uk
Feedback
አዲስ ነገር መረጃ

አዲስ ነገር መረጃ

Відкрити в Telegram

#አዲስ_ነገር_መረጃ #መረጃዎች_በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ Addis Ababa , Ethiopia Buy Ads : https://telega.io/?r=UbutLo2z #ለአስተያየት እና ለማስታወቂያ ስራዎች 👇👇 @Addisnegermereja_bot

Показати більше
2025 рік у цифрахsnowflakes fon
card fon
103 076
Підписники
-9224 години
-3717 днів
+21730 день
Архів дописів
Фото недоступнеДивитись в Telegram
የሰው ልጅን አስተሳሰብ ወደ ተግባር የሚቀይረው ረቂቅ ቺፕ ይፋ ተደረገ በሳይንሱ ዓለም ከፍተኛ መነቃቃትን የፈጠረውና ቢአይኤስሲ (BISC) ተብሎ የሚጠራው አዲስ የአእምሮ ውስጥ ቺፕ በታህሳስ 2025 በይፋ ለዓለም ቀርቧል። ይህ ቴክኖሎጂ ከሰው ፀጉር በበለጠ የሚቀጥን ሲሆን ያለምንም የሚታይ ገመድ ወይም የውጭ መሣሪያ የሰውን ልጅ የውስጥ ሃሳብ በቀጥታ ወደ ተግባር የመተርጎም ልዩ አቅም አለው። በኔቸር ኤሌክትሮኒክስ (Nature Electronics) ላይ የወጣው ይሄው ጥናት እንደሚያመለክተው መሣሪያው በአእምሮ እና በኮምፒውተር መካከል ያለውን ግንኙነት እጅግ ፈጣንና ስውር በሆነ መንገድ ያከናውናል። ቺፑ በአእምሮ ውስጥ የሚፈጠሩ የኤሌክትሪክ ምልክቶችን በሰው ሰራሽ አስተውሎት በመታገዝ ወደ እንቅስቃሴ የሚቀይር ሲሆን ይህም በተለይ አካል ጉዳተኞች በሃሳባቸው ብቻ የተለያዩ መሣሪያዎችን እንዲቆጣጠሩ ያስችላቸዋል። ከቀድሞዎቹ ተመሳሳይ ቴክኖሎጂዎች በተለየ መልኩ ይህ ቺፕ በራስ ቅል ላይ ምንም ዓይነት ትልቅ ቀዳዳ ወይም ግዙፍ ሃርድዌር የማይጠይቅ በመሆኑ የቴክኖሎጂውን ስውርነትና ምቾት ወደ ላቀ ደረጃ አሳድጎታል። መረጃዎችን በከፍተኛ ፍጥነትና በገመድ አልባ ዘዴ ወደ ውጭ የሚያስተላልፈው ይህ ግኝት በሰው ልጅ እና በዲጂታል ዓለም መካከል ያለውን ልዩነት የሚያጠብ ታላቅ የፈጠራ ውጤት ተብሎ ተመዝግቧል። @seledadotio @seledadotio
Показати все...
31😢 16🤔 5🤣 5
Фото недоступнеДивитись в Telegram
መረጃ‼️ በቲክቶክ የፈጠራ ስራዎች እና በባህል ጥበቃ ዙሪያ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የተሰጠ ማብራሪያ‼️ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቲክቶክ ማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ዙሪያ በሰጡት አዲስ ማብራሪያ፣ ወጣቶች ቴክኖሎጂውን ለፈጠራ ስራዎችና ለኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት እንዲያውሉት መንግስት ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታወቁ። ይሁን እንጂ፣ ይህ ነፃነት * የሀገሪቱን ባህል፣ * ወግና * እሴቶች በጣሰ መልኩ መሆን እንደሌለበት በጥብቅ አሳስበዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው፤ ወጣቶች ከውጭው ዓለም የሚመጡ ተጽዕኖዎችን ሲቀበሉ "ጠቃሚውን ብቻ" በመለየት መሆን እንዳለበት ጠቁመው፣ ከኢትዮጵያ ስርአት ውጪ የሚንቀሳቀሱ አካላት ላይ "መመከርና መገሰጽ" አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል። ቀጣዩ ትውልድ ሊታሰብበት ይገባል፤ መልካሙን ብቻ ማሳየት የሁላችንም ኃላፊነት ነው" ሲሉም ተናግረዋል። @sheger_press @sheger_press
Показати все...
61🤪 26🔥 8
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ግብፅ ከኢትዮጵያ ጋር 'ምንም ችግር' የለባትም፤ የምትፈልገው በሕዳሴ ግድብ ላይ ሕጋዊ አስገዳጅ ስምምነት ብቻ ነው – አብደል ፈታህ ኤል-ሲሲ የግብፁ ፕሬዝዳንት ይህንን የተናገሩት፣ በሁለተኛው የሩሲያ-አፍሪካ አጋርነት ፎረም የሚኒስትሮች ጉባኤ ከተሳተፉ የአፍሪካ ልዑካን ጋር ባደረጉት ውይይት ነው። ከኢትዮጵያ ጋር ልዩነቶች ቢኖሩም "ግብፅ በጭራሽ ዛቻ ሰንዝራ አታውቅም" ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ አለመግባባቶች በውይይት እና በፖለቲካዊ መፍትሄዎች መፈታት አለባቸው ብለዋል ሲል የሀገሪቱ ሚዲያ ዘግቧል። እሳቸው ይህን ይበሉ እንጂ፣ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሕዳር ወር መጨረሻ ባወጣው መግለጫ፣ ግብጽ የ21ኛውን ክፍለ ዘመን እውነታ ያልተረዱ ማስፈራሪያዎችና ዛቻዎች ኢትዮጵያ ላይ እያቀረበች ነው ሲል ከሷል፡፡ ሚኒስቴሩ "... ባለሥልጣናቱ (የግብጽ) ትኩረቱን በኢትዮጵያ ላይ ብቻ ያልተገደበ የአፍሪካ ቀንድን የማተራመስ ዘመቻ እያካሄዱ ነው.... ኢትዮጵያን በፍጹም ሊያስፈራራት ያልቻለውን ይህን ያረጀ አሠራር የምንሰናበትበት ጊዜ አሁን ነው" ብሏል፡፡ @seledadotio @seledadotio
Показати все...
26🤣 12👍 2😍 2
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ዛሬ እና ነገ የሚደረገው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የደሴ በረራ ተቋረጠ‼️ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአሁኑ ሰዓት በደሴ እና አካባቢዋ ባለው ለበረራ አመቺ ያልሆነ የአየር ጠባይ ምክንያት፤ ዛሬ እሑድ ታኅሣሥ 12/2018 እና ነገ ሰኞ ወደ ከተማዋ የሚያደርገውን በረራ ለማቋረጥ መገደዱን ለመንገደኞች አሳውቋል። አየር መንገዱ ከሚቲዎሮሎጂ በሚደርሰው መረጃ መሠረት የአየር ጠባዩ እንደተስተካከለ በረራዎቹ ወደመደበኛ አገልግሎታቸው የሚመለሱበት ጊዜ ይገለጻል ብሏል። @seledadotio @seledadotio
Показати все...
15🤔 7👍 6
ቻይና የወሊድ የህክምና ወጪዎችን ሙሉ በሙሉ በነጻ ልታደርግ መሆኑ ተገለጸ የቻይና መንግስት በሀገሪቱ በከፍተኛ ሁኔታ እየቀነሰ የመጣውን የህዝብ ቁጥር ለመታደግ እና የውልደት ምጣኔን ለማሳደግ በማለም ከመጪው 2026 የፈረንጆቹ ዓመት ጀምሮ ማንኛውም ከወሊድ ጋር የተያያዘ የህክምና ወጪ በመንግስት እንዲሸፈን መወሰኑን አስታውቋል። ይህ አዲስ መመሪያ ከቅድመ ወሊድ ምርመራ ጀምሮ እስከ ወሊድ ድረስ ያሉ ማናቸውንም የህክምና አገልግሎቶች ያካተተ ሲሆን ወላጆች ከኪሳቸው ምንም አይነት ክፍያ እንዳይከፍሉ ለማድረግ ያለመ መሆኑ ተገልጿል። ቻይና በአሁኑ ወቅት የ1.416 ቢሊዮን ህዝብ ባለቤት ብትሆንም በህዝብ ብዛት በህንድ ተበልጣ የዓለማችን ሁለተኛዋ ሀገር ሆና ትገኛለች። የሀገሪቱ የህዝብ ቁጥር ከ2022 ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ማሽቆልቆል የጀመረ ሲሆን ይህ አዝማሚያ እስከ 2025 ድረስ ቀጥሎ ታይቷል። ለዚህ የህዝብ ቁጥር መቀነስ ዋነኛ ምክንያቶች ናቸው ተብለው የሚጠቀሱት ለበርካታ አስርት ዓመታት ተግባራዊ የነበረው የአንድ ልጅ ብቻ ፖሊሲ፣ የከተማ መስፋፋት እና የልጆች ማሳደጊያ ወጪ በከፍተኛ ሁኔታ መናር ናቸው። መንግስት የወሊድ ወጪን ሙሉ በሙሉ በነጻ ለማድረግ የወሰነውን እርምጃ ተከትሎም ከጃንዋሪ 2026 ጀምሮ በእርግዝና መከላከያ ቁሶች ላይ የ13 በመቶ ታክስ ለመጣል ማቀዱ ተሰምቷል። ቤጂንግ ይህንን ውሳኔ ያስተላለፈችው ወደፊት ሊያጋጥማት የሚችለውን የሰው ኃይል እጥረት ለመከላከል እና የኢኮኖሚ ጥንካሬዋን ለማስቀጠል እንደሆነ የዘርፉ ባለሙያዎች እየገለጹ ይገኛሉ። @seledadotio @seledadotio
Показати все...
31
አለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት ማህበር (IATA) የወጣው አዲስ መረጃ እንደሚያመለክተው፣ በተለያዩ አገራት ወደ ውጭ መላክ ሳይቻል የተያዘው የአየር መንገዶች የገንዘብ መጠን አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል። በተለይም በኢትዮጵያ እና በኤርትራ ያለው የገንዘብ መጠን መጨመሩን ሪፖርቱ ጠቁሟል። በተቋሙ መረጃ መሠረት፣ በኢትዮጵያ ወደ ውጭ ሳይላክ የቆየው የገንዘብ መጠን 54 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ደርሷል። ይህም ባለፈው ዓመት ጥቅምት 2024 ላይ ከነበረበት 43 ሚሊዮን ዶላር የ11 ሚሊዮን ዶላር ጭማሪ አሳይቷል። በጎረቤት ሀገር ኤርትራ በኩል የተያዘው የገንዘብ መጠን ደግሞ 78 ሚሊዮን ዶላር የደረሰ ሲሆን፣ ይህም አገሪቱን በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ገንዘብ ከያዙ ሀገራት 6ኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧታል። ኢትዮጵያ በ2024 አጋማሽ ላይ የብርን ዋጋ በገበያ እንዲወሰን ማድረጓን ተከትሎ፣ የተያዘው ገንዘብ ከ149 ሚሊዮን ዶላር ወደ 43 ሚሊዮን ዶላር ዝቅ ብሎ የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ላይ አሃዙ በድጋሚ ማደግ መጀመሩ ተመልክቷል። በዓለም ዙሪያ በድምሩ 1.2 ቢሊዮን ዶላር የተከማቸ ሲሆን፣ 89 በመቶው የሚገኘው በሚከተሉት 10 አገራት ውስጥ ነው ። በተለይ በቀዳሚነት አልጄሪያ 307 ሚሊዮን ዶላር ፣ ሞዛምቢክ 91 ሚሊዮን ዶላር ኤርትራ ደግሞ 78 ሚሊዮን ዶላር በስምንተኛ ደረጃ ላይ የምትገኘዉ ኢትዮጵያ ደግሞ 54 ሚሊዮን ዶላር መድረሱ ተነግሯል። Via Capital Newspaper @Addis_News @Addis_News
Показати все...
12🤪 3
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ዛሬ በመላው ዓለም የአጭር ሴቶች ቀን እልል ብሎ እየተከበረ ነው! ይህ ቀን አጭርነታቸውን በኩራት እና በልዩ ውበታቸው የሚያከብሩበት ልዩ አጋጣሚ ነው። ለውብ እና ደማቅ አጫጭር ሴቶች ሁሉ፣እንኳን ለዚህ ልዩ የኩራት እና የደስታ ቀን በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ እንላለን! በአጭርነታችሁ ኩሩ፣ ውበታችሁም ልዩ ነው! የምታቋትን አጭር ሴት " Mention " እያደረጋችሁ እንኳን አደረሳችሁ በሏችሁ መልካም በዓል @seledadotio @seledadotio
Показати все...
🤪 35 26🤣 6💯 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
በአሜሪካ አንዲት ሴት በልጆቿ አስተዳደግ እና በቀለብ ክርክር ምክንያት ሁለቱን የቀድሞ ባሎቿን በአንድ ቀን ገደለች ኪቢቲኤክስ ሰሞኑ እንደዘገበው ​በአሜሪካ ፍሎሪዳ ግዛት የምትኖረው የ54 ዓመቷ ሱዛን አቫሎን  ሁለቱን የቀድሞ ባሎቿን በአንድ ቀን በመግደሏ በቁጥጥር ስር ውላለች። ከሁለቱ የቀድሞ ትዳሮቿ አምስት ልጆች ያሏት አቫሎን፣ ከቀድሞ ባሎቿ ጋር በልጆች አስተዳደግ እና በቀለብ ክፍያ ዙሪያ ክርክር ነበራት ​በዚህም መሰረት፣ አቫሎን ልጆቿን ለሚያሳድገው የቀድሞ ባሏ መክፈል ከነበረባት 4,000 ዶላር ገደማ የቀለብ ዕዳ ውስጥ የተወሰነውን ባለመክፈሏ ምክንያት የመንጃ ፈቃዷ ሊሰረዝ እንደሚችል ስጋት ገብቷት ነበር። ከቀድሞ ባሎቿ ጋር መስማማት ያቃታት አቫሎን፣ በመጀመሪያ ታምፓ ውስጥ የሚኖረውን የቀድሞ ባሏን  በጥይት ተኩሳ ገድላለች። ​በዚያው ዕለት ከሰዓት በኋላ ደግሞ ብሬደንተን  የሚኖረው ሌላኛው የቀድሞ ባሏ ቤት ሄደች። ከምግብ ቤት ምግብ ይዛ በመምጣት በሩን እንዲከፍትላት ጠየቀችው። በሩን ሲከፍትላትም ተኩሳ አቆሰለችው፤ እሱም ሆስፒታል ከገባ በኋላ ህይወቱ አለፈ። ፖሊሶች ስለ ቀድሞ ባሏ ሊያነጋግሯት ሲመጡ "የትኛውን የቀድሞ ባሌን?" ስትል ጠየቀች። ፖሊሶቹ በወቅቱ የሚያውቁት ስለ ብሬደንተኑ ግድያ ብቻ ነበር። አቫሎን ይህን ጥያቄ ካነሳች በኋላ ፖሊሶች በታምፓ የሚገኘውን የሌላኛውን ባሏን አድራሻ ሲፈልጉ እሱም መገደሉን አረጋገጡ። Fidel post @Addis_News @Addis_News
Показати все...
20🤣 7😢 3
01:08
Відео недоступнеДивитись в Telegram
👉 ከ8 በላይ ሳይቶችን ገንብቶ ያስረከበው ቴምር ፕሮፐርቲ አሁንም በድጋሜ አዳዲስ ሳይቶችን ለሽያጭ አቅርቧል ። 📍 ሳር ቤት #በ35%ቅናሽ! (በ100% ክፍያ) 👉 ባለ 2 መኝታ = 81ካሬ = 5.7ሚ 👉 ባለ 2 መኝታ = 106ካሬ = 7.9ሚ 👉 ባለ 3 መኝታ = 139ካሬ = 10.3ሚ 👉 ባለ 3 መኝታ = 153ካሬ = 11.4ሚ #በ20% ቅድመ ክፍያ (በግንባታ ሂደት ለሚከፍሉ) 👉 81ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 9.3ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (1.8ሚሊዮን) 👉 106ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 12.1ሚ                  ቅድመ ክፍያ = 20% (2.4ሚሊዮን) 👉 139ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 15.9ሚ                  ቅድመ ክፍያ = 20% (3.1ሚሊዮን) 📍 አዋሬ #በ35%ቅናሽ! (በ100% ክፍያ) 👉 ባለ 1 መኝታ = 78ካሬ = 5.5ሚሊዮን 👉 ባለ 3 መኝታ = 117ካሬ = 8.3ሚሊዮን 👉 ባለ 3 መኝታ = 137ካሬ = 9.7ሚሊዮን 👉 ባለ 3 መኝታ = 145ካሬ = 10.3ሚሊዮን #በ20% ቅድመ ክፍያ (በግንባታ ሂደት ለሚከፍሉ) 👉 78ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 8.5ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (1.7ሚሊዮን) 👉 135ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 14.8ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (2.9ሚሊዮን) 👉 157ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 17.2ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (3.4ሚሊዮን) ⩩ ቀሪውን 80%፤ በግንባታ ሂደት፤ ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት። ⩩ 30% እና ከዚያ በላይ ለሚከፍሉ፤ ከከፈሉት ላይ ከ15 -25% ቅናሽ አዘጋጅተናል። ለበለጠ መረጃ ;- 0940464607 0994003949
Показати все...
25.16 MB
4👏 2
🎯🎯 ያልተኖረ 🎯🎯 አዲስ ፊልም   ታህሳስ 13 ሰኞ በታላቁ ብሔራዊ ቴአትር አዳራሽ ከ ቀኑ 11:30 ጀምሮ በቀይ ምንጣፍ ስነ-ስርዓት ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ ሚዲያዎች እና የኪነ - ጥበብ ባለሙያዎች በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ይመረቃል። ታህሳስ 17፣18፣19 ደግሞ በተመረጡ ሲኒማ ቤቶች በታላቅ ድምቀት ይመረቃል። ፊልሙን ያቀረበው ናዲ መልቲ ሚዲያ በቅርቡ ሌሎችም ትላልቅ ፊልሞችን እንደሚያቀርብ ገልፅዋል #ያልተኖረ
Показати все...
4
1
ብፁዕ አቡነ ያሬድ ከምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ተነሱ። ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ  ሀገረ ስብከቱን እንዲመሩ ተመድበዋል። ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከትን እስከ ግንቦት የቅዱስ ሲኖዶስ ርክበ ካህናት ጉባኤ ድረስ ደርበው እንዲመሩ በቋሚ ሲኖዶስ ተመደቡ። ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ከሚመሩት ሀገረ ስብከት በተጨማሪ የምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከትን እስከ ግንቦት 2018 ዓ/ም የቅዱስ ሲኖዶስ ርክበ ካህናት ጉባኤ ድረስ ደርበው እየመሩ እንዲቆዩ በቋሚ ሲኖዶስ ተወስኖ በቅዱስ ፓትርያርኩ በተጻፈ ደብዳቤ ተመድበዋል። ቋሚ ሲኖዶስ በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ከሚገኙ ካህናት፣ አባ ገዳዎች፣ሀደ ሲንቄዎች፣ ወጣቶችና ምዕመናን የቀረበለትን ተደጋጋሚ አቤቱታ ሲቀርብለት ነበር። ይህን መነሻ በማድረግ አጣሪ ልዑክ መድቦ ችግሩ በዝርዝር ተጠንቶ እንዲቀርብለት ካደረገ በኋላ ሪፖርቱን መነሻ በማድረግ ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት ብፁዕ አቡነ ያሬድ ከምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ተነስተው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርሰቲያን የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስነት ሥራቸውን እያከናወኑ እስከ ግንቦት የቅዱስ ሲኖዶስ ርክበ ካህናት ጉባኤ እንዲቆዩ ውሳኔ አስተላልፏል። የቅዱስ ሲኖስ ምልዐተ ጉባኤ ጥቅምት 2018 ዓ.ም ባደረገደው ጉባኤ  ቋሚ ሲኖዶስ የተከሰተውን ችግር በመመርመር መፍትሔ እንዲሰጥ ውሳኔ ማሰተላለፉ ይታወሳል። Tikbah @Addisinsider_ETH @Addisinsider_ETH
Показати все...
18🙏 3
አለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት ማህበር (IATA) የወጣው አዲስ መረጃ እንደሚያመለክተው፣ በተለያዩ አገራት ወደ ውጭ መላክ ሳይቻል የተያዘው የአየር መንገዶች የገንዘብ መጠን አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል። በተለይም በኢትዮጵያ እና በኤርትራ ያለው የገንዘብ መጠን መጨመሩን ሪፖርቱ ጠቁሟል። በተቋሙ መረጃ መሠረት፣ በኢትዮጵያ ወደ ውጭ ሳይላክ የቆየው የገንዘብ መጠን 54 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ደርሷል። ይህም ባለፈው ዓመት ጥቅምት 2024 ላይ ከነበረበት 43 ሚሊዮን ዶላር የ11 ሚሊዮን ዶላር ጭማሪ አሳይቷል። በጎረቤት ሀገር ኤርትራ በኩል የተያዘው የገንዘብ መጠን ደግሞ 78 ሚሊዮን ዶላር የደረሰ ሲሆን፣ ይህም አገሪቱን በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ገንዘብ ከያዙ ሀገራት 6ኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧታል። ኢትዮጵያ በ2024 አጋማሽ ላይ የብርን ዋጋ በገበያ እንዲወሰን ማድረጓን ተከትሎ፣ የተያዘው ገንዘብ ከ149 ሚሊዮን ዶላር ወደ 43 ሚሊዮን ዶላር ዝቅ ብሎ የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ላይ አሃዙ በድጋሚ ማደግ መጀመሩ ተመልክቷል። በዓለም ዙሪያ በድምሩ 1.2 ቢሊዮን ዶላር የተከማቸ ሲሆን፣ 89 በመቶው የሚገኘው በሚከተሉት 10 አገራት ውስጥ ነው ። በተለይ በቀዳሚነት አልጄሪያ 307 ሚሊዮን ዶላር ፣ ሞዛምቢክ 91 ሚሊዮን ዶላር ኤርትራ ደግሞ 78 ሚሊዮን ዶላር በስምንተኛ ደረጃ ላይ የምትገኘዉ ኢትዮጵያ ደግሞ 54 ሚሊዮን ዶላር መድረሱ ተነግሯል። Via Capital Newspaper @Addis_News @Addis_News
Показати все...
8
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ሞሮኮ የአፍሪካ ዋንጫን ታሳካ ይሆን ? የ 2025 የአፍሪካ ዋንጫ ዛሬ ምሽት በደማቅ ሁኔታ ጅማሮውን በሞሮኮ ራባት የሚያደርግ ይሆናል። አዘጋጇ ሀገር ሞሮኮ ለዋንጫው ቅድመ ግምት ከተሰጣት ብሔራዊ ቡድኖች በቀዳሚነት ትገኛለች። በደጋፊዎቻቸው ፊታ የሚጫወቱት የአትላስ አንበሶቹ የኮከባቸው የአሽራፍ ሀኪሚ ለጨዋታ መድረስ ብቻ አሳስቧቸው ይገኛል። አሽራፍ ሀኪሚ ስለ ጉዳቱ ሲናገር “ ለሀገሬ ለመጫወት ምንም ነገር እንደማደርግ ለአሰልጣኛችን ነገሬዋለሁ “ ብሏል። አሰልጣኝ ዋሊድ ሬግራጉይ በበኩላቸው “ ለሀገሩ ሲል መስዋትነት ከፍሏል “ ያሉ ሲሆን “ እሱ ተምሳሌት የሚሆን ተጫዋች ነው “ ሲሉ አወድሰውታል። አሽራፍ ሀኪሚ በምሽቱ ጨዋታ የመሰለፉ ነገር አጠራጣሪ ሲሆን አሰልጣኙ “ ውሳኔው የኔ ነው “ የሚል ምላሸን ሰጥተዋል። tikvah @Addis_News @Addis_News
Показати все...
11
00:37
Відео недоступнеДивитись в Telegram
🌟🌟ታላቅ የበዓል ቅናሽ በካሬ 78,000 ብር ✅እንዲሁም ሙሉ ክፍያ ለሚከፊል በካሬ 54,800 🔷 በ10 % ቅድመ ክፍያ 🔷 50 %  የባንክ ብድር  የተመቻቸለት 📍Location እንግሊዝ ኢንባሲ አጠገብ  ውብ እይታ (Top View) ያላቸው ቤቶች በሽያጭ ላይ እንገኛለን 👉ከባለ 2 መኝታ- ባለ4 መኝታ ✅ ህንፃው ላይ ያሉ ተጨማሪ አገልግሎትች   ‎👉5 ሰፋፊ ሊፍት /elevator   ‎👉የቆሻሻ መጣያ/garbage chute   👉አውቶማቲክ ጀኔረተር/ automatic       generator    ‎👉ሰገነት/terrace    ‎👉የመኪና ማቆምያ/car parking     👉 ጂም , እስፖ    👉 የዋና ገንዳ    👉 የልጆች መጫወታ ✨ባለ 2 መኝታ ‎           138     ካሬ ‎           157.3   ካሬ ‎           163.6   ካሬ ‎ ✨ባለ 3 መኝታ            152.4  ካሬ            158.1  ካሬ ‎           187.6  ካሬ            211.5  ካሬ ‎ ✨ባለ 4 መኝታ            240.7 ካሬ ‎           258.4 ካሬ ‎        📞 ለበለጠ መረጃ ይደውሉ ‎                 0973559591                  0919489575                  Telegram -@Homef17
Показати все...
7.49 MB
2
የደቡብ አፍሪካው አስከፊ ተኩስና እልቂት በደቡብ አፍሪካ አንድ መጠጥ ቤት ላይ በተከፈተ ጅምላ ተኩስ የዘጠኝ ሰዎች ህይዎት ተቀጠፈ። የዜጎች ህይዎት ከማለፉም ባሻገር አስር ሰዎች ቆስለዋል ሲል የአገሪቱ ፖሊስ አሰአወቋል። በጆሀንስበርግ የተፈፀመው ጥቃት የአገሪቱን ፀጥታ ጥርጣሬ ውስጥ ያስገባ ነውም ተብሏል። 12 ተጠርጣሪዎች መኪና ላይ ሆነው የፈፀሙት ጥቃት ሲሆን ወንጀለኞችን ለመያዝ ፖሊስ ስራ ላይ መሆኑንም እወቁልኝ ብሏል። በቢከርሳድ ንጋቱን የተፈፀመው ከባድ ጥቃት ዜጎች በጎዳና ላይ የድረሱልን ጥሪ ያሰሙበት አሰፈሪ ክስተትም ሆኗል። ማንነታቸው ያልታወቀ ሰዎች የጅምላ ተኩሱን መከፈታቸውን ኤስ ኤ ቢ ሲ ዘግቧል። በስፍራው የፀጥታ ሀይሎች መድረሳቸው ይፋ ቢሆንም የተጠርጣሪዎቹን አድራሻ እሰከአሁን ማግኘት አልተቻለም ሲል አልጀዚራ ዘግባል። @Addisinsider_ETH @Addisinsider_ETH
Показати все...
7💔 6😢 2😍 1
እግዚአብሔር የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልን በነገዱ ውስጥ በመላእክት ሁሉ ላይ በብዙ ክብር ሾመው፡፡ ቅዱስ ሚካኤል በዚህ ሁሉ ልዕልና ላይ ትሕትናን ደርቦ የያዘ በጸሎቱ ተማጽኖ በተራዳኢነት አምኖ ለሚለምነው ሁሉ ፈጥኖ በመድረስ ከአጋንንት ሠራዊተ ተንኰል የሚያድን ነው፡፡ ሚካኤል የሥሙ ትርጓሜ በዕብራይስጥ “ማንነው እንደ እግዚአብሔር?” ማለት ነው፡፡ በክርስትና በአይሁድ፣ እንዲሁም በመላዕክት አማላጅነት በሚያምኑ ሃይማኖቶች የመላዕክት ሁሉ አለቃ ተብሎ ይጠራል፡፡ ይህም የከበረ መልአክ ክብር ይገባውና በጌታችን ፊት ስለ ሰው ልጆችና ስለ ፍጥረትም ሁሉ ይለምናል፤ ይማልዳልም፡፡ የቅዱስ ሚካኤል ተአምራቱ ብዙዎች ናቸው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ለቅዱስ ሚካኤል የተሰጠውን ክብርና ባለሟልነት እንዲሁም የሠራቸውን ሥራዎች በስፋት እንመለከታለን፡፡ በኢያሱ 5÷13 እንዲህ ይላል፡፡ “እንዲህም ሆነ ኢያሱ በኢያሪኮ አጠገብ ሳለ ዓይኑን አንሥቶ ተመለከተ፡፡ እነሆም የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ የያዘ ሰው በፊቱ ቆሞ ነበር፡፡ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ ከእኛ ወገን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህን አለው፡፡ እርሱም አይደለሁም እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆኜ አሁን መጥቻለሁ አለ፡፡ ኢያሱም ወደ ምድር በግምባሩ ተደፍቶ ሰገደ፡፡ ጌታዬ ለባሪያው የሚነግረው ምንድን ነው አለው፡፡ የእግዚአብሔርም ሠራዊት አለቃም ኢያሱን አንተ የቆምህበት ሥፍራ የተቀደሰ ነውና ጫማህን በፊቱ አውልቅ አለው፡፡ ኢያሱም እንዲሁ አደረገ” ይላል፡፡ ኢያሱ ከኢያሪኮ ጀምሮ ታላላቅ አሕዛብን አጥፍቶ እግዚአብሔር ለአብርሃም፣ ለይስሐቅ፣ ለያዕቆብ የማለላቸውን የተስፋይቱን ምድር ለልጆቻቸው ያወረሳቸው በዚህ የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ ይዞ በተገለጸለት የእስራኤል መሪ በቅዱስ ሚካኤል እገዛ ነው፡፡ መልአኩ በሰው አምሳል ስለተገለጸለት አላወቀውም ነበር፡፡ ከቃሉ እንደምንረዳው ከራሱ ወገን ወይም ከጠላቶቹ ወገን የሆነ አንድ ወታደር መስሎት ነበር፡፡ ያነጋገረውም ያለ ፍርሃት ያለ ጭንቀት ያለድንጋጤ ወታደሮቹን እንደሚያነጋግር ዘና ብሎ ነው፡፡ ሆኖም “ከወገኖችህ ወይም ከጠላቶችህ አይደለሁም እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆኜ አሁን መጥቻለሁ” ሲለው ኢያሱ በፊቱ የቆመው ከሙሴ ሳይለይ እስራኤልን የሚጠብቅ የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ሚካኤል መሆኑን ሲረዳ ለመልአኩ ክብር መስጠት ስለሚገባ የአክብሮት ስግደት ሰገደለት፤ “ጌታዬ ለባሪያው የሚነግረው ምንድነው” በማለት በትህትና ጠየቀ፡፡ ጌታዬ ማለቱ የእግዚአብሔርን ክብር ለፍጡር መስጠቱ አይደለም፣ መላእክት የጸጋ ጌቶች ስለሚባሉ እንጂ፡፡ ኢያሱ መልአኩን ጌታዬ ብሎ ከጠራው እኛም ጌታዬ፤ ቅዱስ ሚካኤል ለኔ ለባሪያህ ጸልይልኝ መጥተህ አድነኝ በማለት የአክብሮት የጸጋ ስግደት በመስገድ ብንለምነው፣ ብንታዘዘው ከመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት አልወጣንም፡፡ መላእክትን ማክበርና መታዘዝ እንደሚገባ እግዚአብሔርም ነግሮናል፡፡ በዘጸ.23÷20-22 “በመንገድህ ይጠብቅህ ዘንድ ወዳዘጋጀሁትም ሥፍራ ያገባህ ዘንድ እነሆ እኔ መልአክህን በፊትህ እሰዳለሁ፤ በፊቱ ተጠንቀቁ፤ ቃሉንም አድምጡ፤ ስሜም በእርሱ ስለሆነ ኃጢአት ብትሠሩ ይቅር አይልምና አታስመርሩት፤ አንተ ግን ቃሉን ብትሰማ፣ ያልሁህንም ሁሉ ብታደርግ፣ ጠላቶችህን እጣላቸዋለሁ፣ የሚያስጨንቁህንም አስጨንቃቸዋለሁ፣ መልአኬ በፊትህ ይሄዳል” በማለት ለሙሴ ተናግሯል፡፡ ይህ ቃል ለሙሴና ለሕዝቡ ብቻ ተነግሮ ያበቃ ሳይሆን ዛሬም ያለ ወደፊትም የሚቀጥል ነው፡፡ ገዳማውያንም ይህን ቃል ታምነው ሌሊትና ቀን ሚካኤል ሆይ አማልደን ይሉታል፡፡ ከጸሎታቸው በረከት እንድንካፈል ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡ ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ 1000442598391 ወይም አቢሲኒያ ባንክ 141029444 ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957
Показати все...
46
Фото недоступнеДивитись в Telegram
30
Фото недоступнеДивитись в Telegram