uz
Feedback
TIKVAH-MAGAZINE

TIKVAH-MAGAZINE

Kanalga Telegram’da o‘tish

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። #ኢትዮጵያ ያግኙን +251913134524

Ko'proq ko'rsatish
2025 yil raqamlardasnowflakes fon
card fon
194 394
Obunachilar
-5024 soatlar
-1767 kunlar
-81830 kunlar
Postlar arxiv
እርሶ በሚጠቀሙባቸው ማኅበራዊ ሚዲያዎች ባለፉት አንድ ወራት የትኞቹ መረጃዎች በስፋት ሀሰተኛ መረጃዎች የተሰራጨባቸው ነበሩ?Anonymous voting
  • 1. ፖለቲካዊ እና ከግጭት ጋር የሚያያዙ መረጃዎች
  • 2. የማጭበርበሪያ ስልቶችና ሀሰተኛ የሥራ ማስታወቂያዎች
  • 3. አሳሳች የጤና መረጃዎች
  • 4. በኤ አይ የተቀነባበሩ ምስሎችና ቪዲዮዎች
0 votes
star reaction 1❤ 45👎 19🤷‍♂ 12
Photo unavailableShow in Telegram
ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ኡጋንዳ በህንድ ውቅያኖስ የባህር በር እንደሚኖራት ተናገሩ። ከቀናት በፊት የኡጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ ኡጋንዳ የህንድ ውቅያኖስ ባለቤት ነች በማለት በባህር አማራጭ ዙሪያ ከኬንያ ጋር ግጭት ሊኖር እንደሚችል ተናግረው ነበር። የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ" ኡጋንዳ እና ኬንያ ወንድማማቾች ናቸው፤ ኡጋንዳ በኬንያ በኩል የባህር አማራጭ ታገኛለች" ብለዋል። ሙሴቬኒ እንደ ኢጋንዳ ያሉ ሃገራት የባህር በር ማጣታቸው ምክንያታዊ እንዳልሆነ አንስተው በአፍሪካ ያሉ ፖለቲካዊ ድንበሮች ለንግድና ደህንነት የማይመቹ ናቸውም ብለው ነበር። ዊሊያም ሩቶ ኡጋንዳ በኬንያ በኩል የባህር በር እንደሚኖራት ከተናገሩ በኋላ የኡጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ዊሊያም ሩቶን እውነተኛ ፓን አፍሪካኒስት ሲሉ ገልፀዋቸዋል። ዘገባው ከኬንያ ታይምስ የተገኘ ነው። @TikvahethMagazine
Hammasini ko'rsatish...
❤ 207👍 40🤣 10🤝 2
Photo unavailableShow in Telegram
#Update የምያንማር ወታደሮች በማጭበርበሪያ ካምፖች ላይ ባደረጉት ዘመቻ 1590 የውጪ ዜጎችን መያዛቸውን አስታወቁ። የምያንማር ጦር ከታይላንድ በሚዋሰንበት አካባቢ በሚገኙ የማጭበርበሪያ ካምፖች ለ5 ቀናት ኦፕሬሽን አድርጎ ወደ ምያንማር በህገወጥ መንገድ የገቡ ናቸው ያላቸውን 1590 የውጪ ሃገር ዜጎች ማሰሩን ገልጿል። በተጨማሪም 2893 ኮምፒውተሮች ፣ 21750 የሞባይል ስልኮች፣ 101 የስታርሊንክ የሳተላይት መቀበያና ሌሎች ለማጭበርበር ተግባራት ይውሉ የነበሩ መሳሪያዎች ተይዘዋል ተብሏል። ባለፈው ወር አጭበርባሪዎቹ የስታርሊንክ የሳተላይት ኢንተርኔት አገልገሎት እንደሚጠቀሙ ከተነገረ በኋላ ተቋሙ አጭበርባሪዎች ይጠቀሙበት የነበረን 2500 የስታርሊንክ መገልገያዎች ማጥፋቱን መግለፁ ይታወሳል። ምያንማር በ2021 መፈንቅለ መንግስት ከተፈፀመባትና መረጋጋት ካቃታት በኋላ የአጭበርባሪዎች መናኸሪያ ስትሆን በርካታ የውጪ ሃገር ዜጎችሞ ተታለው ከተወሰዱ በኋላ የራሳቸው ጦር ባላቸው አጭበርባሪዎች ተገደው እንዲሰሩ ይደረጋል። ተመድ በደቡብ ምስራቅና ምስራቅ እስያ ያሉ አጭበርባሪዎች በ2023 ብቻ 37 ቢሊየን ዶላር አግኝተዋል ያለ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ቻይና በምትሰጠው ድጋፍ የተነሳ በካምፖቹ ላይ እርምጃ እየተወሰደ ይገኛል። ዘገባው የAFP ነው። @TikvahethMagazine
Hammasini ko'rsatish...
❤ 53👍 12
Photo unavailableShow in Telegram
ብዙ ወጣቶች የተዘፈቁበት የ"ቨርቹዋል" ቁማር ከኢንተርኔት መስፋፋት ጋር በተያያዘ እያደጉ ከመጡ ነገሮች አንዱ የ "ቨርቹዋል ቁማር" ነው። ነገሩ በኦንላይን መከናወኑና የክፍያ ሥርዓቶች ዲጂታል መሆናቸው ደግሞ በርካታ ሰዎች እንዲገቡበትና እንዲዘፈቁበት ምክንያት ሆኗል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ዳይሬክተሩ አቶ ደሴ ደጀኔ ለስፖርት ውርርድና ለ4 የሎተሪ አይነቶች ፈቃድ መሰጠቱን አንስተው ሌሎች የቁማር አይነቶች ግን በህግ እንዳልተፈቀዱ ቢያነሱም፥ በርካቶች በተለይ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በቨርቹዋል ጌሞች ህይወታቸውን አበላሽተዋል። ጫላ ማረማ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ሲሆን በቨርቹዋል ቁማር ከተጠመዱ ወጣቶች ውስጥ አንዱ ነው። ጫላ በመማሪያ ክፍል ውስጥ መምህራንን ከመስማት ይልቅ የሞባይል ዳታ እየገዛ እነዚህን የቨርቹዋል ቁማሮች እንደሚጫወት ይገልፃል። ጫላ የጀመረው በስፖርት ውርርድ ቢሆንም ከሰዎች ስለ ቨርቹዋል ቁማር ከሰማ በኋላ እንደገባበት ይናገራል። ወጣቱ ተማሪ ከመማሪያ ክፍል በተጨማሪ ማንበቡን ትቶ ቁማሩን ማሳደዱ ለ16 አመት ሲዘጋጅለት የነበረውን ድግሪ ዋጋ እንዳስከፈለው አንስቶ ሥነ-ልቦናዊ ሁኔታውም ሰዎችን ወደመጥላትና ደስታን ወደ ማጣት ይከታል ይላል። ጫላ ቤተሰቦቹ ለእሱ ገንዘብ ለመላክ እዳ ውስጥ እንደሚገቡ፣ እሱ ግን ቁማሩን ለመጫወት እንደሚጠቀምበት አንስቶ ከሰዎችም ብድር ውስጥ እንደገባም ይናገራል። በዚህ የተነሳ ከፍቅረኛው ጋር መለያየቱን፣ ከራሱ ጋር መጋጨቱንና ለሶስት ተከታታይ ዓመታት የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ማለፍ ሳይችል በመቅረቱም የኦንላይን ጌም ህይወቴን አበላሽቶታል ይላል። እንደ ጫላ ሁሉ በርካታ ወጣቶች በዚህ የቨርቹዋል ጌም የተጠመዱ ሲሆን ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ ሌላ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ ዓመት ተማሪ በሁሉም ቦታ ቁማሩን እንደሚጫወት ተናግሮ ከቤተሰብ ብር ከማስላክ በተጨማሪ ከጓደኞቹና ከቴሌብር ጭምር እንደተበደረ ይናገራል። ተማሪዎቹ ከአቋማሪ ድርጅቶች የሚደርሳቸው የቦነስና ሽልማት መልዕክት እንደዚሁም በተፅዕኖ ፈጣሪዎች የሚሰሩ ማስታወቂያዎች ወደቁማሩ እንዲመለሱ እንደሚስባቸው ይናገራሉ። የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር የህጉ አፈፃፀም ላይ ክፍተቶች እንዳሉ አንስቶ ድጋሚ እንደሚታይ ገልጿል። የዓለም ጤና ድርጅት ቁማር በኦንላይን መንገድ መቅረቡና በተፅዕኖ ፈጣሪዎች መተዋወቁ እንደሚያስፋፋው ሲገልፅ በነዚህ መንገዶች ወደ ቁማሩ የገቡ ወጣቶች ግን ዛሬም የሰላም እንቅልፍ መተኛት አልቻሉም። ፅሁፉ ከአዲስ ስታንዳርድ የተገኘ ነው። @TikvahethMagazine
Hammasini ko'rsatish...
❤ 181🤣 39😢 23👍 16👎 3🙏 3🕊 3
Photo unavailableShow in Telegram
‼️ ይፍጠኑ ‼️ á‰ áˆ˜áˆ€áˆ ሳር ቤት ቫቲካን ኢምባሲ አካባቢ ‼️ # ቴምር ሪልስቴት ከ8 በላይ ሳይቶችን ጥንቅቅ አድርገን አስረክበን አሁን ደግሞ ሳርቤት ቫቲካን ኢምባሲ አካባቢ ለሽያጭ ያወጣናቸው አፓርትመንቶች   ➤ 100% ለሚከፍሉ 35% ቅናሽ 👉 ባለ 2 መኝታ = 81ካሬ = 6ሚሊዮን 👉 ባለ 2 መኝታ = 106ካሬ = 7.9ሚሊዮን 👉 ባለ 3 መኝታ = 139ካሬ = 10.3ሚሊዮን 👉 ባለ 3 መኝታ = 152ካሬ = 11.3ሚሊዮን ➤ በ20% ቅድመ ክፍያ (በግንባታ ሂደት ለሚከፍሉ) 👉 81ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 9.3ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (1.8ሚሊዮን) 👉 106ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 12.1ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (2.4ሚሊዮን) 👉 139ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 15.9ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (3.1ሚሊዮን) ⊊ ቀሪውን 80%፤ በግንባታ ሂደት፤ ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት። ⊊ 30% እና ከዚያ በላይ ለሚከፍሉ፤ ከከፈሉት ላይ ከ15 -25% ቅናሽ አዘጋጅተናል። ለበለጠ መረጃ ይደውሉልን ☎️+251980782850
Hammasini ko'rsatish...
❤ 16👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
በናይጄሪያ ከ300 በላይ ተማሪዎች በታጣቁ ሰዎች ታግተው ተወሰዱ። በናይጀሪያ ኒጀር ግዛት ከሚገኝ የሁለተኛ ደረጃ የካቶሊክ ትምህርት ቤት 303 ተማሪዎችና 12 መምህራን በታጣቂዎች መወሰዳቸው ተዘግቧል። ባለፈው ሳምንት በናይጄሪያ 25 ተማሪዎች ተወስደው አንዷ ማምለጧና የቀሩት 24ቱ ያሉበት እንደማይታወቅ ተነግሯል። ለተማሪዎቹ መወሰድ ኃላፊነት የወሰደ አካል የሌለ ሲሆን የኒጀር ግዛት ያለ መንግስት ፈቃድ ትምህርት ቤቱ ዳግም በመከፈቱ ተማሪዎችና መምህራን መቅረት ለሚችል አደጋ ተጋርጠዋል ብሏል። በናይጄሪያ እየተስፋፋ የመጣውን የተማሪዎች ታግቶ መወሰድ ተከትሎም የሃገሪቱ ፕሬዚዳንት ቦላ ቲኑቡ በቡድን 20 አባል ሃገራት ስብሰባ ለመካፈል ወደ ደቡብ አፍሪካ ሊያደርጉት የነበረውን ጉዞ ሰርዘዋል። ዘገባው የአልጄዚራ ነው። @TikvahethMagazine
Hammasini ko'rsatish...
😢 44❤ 24🤣 2👎 1
Photo unavailableShow in Telegram
የሶማሊያ ካቢኔ የሴት ልጅ ግርዛትን የሚከለክል የህግ ማዕቀፍ አፅድቋል። የሶማሊያ ካቢኔ የሴት ልጅ ግርዛትን የሚከለክል ህግ ሲያፀድቅ ለሶማሊ ሴቶች ትልቅ ድል ነው ተብሏል። የሴት ልጅ ግርዛት በሶማሊያ ባህል ውስጥ ለረጅም ዘመናት የቆየ ጎጂ ባህል ሲሆን በካቢኔው የፀደቀው ማዕቀፍ ድርጊቱን ከመከልከል በተጨማሪ በወንጀል የሚያስጠይቅ አድርጎታል። እንደ ተመድ የህዝብ ፈንድ መረጃ ከሆነ በሶማሊያ ከሚገኙ ዕድሜያቸው ከ15-49 ዓመት ከሆኑ ሴቶች መካከል 98 በመቶዎቹ የሴት ልጅ ግርዛት የተፈፀመባቸው ናቸው። በአለም አቀፍ ደረጃ 230 ሚሊየን ሴቶች ለዚህ ጎጂ ተግባር የተጋለጡ ቢሆንም አሁንም ባለው የአረዳድ ችግር የተነሳ ድርጊቱ በአንዳንድ ቦታዎች መፈፀሙን ቀጥሏል። ዘገባው የHORN OBSERVER ነው። @TikvahethMagazine
Hammasini ko'rsatish...
❤ 54👏 23👍 5🤣 3🤔 1
Photo unavailableShow in Telegram
የጃኮብ ዙማ ልጅ ለሩሲያ ጦርነት ከሁለት ሃገራት ወጣቶችን ትመለምላለች ተባለ። የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ ሴት ልጅ ዱዱዚሌ ዙማ ሩሲያ ከዩክሬን ጋር በምታደርገው ጦርነት ለሩሲያ ጦር ከደቡብ አፍሪካና ቦትስዋና ወጣት ወንዶችን ስትመለምል ነበር ተብሏል። የቀድሞ ፕሬዚዳንት ልጅ ለአባቷ የፖለቲካ ፓርቲ የጥበቃ ስልጠና ሊወስዱ ነው በሚል ስም 20 ወጣት ወንዶች ወደ ሩሲያ እንደላከች ሲገለፅ የወጣቶቹ ቤተሰቦችም ወጣቶቹ በሩሲያ ቋንቋ የተፃፈ ወታደራዊ ኮንትራት እንዲፈርሙ ከተደረገ በኋላ ወደ ጦር ግንባር እንደተላኩ ተናግረዋል። አንዳንዶቹ ወደ ሩሲያ ያቀኑት ወጣቶች ከባለፈው ነሐሴ ወር ጀምሮ ከቤተሰባቸው ጋር ያላቸው ግንኙነት መቆሙም ተገልጿል። ዩክሬን ባለፉት ሳምንታት ከ1400 የሚልቁ አፍሪካውያን ወጣቶች ለሩሲያ እየተዋጉ እንደሆነ ማስታወቋ የሚታወስ ሲሆን ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳም የደቡብ አፍሪካ ዜጎች እንዴት እንደተመለመሉ ምርመራ እንዲደረግ ማዘዛቸው ይታወሳል። መረጃው የDW ነው። @TikvahethMagazine
Hammasini ko'rsatish...
❤ 63😢 15💔 9👏 3🤣 3
Photo unavailableShow in Telegram
የኬንያ መንግስት በባለፈው ተቃውሞ ወቅት ገንዘብ ከፍሎ ወጣቶችን ያስፈራራ ነበር ተባለ። የሰብዓዊ መብት ተቆራቋሪው አምነስቲ ኢንተርናሽናል በኬንያ በነበረው ተቃውሞ ወቅት መንግሰት ለተለያዩ ቡድኖች እየከፈለ ወጣቶችን ያስፈራራ እንደነበርና ሃሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩ ቡድኖችን አሰማርቶ እንደነበር አስታውቋል። በተቃውሞ ወቅትም ለማስፈራራት በሰው ሰራሽ አስተውሎት የተፈጠሩ ወሲባዊ ፎቶዎች ጥቅም ላይ ውለዋል ተብሏል። አንዳንድ ተቃዋሚዎች የመግደል ዛቻ እንደደረሰባቸውና የልጆቻቸው ስም ተልኮ ሲያስፈራሯቸው እንደነበር ገልፀው የልጆቻቸውን ትምህርተ ቤት ለመቀየር እንደተገደዱ ለአምነስቲ ተናግረዋል። በአምነስቲ ሪፖርትም የሚያስፈራሩት ቡድን አባላት የመንግስትን ሃሳብ ለማሰራጨትና በማህበራዊ ትስስር ገፆች በተለይ በኤክስ ተቃውሞውን የተመለከቱ ልጥፎችን ለማውረድ በቀን ከ25,000-50,000 የኬንያ ሽልንግ ይከፈላቸው እንደነበር ተገልጧል። የታክስ ጭማሪን አስታኮ በተፈጠረው ተቃውሞም ከ100 በላይ ሰዎች መገደላቸው ይታወሳል። ዘገባው ከቢቢሲ የተወሰደ ነው። @TikvahethMagazine
Hammasini ko'rsatish...
❤ 32😢 11🤣 2
Photo unavailableShow in Telegram
ሶማሊያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጃለች። በሶማሊያ የድርቅ ሁኔታው እየተባባሰ በመምጣቱና ለረሃብ የተጋለጡ ሰዎች ቁጥር በመጨመሩ ብሔራዊ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጇ ተነግሯል። ሶማሊያ ተቋማቷ፣ የሰብዓዊ ተቋማትና አለም አቀፍ አጋሮች የምግብ አቅርቦትን በማሻሻል፣ የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትን በማሻሻል እና ለዘለቄታው የአየር ንብረት ተፅዕኖን ለመከላከል አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስዱ ጠይቃለች። ከፊል ራስ ገዟ ፑንትላንድም 1 ሚሊየን ሰዎች በድርቁ ሊጠቁ እንደሚችል ገልፃ ማስጠንቀቂያ ሰጥታለች። ከባለፈው ጥቅምት ወር ጀምሮ በሶማሊያ የሚገኙ ከ4 ሚሊየን በላይ ሰዎች ለምግብ እጥረት ሲጋለጡ 2 ሚሊየን ያህሉ ህፃናት ናቸው። በሶማሊያ የድንበር አካባቢዎች ውሃና ግጦሽ በመጥፋቱም ሰዎች ወደ ኢትዮጵያ እና ኬንያ ድንበር አካባቢ ወጣ ገባ እያሉ እየኖሩ እንደሆነ ተሰምቷል። ኢጋድ ከቀናት በፊት በሶማሊያ፣ ኢትዮጵያ እና ኬንያ ያለው ድርቅ እየተባባሰ መምጣቱን ገልፆ ማስጠንቀቂያ እንደሰጠ ይታወሳል። ዘገባው የኒው አረብ ነው። @TikvahethMagazine
Hammasini ko'rsatish...
❤ 23😢 17🙏 3
Photo unavailableShow in Telegram
🌟ብልሕ ነገዴ ገበያው በደራበት ሱቁን ይከፍታል!!! 🌟አያት ግራንድ ሞል ✨ 3000 የንግድ ሱቆች ✨በካሬ ከ126,500 ብር ጀምሮ ✨ከ 30 ካሬ እስከ 200 ካሬ አማራጮች ያለው ✨4 ክፍለ ከተሞችን አዋስኖ ሴሚሲ ሚካኤል ላይ ይገኛል 🌟 90% የደረሰ ሳይታችን በ 20% ቅድመ ክፍያ 🌟መሀል ከተማ ካዛንቺስ በካሬ 89,815 ብር በ 15% ቅድመ ክፍያ ዛሬውኑ የግልዎ ያርጉ!!! 💥ለበለጠ መረጃ በ 251977630693 በቀጥታ @ayat121921 በቴሌግራም በዋትሳፕ ይደውሉ
Hammasini ko'rsatish...
❤ 18🤝 2🤔 1🤬 1
Photo unavailableShow in Telegram
"ከዓለም የወታደራዊ በጀት ከ1% በታች በሆነ በጀት ረሃብን በ2030 ማጥፋት ይቻላል" - የዓለም ምግብ ፕሮግራም የተመድ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ረሃብን በ2030 ለማጥፋት 93 ቢሊየን ዶላር በዓመት እንደሚያስፈልግና ይህም ባለፉት አስር ዓመታት ለወታደራዊ በጀት ወጪ ከተደረገው 21.9 ትሪሊየን ዶላር አንፃር  ከ1% በታች እንደሆነ ገልጿል። በተጨማሪ የዓለም ምግብ ፕሮግራም በ2026 በአለም አቀፍ ደረጃ 318 ሚሊየን ሰዎች ለረሃብ እንደሚጋለጡ ገልፆ፥ ይህም ከ2019 አንፃር በእጥፍ የጨመረ እንደሚሆን አስታውቋል። ባለፈው ዓመት 295 ሚሊየን ሰዎች ለከፋ ረሃብ የተጋለጡ ሲሆን ከቀደመው አመት ተጨማሪ 14 ሚሊየን ሰዎች መራባቸው ተገልጿል። የተመድ ምክትል ጸሐፊ አሚና መሐመድ ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች ምግብ እንደ የጦር መሳሪያነት እያገለገለ መሆኑንም ተናግረዋል። ምከትል ጸሐፊዋ ሀገራት ረሃብን ከማጥፋት ይልቅ ገንዘብ እያወጡ ያሉት ለወታደራዊ በጀት መሆኑን በመጥፎነት አንስተዋል። በ2026 የዓለም ምግብ ፕሮግራም 13 ቢሊየን ዶላር በጀት በመያዝ 110 ሚሊየን ሰዎችን ለመደገፍ እንዳቀደ ተገልጿል። ዘገባው ከአፍሪካ ኒውስ የተገኘ ነው። @TikvahethMagazine
Hammasini ko'rsatish...
❤ 95😢 47🕊 14🤔 6🤷‍♂ 5🙏 4👍 2🤯 2
Photo unavailableShow in Telegram
"ከዓለም የወታደራዊ በጀት ከ1% በታች በሆነ በጀት ረሃብን በ2030 ማጥፋት ይቻላል" - የአለም ምግብ ፕሮግራም የተመድ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ረሃብን በ2030 ለማጥፋት 93 ቢሊየን ዶላር በዓመት እንደሚያስፈልግና ይህም ባለፉት አስር ዓመታት ለወታደራዊ በጀት ወጪ ከተደረገው 21.9 ትሪሊየን ዶላር አንፃር  ከ1% በታች እንደሆነ ገልጿል። በተጨማሪ የዓለም ምግብ ፕሮግራም በ2026 በአለም አቀፍ ደረጃ 318 ሚሊየን ሰዎች ለረሃብ እንደሚጋለጡ ገልፆ፥ ይህም ከ2019 አንፃር በእጥፍ የጨመረ እንደሚሆን አስታውቋል። ባለፈው ዓመት 295 ሚሊየን ሰዎች ለከፋ ረሃብ የተጋለጡ ሲሆን ከቀደመው አመት ተጨማሪ 14 ሚሊየን ሰዎች መራባቸው ተገልጿል። የተመድ ምክትል ጸሐፊ አሚና መሐመድ ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች ምግብ እንደ የጦር መሳሪያነት እያገለገለ መሆኑንም ተናግረዋል። ምከትል ጸሐፊዋ ሀገራት ረሃብን ከማጥፋት ይልቅ ገንዘብ እያወጡ ያሉት ለወታደራዊ በጀት መሆኑን በመጥፎነት አንስተዋል። በ2026 የዓለም ምግብ ፕሮግራም 13 ቢሊየን ዶላር በጀት በመያዝ 110 ሚሊየን ሰዎችን ለመደገፍ እንዳቀደ ተገልጿል። ዘገባው ከአፍሪካ ኒውስ የተገኘ ነው። @TikvahethMagazine
Hammasini ko'rsatish...
Photo unavailableShow in Telegram
በድርቅ በተፈተነችው ኢራን የዘነበው ዝናብ የጎርፍ አደጋ አስከተለ። በምዕራብ ኢራን አካባቢዎች በጣለው ከባድ ዝናብ የጎርፍ አደጋ ሲከሰት የሃገሪቱ የሜትሮዎሎጂ ተቋም ኢራን ካሏት 31 ግዛቶች በ18ቱ ዝናብ ይዘንባል ብሎ እንደሚጠብቅና በስድስቱ ግዛቶች ጎርፍ እንደሚኖር አስጠንቅቋል። ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ኢራን የክላውድ ሲዲንግን በመጠቀም ዝናብ ለማዝነብ የሞከረች ሲሆን የጎርፍ አደጋው ተከሰተ የተባለውም የክላውድ ሲዲንጉ በተሞከረባቸው አካባቢዎች ስለመሆኑ ተዘግቧል። የኢራን የሜትሮዎሎጂ ተቋም መሪ የክላውድ ሲዲንግ ወጪው  ከፍተኛ መሆኑን አንስተው ከሱ የሚገኘው ዝናብም ኢራን ችግሯን ለመፍታት ከሚያስፈልጋት አንፃር ኢምንት መሆኑን ተናግረዋል። ዘገባው የሮይተርስ ነው። @TikvahethMagazine
Hammasini ko'rsatish...
❤ 68🤣 20😢 10👎 2
Photo unavailableShow in Telegram
ቻት ቦት (Chat Bot) ምንድን ነው ? ቴክኖሎጂን በመጠቀም ሰዎች ከሰዎች ጋር መልዕክት መለዋወጣቸው የተለመደ ነገር ነው። ከተወሰኑ ዓመታት በፊት በመጡ ለውጦች ደግሞ ሰዎች ከማሽን ጋር መልዕክት እንዲለዋወጡ አስችሏል። ይህም ድርጅቶች ተጠቃሚዎቻቸው በተደጋጋሚ ለሚጠይቋቸው ጥያቄዎች መልዕክት እንዲመልሱ ለማስቻል ቻት ቦቶችን ተጠቅመዋል። ይህም ለተወሰኑ ጥያቄዎች ወይም መርጠን ለምንልካቸው ጥያቄዎች በአንድ ጊዜ ለብዙ ሰዎች የተዘጋጀ ምላሽ መስጠት ያስችላል። አሁን ላይ እነዚህ ቻት ቦቶች  Generative AI የያዙ ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ ለሚጠየቁት ጥያቄዎች በሰለጠኑበት መረጃ ላይ ተመስርተው ምላሽ መስጠት አስችሏቸዋል። ኤ.አይ ቻት ቦት ለምን ይጠቅማል ? ድርጅቶች/ አገልግሎት አቅራቢዎች ያለማቋረጥ ከደንበኞቻቸው ጋር ለመገናኘት ይጠቅማቸዋል። ለሚጠየቀው ጥያቄምችም ፈጣን ምላሽ ይሰጣል። በርካታ ደንበኞችን በአንድ ጊዜም ያስተናግድልናል። በዚያው ልክ የሚሰጠው መረጃ ሙሉ ለሙሉ ትክክል ላይሆን ይችላል። #IsItAI? #Concepthub   #InterNews   #EU Via @Concepthubeth — Tikvah Magazine | @TikvahethMagazine
Hammasini ko'rsatish...
❤ 47
Photo unavailableShow in Telegram
በህገወጥ መንገድ ወደ አረብ ሃገራት ሄደው ጉዳት ደርሶባቸው ከሚመለሱት መካከል አብዛኞቹ በኤችአይቪ እና ካንሰር እየተጠቁ ናቸው ተባለ። ባለፉት 20 አመታት ከስደት ተመላሾች፣ ጥቃት የደረሰባቸውን ሴቶችና አረጋውያንን በመደገፍ የሚታወቀው አጋር ኢትዮጵያ የተሰኘው ግብረ ሰናይ ተቋም ወደ አረብ ሃገራት ሄደው ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ተቋሙ ከሚመጡ ሰዎች አብዛኞቹ በኤችአይቪ እና ካንሰር የተጠቁ እንደሆኑ ገልጿል። የተቋሙ ኃላፊ ሄለን ዘገየ ተጠቂዎቹ ከካንሰር በብዛት የጡት፣ የእግር ካንሰርና ሌሎችም እንደሚገኝባቸውና በኤችአይቪ የሚያዙት የስደት ተመላሾች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን ገልጸዋል። ኢትዮጵያውያኑ በአሰቃቂ የስራ ሁኔታ ውስጥ መስራታቸው፣ የምግብ ሁኔታና ሌሎች ተደራራቢ ችግሮች ተጋላጭነታቸውን እየጨመረ ነው። ኃላፊዋ በቅርቡ አይኗን አጥታለች ተብላ ወደ ተቋሙ የመጣች ከ7 አመት በላይ በአረብ ሃገር የሰራች ልጅ ገላዋ ሲታጠብ ጡቷ አብጦ መገኘቱንና ሰውነቷ መጎዳቱን አንስተዋል። ይህችው ልጅ፥ ወደ ህክምና ተወስዳ ምርመራ ሲደረግላት የጭንቅላት ካንሰር እንደተገኘባት፣ ረፍዶ ስለነበር ሃኪሙ ለመኖር የቀራት ጥቂት ጊዜ እንደሆነ እንደነገራቸውና ከቤተሰቦቿ ጋር ወደ ሃገሯ አላማጣ ከተላከች ከአንድ ሳምንት በኋላ መሞቷን ተናግረዋል። የአጋር ኢትዮጽያ ኃላፊዋ አብዛኞቹ ደላሎች የቅርብ ቤተሰብ የሚባሉት አጎትና አክስት ስለሆኑ ተጎጂዎች እነሱን ለመክሰስም ሆነ ለመውቀስ እንደሚቸገሩ ተናግረዋል። መረጃው የሸገር ኤፍኤም ነው። @TikvahethMagazine
Hammasini ko'rsatish...
😢 122❤ 49🤬 3💔 3👎 2
Photo unavailableShow in Telegram
ፖሊስ "የተመረዘ ምግብ በልተዉ" ነበር ያላቸው 7 የአንድ ቤተሰብ አባላት ህይወት ማለፉን ገለጸ። በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምስራቅ ጉራጌ ዞን መስቃን ወረዳ መሰረተ ወገራም ቀበሌ ዳሾ ቆቶ  ተብሎ በሚጠራዉ መንደር áˆ…á‹łáˆ­ 6 ቀን 2018 ዓ.ም ምሽት 1:00 ሰዓት áŠ á‰Ľáˆ¨á‹‰ እራት የተመገቡ 8 የቤተሰብ አባላት መካከል 7ቱ ህይወታቸው አልፏል። የክልሉ ፖሊስ የወንጀል መረጃ ኢንተለጀንስ ዳይሬክቶሬት ተወካይ ምክትል ኮማንደር ያለዉ ተመስገን እንደገለፁት በአብሮነት እራት እንደተመገቡ  ብዙም ሳይቆዩ ከፍተኛ ለሆነ ህመም መዳረጋቸዉን መረጃ የደረሳቸዉ  የአካባቢዉ ነዋሪዎች  የተጎጂዎችን ህይወት ለማትረፍ  á‰°áˆ¨á‰Łáˆ­á‰ á‹‰ ወደ ሆስፒታል አድርሰዋቸዋል። ቢሆንም ከተጎዱ የቤተሰቡ አባላት ሦስቱ ማለትም የ5  ዓመቱ መንግስቱ ኃይሌ ፣የ7 ዓመቱ መክብነ ኃይሌ እና የ17 ዓመቱ  ተክሉ ኃይሌ የተባሉት ወንድማማቾች በዕለቱ ሆስፒታል እንደደረሱ áˆ…á‹­á‹ˆá‰łá‰¸á‹‰ አልፏል። የተቀሩ ተጎጂዎችን ህይወት በህክምና ለማትረፍ ሀኪሞች ያልተቋረጠ ጥረት ቢያደርጉም á‹¨14 ዓመቷ áˆ˜á‰…á‹°áˆľ ኃይሌ እና   የ15 ዓመቱ ገብሬ ኃይሌ የሁለቱን እህትና ወንድም ህይወት ማትረፍ ሳይቻል ቀርቶ ህዳር 7 ቀን 2018 ዓ.ም  ምሽት 11:00 ሰዓት ህይወታቸው አልፏል። የ1ዓመት ከ7 ወሩ ህፃን áˆ˛áˆłá‹­ ኃይሌ ህዳር  9 ቀን 2018 ዓ.ም ጥዋት 2:00 ሰዓት ላይ ህይወቱ ሲያልፍ á‹¨áˆľá‹ľáˆľá‰ą  ሟች ልጆች አባት የሆነዉ አቶ ኃይሌ áŠ á‰ áˆŤ ህዳር 10 ቀን 2018 ዓ.ም ለሊት ህይወታቸው አልፏል። ፖሊስ የባለቤቷንና á‹¨áˆľá‹ľáˆľá‰ľ ልጆችዋን ህልፈት ለማወቅ ያልታደለችዉ á‹ˆá‹­á‹˜áˆŽ ዳመነች ደንበል በሚኒሊክ ሆስፒታል [በጽኑ ህሙማን] ክፍል ዉስጥ ሆና በህክምና እየተረዳች እንደሆነ አስታውቋል። ተጎጂዎች የተመገቡት ምግብ የተመረዘዉ  በማንና እንዴት? የሚለዉን áŠĽá‹‰áŠá‰ł ለማረጋገጥና የተፈፀመዉን ድርጊት አጣርቶ እዉነታዉ ለማረጋገጥ ከምስራቅ ጉራጌ ዞን እና ከመስቃን ወረዳ  የተወጣጣ የምርመራ አጣሪ ግብረ ኃይል ተዋቅሮ ምርመራ መጀመሩ ተገልጿል። ኮማንደር ያለዉ ተመስገን የምርመራ ግብረ ኃይሉ በድርጊቱ የሌሎች እጅ ሊኖር ይችላል በሚል ጥርጣሬ  áŠ áˆľáˆ­ ሰዎችን በቁጥጥር ሾር  አዉሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን ገልፀዋል። ተጎጂዎች á‰ á‹łáŒáˆ›á‹Š ምንሊክ ሆስፒታል ህክምና መከታተላቸውን የገለጸው ፖሊስ የሟቾች የአስክሬን ምርመራ ዉጤት እየተጠበቀ መሆኑንና á‹áŒ¤á‰ąáˆ ስለጉዳዩ የተሻለ ፍንጭ የሚሰጥ መረጃ ሊገኝ እንደሚችል áŒ á‰Ľá‰‹áˆá˘  መረጃው የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ነው። @TikvahethMagazine
Hammasini ko'rsatish...
😢 368💔 103❤ 99🕊 6🤯 2💯 1
Photo unavailableShow in Telegram
90 በመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የገንዘብ ልውውጥ የሚከናወነው በዲጂታል መንገድ ነው ተባለ። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ኤፍሬም መኩሪያ በባንኩ ከሚከናወነው የገንዘብ ልውውጥ ወይም ግብይት ውስጥ 90 በመቶ የሚሆነው የሚፈፀመው በዲጂታል መንገድ መሆኑንና ከቀደመው አመት አንፃር በ17% ብልጫ እንዳለው ተናግረዋል። ምክትል ፕሬዚደንቱ በ2017 በጀት አመት በኢትዮጵያ የፋይናንስ ተቋማት በዲጂታል መንገድ የተዘዋወረው ብር 17.7 ትሪሊየን ብር መሆኑን አንስተው ከዚህ ውስጥ 13 ትሪሊየኑ ወይም 73% ያህሉ በንግድ ባንክ በኩል መፈፀሙን ተናግረዋል። የዲጂታል ዝውውሮች እንደማደጋቸው ሁሉ የሳይበር ተጋላጭነትም እየጨመረ መሆኑን ያነሱት አቶ ኤፍሬም አሁን ላይ ግብይቶች ዲጂታል በመሆናቸው እየገጠማቸው ያለው ስጋት የሳይበር ጥቃትና የዲጂታል ማጭበርበር መሆኑን አንስተዋል። አቶ ኤፍሬም የሰው ሰራሽ አስተውሎትን በመጠቀም የሳይበር ስጋቶችን አስቀድሞ ለመለየት፣ ለመከላከል እና ምላሽ ለመስጠት ባንኩ እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል። ዘገባው የሸገር ኤፍኤም ነው። @TikvahethMagazine
Hammasini ko'rsatish...
❤ 51👎 14👍 5
Photo unavailableShow in Telegram
‼️ ይፍጠኑ ‼️ á‰ áˆ˜áˆ€áˆ ሳር ቤት ቫቲካን ኢምባሲ አካባቢ ‼️ # ቴምር ሪልስቴት ከ8 በላይ ሳይቶችን ጥንቅቅ አድርገን አስረክበን አሁን ደግሞ ሳርቤት ቫቲካን ኢምባሲ አካባቢ ለሽያጭ ያወጣናቸው አፓርትመንቶች   ➤ 100% ለሚከፍሉ 35% ቅናሽ 👉 ባለ 2 መኝታ = 81ካሬ = 6ሚሊዮን 👉 ባለ 2 መኝታ = 106ካሬ = 7.9ሚሊዮን 👉 ባለ 3 መኝታ = 139ካሬ = 10.3ሚሊዮን 👉 ባለ 3 መኝታ = 152ካሬ = 11.3ሚሊዮን ➤ በ20% ቅድመ ክፍያ (በግንባታ ሂደት ለሚከፍሉ) 👉 81ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 9.3ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (1.8ሚሊዮን) 👉 106ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 12.1ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (2.4ሚሊዮን) 👉 139ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 15.9ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (3.1ሚሊዮን) ⊊ ቀሪውን 80%፤ በግንባታ ሂደት፤ ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት። ⊊ 30% እና ከዚያ በላይ ለሚከፍሉ፤ ከከፈሉት ላይ ከ15 -25% ቅናሽ አዘጋጅተናል። ለበለጠ መረጃ ይደውሉልን ☎️+251980782850
Hammasini ko'rsatish...
❤ 13
በግ መስለው ስፔን ሊገቡ የነበሩ 3 ስደተኞች ጉዳይ ... ተሸውደዋል ? ከሰሞኑ በተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያዎች 3 ስደተኞች በግ መስለው በአልጄሪያ በኩል ወደ ስፔን ሊገቡ ሲሉ ተያዙ የሚል መረጃ ሲሰራጭ ሰንብቷል። በርካቶችም ወሬውን ተቀባብለው ያሰራጩት ቢሆንም ነገሩ ግን እንደተዘገበው አይደለም። ምስሉ እንደተባለው ስደተኞች በግ መስለው ወደ ስፔን ሊገቡ ሲሉ የተያዙበት ሳይሆን ምስሉ ባለፈው ዓመት ታዋቂውን የካርቱን ፊልም "Shaun the sheep" ለማስመሰል ሰዎች በቲክቶክ ካጋሩት ቪዲዮ የተወሰደ ነው። ቪዲዮውም የተጋራው ባለፈው ዓመት ነበር። በተጨማሪም ከተባለው ነገር ጋር የተገናኘ በአልጄሪያም ሆነ በስፔን መንግስት የተሰጠ መግለጫ የሌለ ሲሆን ታማኝ የዜና አውታሮችም አልዘገቡትም። በአሁኑ ጊዜ የሀሰተኛ መረጃዎች ስርጭት በእጅጉን እየጨመረ ሲሆን ሁሉም መረጃን ከማጋራቱ በፊት ምንጩ ምንድን ነው ብሎ ማጣራት እንዳለበት ያሳየ ሁነት ሆኗል። 📹 ትክክለኛው የቲክቶክ ቪዲዮ @TikvahethMagazine
Hammasini ko'rsatish...
2.16 MB
🤣 302❤ 94👍 25😢 7👎 5🔥 1