠን እንደሚችል ነው። Generative AI ምን መስራት ይችላል ? ምስሎችን መፍጠር፣ ሙዚቃ ማቀናበር፣ ቪዲዮ መስራት፣ ጹሑፍ መጽሐፍ፣ ኮድ መጻፍ እና መሰል ተግባራትን ማከናወን ይችላል። #IsItAI #Concepthub   #InterNews   #EU via @concepthubeth - Tikvah Magazine | @TikvahethMagazine
Показати все...
47👍 1👎 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
በአፍሪካ በሚሸጡ የህፃናት ምግቦች ላይ ስኳር እየጨመረ የሚሸጠው የስዊዘርላንድ ድርጅት "Nestle" የተሰኘው የስዊዘርላንድ የምግብ አምራች ወደ አፍሪካ በሚላኩ የህፃናት ምግብ ላይ ስኳር እየጨመረ እንደሚልክ የምርመራ ሪፖርት አመላክቷል። ድርጅቱ ወደ ሃብታም ሃገሮች ሲልክ የተቀመጠውን የጤና መመዘኛ በአፍሪካ እየተገበረ እንዳልሆነ ነው ክስ የቀረበበት። "Public Eye" የተሰኘው የስዊዘርላንድ የሰብዓዊ መብት ተቋም ወደ አፍሪካ የሚላኩ የህፃናት የምግብ ምርቶች ላይ ድርጅቱ በአውሮፓ ከሚሸጡት በተጨማሪነት ስኳር እየጨመረ እየሸጠ እንደሆነ አጋልጧል። የሰብዓዊ መብት ተቋሙ በ20 የአፍሪካ ሀገራት የሚሸጡ 100 የህፃናት ምግቦችን ወስዶ በላብራቶሪ ምርመራ 90 በመቶዎቹ የተጨመረ ስኳር እንደተገኘባቸው አስታውቋል። በምርመራው በአማካይ ከ6 -7.5 ግራም ስኳር የተጨመረባቸው ምርቶች ሲገኙ ትልቁ የተገኘው በኬንያ በተሸጠ ምርት ላይ ነው። የዓለም ጤና ድርጅት በ2022 እ.ኤ.አ ህፃናትን በለጋነታቸው ለስኳር ምርቶች ማጋለጥ ለከፋ በሽታ እንደሚያጋልጥ መመሪያ ቢያወጣም ይህ ድርጅት ግን መመሪያውን ጥሶ ወደ አፍሪካ በሚላኩ የህፃናት ምግቦች ላይ ስኳር እየጨመረ መሸጡን ነው ሪፖርቱ ያስቀመጠው። ድርጅቱ የሚያመርተው የህፃናት ምግብ በስዊዘርላንድ ሲሸጥ ምንም ስኳር የሌለው ሲሆን በሌሎች የአውሮፓ ሃገራት ሲሸጥም እስከ 6 ወር ላሉ ህፃናት በሚሸጠው ምግብ ላይ ምንም ስኳር የለውም። 19 የአፍሪካ የሲቪል ማኅበረሰብ ተቋማትም ድርጅቱ ወደ አፍሪካ ስኳር ያለባቸውን የህፃናት ምግብ መላክ እንዲያቆም በደብዳቤ ጠይቀዋል። በደብዳቤው "ለስዊዝና ለአውሮፓ ህፃናት የተጨመረ ስኳር ተገቢ ካልሆነ ለአፍሪካ ህፃናትም ተገቢ አይደለም" ሲሉ ጠይቀዋል። አምራቹ ድርጅት ግን የወጣው ሪፖርት የተሳሳተ ነው ሲል በሁሉም ሃገራት ተመሳሳይ ምርት እንደሚልክና አድሎ እንደማይፈፅም ገልጿል። ድርጅቱ ስኳር ያለባቸውና የሌለባቸውን ምርቶች በአውሮፓም ሆነ በአፍሪካ በተመሳሳይ ዋጋ እንደሚያቀርብ ገልፆ 97% በሚሆነው ገበያው ስኳር የሌለባቸውን ምርቶች እያቀረበ መሆኑን ገልጿል። የአለም ጤና ድርጅት ከ1990 ወዲህ ከአምስት አመት በታች የሆኑ ህፃናት ከመጠን በላይ ውፍረት በአፍሪካ በእጥፍ እንደጨመረና ስጋት እየሆነ መምጣቱን መግለፁ ይታወሳል። መረጃው የአልጄዚራ ነው። @TikvahethMagazine
Показати все...
🤔 61🤬 43 40😢 18💔 9👍 8🔥 2
Фото недоступнеДивитись в Telegram
አፍሪካ የራሷ የስትሮክ መመሪያ ለምን ያስፈልጋታል? የስትሮክ በሽታ አዕምሮ በቂ የሆነ ደም ሳያገኝ ሲቀር የሚከሰት በሽታ ሲሆን በሽታው ከጊዜ ወደ ጊዜ በአፍሪካ እየተስፋፋ መጥቶ አሁን ላይ በአህጉሪቱ ለሞት እና ለአካል ጉዳት መንስኤ ከሆኑ በሽታዎች አንዱ ሆኗል። በየዓመቱ በበሽታው ከ100,000 ሰዎች ውስጥ 316 #አዳዲስ ተጠቂዎች ሲመዘገቡ አሁን ላይ ከ100,000 ሰዎች ደግሞ 1460 ያህሉ በበሽታው በአፍሪካ ተይዘው ይገኛሉ። ምንም እንኳን ስትሮክ በዚህ ልክ አሳሳቢ ቢሆንም በአኅጉር ደረጃ ስትሮክን ለመቆጣጠር የተቀመጠ ማዕቀፍ ለም። በአህጉሪቱም ብቸኛዋ በብሔራዊ ደረጃ የተቀመጠ መመሪያ ያላት ሀገር ደቡብ አፍሪካ ነች። ባደጉት የሰሜን አሜሪካና አውሮፓ ሃገራት ስትሮክን የተመለከቱ መመሪያዎች ሲኖሩ እነዚህ መመሪያዎችንም በየጊዜው ማሻሻያዎች ይደረግባቸዋል። የአፍሪካ ሀገራትም በእነዚህ መመሪያዎች ላይ የተመሰረቱና የራሳቸው መመሪያ የሌላቸው ናቸው። ታዲያ መመሪያው ለምን ያስፈልጋል? ካደጉት ሀገራት የተወሰዱ መመሪያዎች አፍሪካ ካላት ኃብትና የጤና ሥርዓት አንፃር ተስማሚ እና ውጤታማ አይደሉም። አፍሪካ የራሷን የጤና ስርዓት ማዕከል ያደረገ መመሪያ እንደሚያስፈልጋት ይታመናል። በአፍሪካ በርካታ ሆስፒታሎች የትኛው የስትሮክ ዓይነት እንደሆነ ለመለየት የሚያስችል መሳሪያ እንኳን የላቸውም። በአፍሪካ በርካታ የህዝብ ቁጥር ያላት ናይጄሪያ በ2021 እ.ኤ.አ 209 "CT scanners" የነበራት ሲሆን ለንፅፅር በጀርመን በወቅቱ ከ3000 በላይ መሳሪያዎች ነበሩ። በአፍሪካ በ100,000 ሰዎች 0.12 ኒውሮሎጂስቶች ( የነርቭና የአዕምሮ ሃኪሞች) እንዳሉ ሲገለጽ፥ እንደ ጂቡቲ፣ ኤርትራ፣ ጊኒ ቢሳው፣ ሌሴቶ፣ ላይቤሪያና ደቡብ ሱዳን ደግሞ በዘርፉ የተማረ አንድም ሰው የላቸውም። በአንዳንድ የአፍሪካ ኃገራት ምጣኔው 1 ኒውሮሎጂስት ለ500,000 ሰው ይደርሳል። በአውሮፓ በንፅፅር ከተመለከትን ደግሞ በ100,000 ሰው 8.45 ይሆናል። በአፍሪካ በርካቶች የስትሮክ ተጋላጭነትን በሚጨምሩ በሽታዎች ሲያዙ ለአብነትም 28.5% የሚሆነው ህዝብ ከፍተኛ በሆነ የደም ግፊት የተጠቃ ነው። ቁጥሩ ቀላል ያልሆነ ሰውም በስኳር በሽታ ተይዟል። አፍሪካ ምን አይነት የስትሮክ መመሪያ ያስፈልጋታል? አፍሪካ የራሷን ኃብት ባገናዘበ መልኩ የስትሮክ መመሪያ ሊኖራት እና በዘርፉ የሰለጠኑ የጤና ባለሙያዎዎች ያስፈልጓታል። በታንዛኒያ ተሞክሮ ውጤታማ የሆነው የቴሌሜዲስን መተግበርም በአማራጭነት ይቀመጣል። ይህም በገጠር የጤና ማዕከላትና በስትሮክ ማዕከላት መካከል ትስስር እንዲኖር ያግዛል። መመሪያዎቹ በየጊዜው የሚደረግን የደም ግፊት ምርመራን የሚያበረታቱና መከላከልን መሰረት ያደረጉ ሊሆኑ ይገባል። ለህብረተሰቡ በቂ ግንዛቤ መስጠትና ስትሮክን ለመከታተል የሚያስችሉ ቀላል የጤና መተግበሪያዎች መሰራትም ሌላኛው መንገድ ነው። መመሪያዎቹ በተጨማሪ በገጠርና በከተማው መካከል ያለውን ክፍተት በማጥበብ ደረጃ ሚናቸው የጎላ ሊሆን ይገባል። የጋራ የሆነ የስትሮክ መመሪያ በአፍሪካ ለማምጣት የጋራ አመራር የሚጠይቅ ሲሆን በዘርፉ ያሉ የጤና ባለሙያዎችም ለዚህ ግንባር ቀደም መሪ መሆን ይጠበቅባቸዋል። ይህ ጹሑፍ ፅሁፉ ከTHE CONVERSATION ድህረገጽ ላይ የተወሰደ ነው። @TikvahethMagazine
Показати все...
54👍 3👎 2