uk
Feedback
ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

Відкрити в Telegram

The best fiction is far more true than any journalism 📢 ተዓማኒ የመረጃ ምንጭ ፤ ለሙያው ስነምግባር ተገዢ በሆኑ ጋዜጠኞች ብቻ 👉 በፌስቡክ ገፆቻችን https://www.facebook.com/simon.dereje.56 👉 https://www.facebook.com/mik0Man

Показати більше
2025 рік у цифрахsnowflakes fon
card fon
44 133
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
-21530 день
Архів дописів
የቡኢ ከተማ ነዋሪዎች ከ30 ዓመታት ጥያቄ  በኋላ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ሆኑ በምስራቅ ጉራጌ ዞን በቡኢ ከተማ አስተዳደር በነጌሳ ቀበሌ ለበርካታ ዓመታት የህዝብ ጥያቄ የነበረው  የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ስራ ተጠናቆ  አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታውቋል።በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የምስራቅ ጉራጌ ዞን ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ መሰለ ጫካ  የመብራት ሀይል አቅርቦት የነጌሳ  ቀበሌ ህዝብ የረጅም ጊዜ  ጥያቄ ስለነበር ምላሽ በማግኘቱ   እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል። የነጌሳ ቀበሌ የመብራት ሀይል አቅርቦቱ መንግስት በአሁኑ ሰዓት የጀመረውን የገጠር ትራንስፎርሜሽን ስራ ለማሳካት   ወሳኝ ሚና የሚኖረው መሆኑን አመላክተዋል።በቀጣይም  ከህዝቡ ጋር በመቀናጀት የተጀመሩ ልማቶች የበለጠ እንዲሰፋ እንደሚሰራ እና ማህበረሰቡም  የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።ቀበሌው በከተማ አስተዳደሩ ስር ሲካለል የህዝቡ ጥያቄ የነበረው የመብራት ሀይል አቅርቦት እንደነበረ እና የከተማ አስተዳደሩም ቃል በገባው መሠረት የህዝቡን ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ ማድረጉ ተነግሯል። የቡኢ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ በለጠ ጫካ  የመብራት ሀይል አቅርቦቱ የቀበሌው ህዝብ ለ30 ዓመት ሲጠይቀው የነበረ እንደሆነ አንስተዋል። የከተማ አስተዳደሩ  ለመብራት ሀይል አቅርቦት ሙሉ ወጪውን  5.5 ሚሊየን ብር በማውጣት 3.2 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ዝርጋታ በማከናወን  የህዝቡን ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ ያደረገ መሆኑን ተናግረዋል።ከተማው ሲሰፋ እድል እንጂ ስጋት በማይሆን መንገድ የከተማውን ፕላን ተከትሎ ቅድሚያ የአርሶ አደሩን  መብት ባረጋገጠ መልኩ እንዲለማ ታቅዶ ይሰራል  ብለዋል። የቀበሌው ነዋሪዎችም የረጅም ጊዜ ጥያቄያቸው የነበረውን የመብራት ሀይል አቅርቦት ምላሽ በማግኘቱ በጣም ደስተኛ እንደሆኑ ተናግረዋል። ምህረት ታደሰ #ዳጉ_ጆርናል
Показати все...
31😁 11😭 3
የቡኢ ከተማ ነዋሪዎች ከ30 ዓመታት ጥያቄ  በኋላ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ሆኑ በምስራቅ ጉራጌ ዞን በቡኢ ከተማ አስተዳደር በነጌሳ ቀበሌ ለበርካታ ዓመታት የህዝብ ጥያቄ የነበረው  የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ስራ ተጠናቆ  አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታውቋል።በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የምስራቅ ጉራጌ ዞን ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ መሰለ ጫካ  የመብራት ሀይል አቅርቦት የነጌሳ  ቀበሌ ህዝብ የረጅም ጊዜ  ጥያቄ ስለነበር ምላሽ በማግኘቱ   እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል። የነጌሳ ቀበሌ የመብራት ሀይል አቅርቦቱ መንግስት በአሁኑ ሰዓት የጀመረውን የገጠር ትራንስፎርሜሽን ስራ ለማሳካት   ወሳኝ ሚና የሚኖረው መሆኑን አመላክተዋል።በቀጣይም  ከህዝቡ ጋር በመቀናጀት የተጀመሩ ልማቶች የበለጠ እንዲሰፋ እንደሚሰራ እና ማህበረሰቡም  የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።ቀበሌው በከተማ አስተዳደሩ ስር ሲካለል የህዝቡ ጥያቄ የነበረው የመብራት ሀይል አቅርቦት እንደነበረ እና የከተማ አስተዳደሩም ቃል በገባው መሠረት የህዝቡን ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ ማድረጉ ተነግሯል። የቡኢ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ በለጠ ጫካ  የመብራት ሀይል አቅርቦቱ የቀበሌው ህዝብ ለ30 ዓመት ሲጠይቀው የነበረ እንደሆነ አንስተዋል። የከተማ አስተዳደሩ  ለመብራት ሀይል አቅርቦት ሙሉ ወጪውን  5.5 ሚሊየን ብር በማውጣት 3.2 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ዝርጋታ በማከናወን  የህዝቡን ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ ያደረገ መሆኑን ተናግረዋል።ከተማው ሲሰፋ እድል እንጂ ስጋት በማይሆን መንገድ የከተማውን ፕላን ተከትሎ ቅድሚያ የአርሶ አደሩን  መብት ባረጋገጠ መልኩ እንዲለማ ታቅዶ ይሰራል  ብለዋል። የቀበሌው ነዋሪዎችም የረጅም ጊዜ ጥያቄያቸው የነበረውን የመብራት ሀይል አቅርቦት ምላሽ በማግኘቱ በጣም ደስተኛ እንደሆኑ ተናግረዋል። ምህረት ታደሰ #ዳጉ_ጆርናል
Показати все...
6
በታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ላይ በደረቅ ቆሻሻ መልሶ መጠቀምና ዑደት ስራ ላይ የተሰማሩ ማህበራት ከፍተኛ ቆሻሻን በመሰብሰ ከፍተኛ ገቢ አገኙ የማህበራቱ ጥረት ለከተማው ጽዳት ትልቅ ድጋፍ ሲሆን፣ የስፖርቱን ደስታ ከአካባቢ ንጽህና እና ከገቢ ማስገኛነት ጋር ባገናኘ መልኩ ትልቅ ትምህርት መሰጠቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቢሮ አስታውቋል። ብዙ የሰበሰበ ብዙ አገኝ የሚለው መርህ በደማቅ ሁኔታ ሩጫው በተካሄደበት ወቅት ታዳሚዎች የተጠቀሙባቸውን ያገለገሉ የፕላስቲክ ጠርሙሶች ወዲያውኑ በመሰብሰብ ረገድ የማህበራቱ ሚና እጅግ የጎላ ነበር ተብሏል። በተለይም የውሃ ጠርሙሶችን ለመሰብሰብ ባደረጉት የተቀናጀ ጥረት፣ ከፍተኛ መጠን ያለው ቆሻሻ ወደ መልሶ ማምረቻ ግብዓትነት እንዲለወጥ አድርገዋል።ህጋዊ ባጆችን በመጠቀም በስርዓት ሲሰሩ የዋሉት እነዚህ ማህበራት፤ ከፍተኛ ገቢ በማስገኘት ለራሳቸው ብልጽግና መሰረት ከመጣልም በተጨማሪ የከተማዋ ጽዳት እንዳይጓደል እና የአካባቢ ብክለት እንዳይፈጠር በመከላከል ለአካባቢ ፅዳት ትልቅ ድርሻ ተወጥቷል። ይህ ስፖርታዊ ፌስቲቫል ትልቅ የኢኮኖሚ ዕድል መፍጠሩ ብቻ ሳይሆን፣ የደረቅ ቆሻሻን ችግር ወደ "ብልፅግና ዕድል" መቀየር እንደሚቻል በተግባር ያሳየ ስኬታማ ምሳሌ ሆኗል። ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን በአንድ ላይ የሚያሰባስብበት መድረክ መሆኑ ለፕላስቲክ መልሶ መጠቀም ስራውም ታላቅ ሽፋን በመስጠት፣ የአካባቢ ንቃተ-ህሊናን ከፍ ለማድረግ ከፍተኛ እገዛ አድርጓል። #ዳጉ_ጆርናል
Показати все...
😁 50 18👍 8
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ፑቲን ወደ ድርድር ጠረጴዛ እንዲመጡ ትራምፕ ጫና ማድረግ አለባቸው ሲሉ የቀድሞ የአሜሪካ አምባሳደር ተናገሩ በዩክሬን የቀድሞ የአሜሪካ አምባሳደር የምዕራባውያን መሪዎች በሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ላይ የበለጠ ጫና እንዲያደርጉ አሳስበዋል። አምባሳደር ዊልያም ቢ ቴይለር ፑቲን ዩክሬንን፣ አውሮፓን እና አሜሪካን "ለመጠበቅ" እየሞከሩ ነው ፤ ይህንን የሚያደርጉት ለሩሲያ ምቹ ስምምነትን ለማግኘት ነው። "ጠንክረን ከቆየን ፑቲን ወደ ጠረጴዛው እንዲመጡ ልናስገድደው እንችላለን ነገርግን ይህን አላደረግነውም" ሲሉ ለሬዲዮ 4 ቱዴይ ፕሮግራም ተናግረዋል። በሌላ በኩል በሩሲያ የቀድሞ የእንግሊዝ አምባሳደር ለዩክሬን "የደህንነት ዋስትና" ስምምነት ላይ መድረስ አስቸጋሪ እንደሚሆን አስጠንቅቀዋል። የመጀመርያው ባለ 28 ነጥብ የሰላም እቅድ ለወደፊት የሩስያ ጥቃትን ለመከላከል በምዕራባውያን የሚደገፍ ለዩክሬን የደህንነት ዋስትናዎች ይኖሩታል።ነገር ግን ዕቅዱ ዩክሬን የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃልኪዳን ኔቶ የምዕራባውያን ሀገራት ወታደራዊ ጥምረት ላለመቀላቀል ቃል እንድትገባ ያስገድዳታል። በስምዖን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
Показати все...
😁 9👍 4 1
በካርኪቭ ሩሲያ በፈፀመችው የድሮን ጥቃት አራት ሰዎችን ተገደሉ የሩስያ ወታደራዊ ኃይል እሁድ እለት በዩክሬን ካርኪቭ ላይ "ግዙፍ" ሰው አልባ አውሮፕላኖች በማሰማራት በዩክሬን ሁለተኛ ግዙፍ ከተማ በፈፀመው ጥቃት ቢያንስ አራት ሰዎች ሲገድሉ ሌሎች 12 ሰዎች ቆስለዋል። የካርኪቭ ከንቲባ ኢጆር ቴሬክሆቭ በቴሌግራም ላይ ባሰፈሩት መልዕክት ቢያንስ አራት ሰዎች ተገድለዋል ፣ አንድ ተጎጂም አካሉ ከፍርስራሹ ውስጥ ተገኝቷል ብለዋል። የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦሌህ ሲኒዬሁቦቭ እንደተናገሩት 12 ሰዎች በጥቃቱ ቆስለዋል፤ ከነዚህም መካከል የ11 እና የ12 አመት እድሜ ያላቸው ሁለቱ ታዳጊዎች ናቸው ሲሉ ተናግረዋዋ። ባለስልጣናት ከሩሲያ ድንበር 30 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በሚገኙት የከተማዋ ስድስት ወረዳዎች 15 ጥቃቶችን በአንድ ሌሊት መፈፀሙን መዝግበዋል ።በጦርነቱ መጀመሪያ ላይ ሩሲያ ካርኪቭን ለመያዝ የምታደርገውን ሙከራ ተቋቁማለች ፣ ነገር ግን ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ተደጋጋሚ ጥቃቶች ገጥሟታል። ዩናይትድ ስቴትስ እና ዩክሬን እሁድ እለት በስዊዘርላንድ ውስጥ ከተነጋገሩ በኋላ የሩሲያን ጦርነት ለማስቆም የታለመውን የተሻሻለውን የሰላም ማዕቀፍ ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል።የዩክሬን ልዑካን "አብዛኞቹን የዩክሬን ዋና ዋና ጉዳዮችን የሚያንፀባርቅ" በማለት ገና ይፋ ያልሆነውን አዲሱን የዩናይትድ ስቴትስ የሰላም ረቂቅ እቅድን ጠቅሷል። የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ኡርሱላ ፎን ደር ሌየን ማንኛውም የሰላም እቅድ የዩክሬን የአውሮፓ ህብረት አባልነትን ጨምሮ "የራሷን ዕድል የመምረጥ" መብት ማክበር አለበት ብለዋል ። በስምዖን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
Показати все...
9😢 2👎 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
የስምንት ዓመቷን ታዳጊ አታሎ በመውሰድ የመድፈር ጥቃት የፈፀመው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ በባቱ ከተማ አስተዳደር መልካ ዝዋይ ቀበሌ ውስጥ የስምንት ዓመቷን ልጅ አታሎ በመውሰድ የመድፈር ጥቃት የፈፀመው ግለሠብ በእስራት መቀጣቱን ፖሊስ አስታውቋል ።የባቱ ከተማ አስተዳደር  ፖሊስ ዋና መምርያ የሴቶችና ሕፃናት ጉዳይ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ኢንስፔክተር ረሒማ ከድር  ለብስራት ሬዲዮ እደተናገሩት ተከሳሽ ፍራንኦል አብዮት የተባለው ግለሰብ ሐምሌ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 11 ሰዓት ላይ ታዳጊዋን ነይ ማስቲካ ልግዛልሽ ብሎ ከምትጫወትበት ስፍራ አታሎ በመውሰድ የመድፈር ጥቃት እንደፈፀመባት ገልፀዋል። ተጎጂዋ ልጅም በነጋታው ሐምሌ 23 ቀን 2017 ዓ.ም  ሽንት መሽናት አቅቷት  ስትሰቃይ የተመለከቱ ቤተሰቦች ጉዳዩን ወዲያው ለምርመራ  ወደ ጤና ተቋም በመውሰድ በጤና ሲያስመረምሯት የመደፈር ወንጀል እንደተፈፀመባት ተረጋግጧል፡ተከሣሹ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዉሏል።ፖሊስ የምርመራ መዝገቡን በሕክምና እና በሌሎች ማስረጃዎች አጠናክሮ ለአቃቢ ሕግ የላከ ሲሆን አቃቢ ሕግም ከፖሊስ የቀረበውን የምርመራ መዝገብ ተመልክቶ በወንጀል ሕግ ቁጥር627 /2 እድሜያቸው ከ13 አመት በታች በሆኑ ሕፃናት ላይ የሚፈፀም የግብረ ስጋ ድፍረት በደል ክስ መስርቷል። በአቃቢ ሕግ የተመሠረተውን ክስ የተመለከተው የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ህዳር 8 ቀን 2018ዓ.ም ባስቻለው ችሎት ተከሣሽ ፍራንኦል አብዮት ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በ17 አመት እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን ኢንስፔክተር ረሒማ ከድር ጨምረው  ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ። በምህረት ታደሰ #ዳጉ_ጆርናል
Показати все...
🤬 16 7
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ሄዝቦላህ በእስራኤል ላይ የአፀፋ እርምጃ ለመውሰድ በጥሩ አቋም ላይ አይደለም ተባለ ሄዝቦላህ እስራኤል በቤሩት በወታደራዊ ሃይል ለፈፀመችው ጥቃይ እና ግድያ የአፀፋ ምላሽ ለመስጠት “ጥሩ አቋም ላይ አይደለም” ሲሉ አንድ ምሁር ተናግረዋል። በሊባኖስ አሜሪካን ዩኒቨርሲቲ ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑት ኢማድ ሳላሜይ የሊባኖስ ቡድን የአፀፋ ምላሽ ከሰጠ የእስራኤል የበቀል እርምጃ "ከባድ ሊሆን ይችላል" ብለዋል። እስራኤል እና የኔታኒያሁ የቀኝ ክንፍ መንግስት የአፀፋ ምላሽ በሂዝቦላ በኩል ተሰጥቶ የግጭቱ መባባስ እንዲፈጠር ጓጉተዋል፤ ምክንያቱ ደግሞ ይህ የግጭት መባባስ የእስራኤልን መንግስት በስልጣን ላይ እንዲቆይ ስለሚያደርግ ነው ብለዋል። "ከአሜሪካውያን ሙሉ ድጋፍ አለው እና በሊባኖስ ውስጥ ለመሳተፍ እና ምናልባትም ሊባኖስን ለመውረር ከፍተኛ ፍላጎት በሚያገኝበት ሁኔታ ላይ ነው" ሲሉ አክለዋል።በአንጻሩ የሂዝቦላህ መከላከያ ሃይል “በከባዱ ተጎድቷል” በተጨማሪም በሚጣሉበት እገዳዎች ምክንያት ተዳክሟል። ሳላሜይ እንዳሉይ “ከእንግዲህ ቀደም ሲል የነበረው ድጋፍ ወይም በሶሪያ በኩል ይጠቀምበት የነበረው የሎጂስቲክስ መስመር የለውም” ብለዋል። ለእስራኤላውያን ወታደራዊ የአፀፋ ምላሽን በመስጠት ለመበቀል ወይም ኃይሉን በድጋሚ ለማቀናጀት ጥሩ ቦታ ላይ አይደለም ሲሉ ተናግረዋል።እስራኤል በሊባኖስ ዋና ከተማ ቤይሩት ላይ በፈፀመችው የአየር ጥቃት የሂዝቦላህ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዥ ሃይተም አሊ ታባታባይን እና ሌሎች አራት ሰዎችን ገድላለች። ከፍተኛ የሂዝቦላህ ባለስልጣን የሆኑት ማህሙድ ቁምቲ የእስራኤል የጥቃት እርምጃ "ቀይ መስመር" እንዳለፈ እና የቡድኑ አመራር የአፀፋ ምላሽ ይሰጥ እንደሆነ እያሰላሰለ ነው ሲሉ ተናግረዋል። በስምዖን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
Показати все...
10😁 4👍 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ከ1ሺህ በላይ ሰዎች የአይን ብሌናቸው ለመለገስ ቃል ገቡ የኢትዮጲያ ደም እና ህብረ ህዋስ ባንክ "የዓይን ብሌን ለጋሾቻችን የሁልጊዜ ጀግኖቻችን" በሚል መሪ ቃል የሚከበረው የዘንድሮው አለም አቀፍ የዓይን ብሌን ልገሳ ወር እያከበረ ይገኛል።በ2018 ዓመት በሩብ ዓመቱ  ውስጥ 1ሺህ በላይ  ሰዎች ከህልፈታቸው በኋላም የዓይን ብሌናቸው ለመለገስ ቃል ለማስገባት ታቅዶ 1ሺህ 80 ሰዎች ቃል ማስገባት ተችሏል ሲሉ የኢትዮጲያ ደም እና ህብረ ህዋስ ባንክ  የህዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ ተወካይ አቶ ነጋ ደምሴ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል። በተጨማሪም በሩብ ዓመቱ ለ123 ሰዎች የአይን ብሌን ንቅለ ተከላ መከናወኑ ተገልጿል። የኢትዮጵያ ደምና ህብረ ህዋስ ባንክ የመጀመሪያ የሆነዉን የጅማ የአይን ብሌን ባንክ ተመርቆ ወደ ስራ መግባቱ አስታውቋል።በዚህ በህዳር ወር ውስጥ 1ሺህ 500  የሚሆኑ በጎ ፍቃድ ለጋሾች ከህልፈታቸው በኋላ የዓይን ብሌናቸውን ለመለገስ ቃል እንዲገቡ ለማድረግ ታቅዷል ሲሉ  ሀላፊው ጨምረው ለጣቢያችን ተናግረዋል። በኢትዮጰያ በአይን ብሌን ጠባሳ ምክንያት ብርሃናቸው ያጡ ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ በመሆኑ   ሰዎች ከህልፈታቸው በኋላ የአይን ብሌናቸውን ቢለግሱ ጊዜ የማይወስድ ፣የቀብር ስነርዓትን የማስተጓጉል በመሆኑ ቃል ሊገቡ ይገባል ሲሉ የዓይን ባንኩ ጥሪ አቅርቧል፡፡ነ የዓይን ባንኩ ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ ለ3ሺህ 700 ሰዎች የዓይን ብሌን ንቅለ ተከላ አድርጓል። ሳምራዊት ስዩም #ዳጉ_ጆርናል
Показати все...
9🙏 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
በፓኪስታን ፔሻዋር ውስጥ በተኩስ ልውውጥና ፍንዳታ ቢያንስ 6 ሰዎች ተገደሉ በፓኪስታን ሰሜናዊ ምዕራብ ፔሻዋር ከተማ ውስጥ በታጣቂዎች እና የአጥፍቶ ጠፊ የቦምብ ጥቃት የጦር ሃይል ዋና መሥሪያ ቤት ላይ ማነጣጠራቸውን የመገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ዶውን ዴይሊ ሰኞ እለት እንደዘገበው የፌደራል ኮንስታቡላሪ ዋና መሥሪያ ቤት “ጥቃት ተፈፅሞበታል” የአጥፍቶ ጠፊ ፈንጂዎች በግቢው በራፍ ላይ እንዳፈነዳ ዘግቧል። የፖሊስ እና የደህንነት ምንጮችን በፔሻዋር ስለደረሰው ጥቃት ማረጋገጫ ሰጥተዋል። ምንጮች እንዳሉት ሁለት ታጣቂዎች መገደላቸውን እና የጸጥታ ሃይሎች አካባቢውን እንደከበቡት ተናግረዋል። የሮይተርስ የዜና ወኪል እንደዘገበው ሕንጻው በሁለት አጥፍቶ ጠፊዎች የተመታ ሲሆን ቢያንስ የስድስት ሰዎች ህይወት ማለፉን ዘግቧል። የመጀመሪያው አጥፍቶ ጠፊ ጥቃት በዋናው መግቢያ በር ላይ የደረሰ ሲሆን ሌላኛው ጥቃት ግቢው ከገባ በኃላ መፈፀሙን ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ ከፍተኛ ባለስልጣናት ተናግረዋል።የጦር ኃይሉ ዋና መሥሪያ ቤት አቅራቢያ በህዝብ እንቅስቃሴ የተጨናነቀ አካባቢ እንደሆነ ዘገባዎች አመላክተዋል። በስምዖን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
Показати все...
4💔 4
15 ሴቶችን ጨምሮ 36 ሿሿ የሚስሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ በቡድን በመደራጀት በመዲናዋ በተለምዶ ሿሿ ተብሎ የሚጠራውን ወንጀል የሚፈፅሙ እና ከወንጀለኞቹ የተሰረቀ እቃን የሚገዙ ወንጀል ፈፃሚዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ እያጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ፡፡ ከወንጀሉ ጋር ተያያዥነት ያላቸው 36 ግለሰቦች እና 5 ተሽከርካሪዎች ተይዘዋል፡፡ አዲስ አበባ፤ ህዳር 15 ቀን 2018 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፡- የምርመራ መነሻ የሆነው በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ኤሚግሬሽን አካባቢ ህዳር 9 ቀን 2018 ዓ/ም ከቀኑ 7:00 ሰዓት ላይ የተፈፀመው የወንጀል ድርጊት ነው። የግል ተበዳይ ኢየሩስ ግርማ ትራንስፖርት በመጠበቅ ላይ እንዳለች ወንጀል ፈፃሚዎቹ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 ማ.ኢ 01058 ሚኒባስ ተሽከርካሪ ይዘው በመንቀሳቀስ የት ነሽ? በማለት ካሳፈሯት በኋላ ሞባይል ስልኳን ለመቀማት ሲታገሉ በአካባቢው ላይ በወንጀል መከላከል ሥራ ላይ በነበሩ የፖሊስ አባላት ዕይታ ውስጥ ይወድቃሉ፤ በፖሊስ ዕይታ ውስጥ መውደቃቸውን የተረዱት ተጠርጣሪዎች የግል ተበዳይን ገፍትረው በመጣል ለማምለጥ ቢሞክሩም ተጠርጣሪዎቹን እስከ መጨረሻው በመከታተል አራቱንም በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል። ፖሊስ በቁጥጥር ስር የዋሉትን ተጠርጣሪዎች መነሻ በማድረግ በተደረገ ሰፊ ምርመራ የማስፋት ተግባር የወንጀል ድርጊቱን የሚመራ እና የሚያስተባበር ቡድን እንዳለ ይደርስበታል፡፡ የወንጀለኛ ቡድኑን በቁጥጥር ስር ለማዋል በተደረገ ክትትልም በጉለሌ ክፍለ ከተማ አዲሱ ገበያ አካባቢ ስምሪት የሚሰጡ 11 ግለሰቦች ሊያዙ ችለዋል፡፡ ለወንጀል ፈፃሚዎቹ ስምሪት በሚሰጠው ቡድን ላይ በተከናወነ ሌላ ጠንካራ ምርመራን የማስፋት ተግባርም በቡድኑ ስምሪት የተሰጣቸውን 8 ሌሎች ወንጀል ፈፃሚዎች በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3B አ/አ 55902 ሚኒባስ ተሽከርካሪ በመጠቀም የሿሿ ወንጀል ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ በልደታ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ኮካ እየተባለ በሚጠራው አደባባይ በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል፡፡ ፖሊስ ምርመራውን በማጠናከር ባደረገው ብርቱ ክትትል ተመሳሳይ የወንጀል ድርጊት ለመፈፀም ስምሪት የተሰጣቸው በኮድ 3 አ/አ 96708 አራዳ ክፍለ ከተማ እንዲሁም በኮድ3 ኦሮ A02639 ቦሌ ክፍለ ከተማ በሚኒባስ ተሽከርካሪዎች ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 13 አባላት ያሉት ሁለት ቡድን በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል፡፡ ከዚሁ ወንጀል ጋር በተያያዘ በኮድ 3B አ/አ 47364 በሆነ ቪትስ ተሽከርካሪ እየተዟዟሩ ከወንጀል ፈፃሚዎች የተሰረቀ እቃ ሲገዙ የነበሩ ሁለት የሌባ ተቀባዮች ተይዘው በህግ አግባብ በተደረገ ብርበራ እና ፍተሻ ከግለሰቦቹ መኖሪያ ቤት 30ሺ 700 ብር፣ 1 ላፕቶፕ፣ 1 ታብሌት፣ 11 ዘመናዊ ስልኮች፣ ተሰርቀው ቀፎዎቹ የተሸጡበት 188 የስልክ ከቨሮች በኤግዚቢትነት መያዙን የልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታውቆ በአጠቃላይ ከዚህ ወንጀል ጋር በተያያዘ 36 ሰዎችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑንም ፖሊስ መምሪያው ገልጿል። በተለይም የትራንስፖርት ተሽከርካሪዎችን በመጠቀም የሚፈፀሙ የሿሿ ወንጀሎችን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት በማገዝ ህብረተሰቡ መረጃ በመስጠት ተባባሪ መሆን እንደሚገባው ያሳሰበው ፖሊስ ትራንስፖርት ተጠቃሚዎች ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባቸው አሳስቧል። በወንጀሉ የምርመራ ሂደት አንዳንድ የተሽከርካሪ ባለንብረቶች ሆን ብለው ተሽከርካሪዎቻቸውን ለወንጀል ፈጻሚዎች እንደሚያከራዩ በምርመራ የተደረሰበት ሲሆን በግለሰቦቹ ላይ የሚያስከተለው የህግ ተጠያቂነት እንደተጠበቀ ሆኖ ወደ ፊት የተሽከርካሪያቸውን አይነትና የባለ ንብረቶቹን ስም ዝርዝር ለህዝብ ግልፅ እንደሚያደርግ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል። በዚህ የወንጀል ድርጊት በቁጥጥር ስር ከዋሉት ተጠርጣሪዎች ጋር በተያያዘ ወንጀል ተፈፅሞብኛል የሚል ግለሰብ ልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በአካል በመቅረብ ማመልከት እና መረጃ መስጠት እንደሚችልም ፖሊስ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡ Via AAP
Показати все...
29🤔 4🤯 3👍 1
4
ወንበር ላይ ልብስ ያሰጡ ግለሰቦች እርምጃ ተወሰደባቸው በኮሪደር ልማት ለህዝብ ማረፊያ በተሰሩ ወንበሮች ላይ የታጠቡ ልብሶችን ያሰጡ ግለሰቦችና ተቋም ላይ እርምጃ ተወሰደ ህዳር 14 ቀን 2018 ዓ.ም በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 በኮሪደር ልማት በተሰሩ የህዝብ ማረፊያ ወንበሮች ላይ የታጠቡ ልብሶችን ያሰጡ ግለሰቦችና ተቋም እርምጃ መውሰዱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አስታወቀ። ድርጊቱን ፈጽመው የተገኙ የኮሪደር ልማቱ የመዝናኛ ካፌ እና ሰራተኞቹን ወደ ህግ በማቅረብ ተጠያቂ በማድረግ ካፌው ተገቢው ቅጣት አስኪቀጣ መታሸጉ ተገልጿል። ህብረተሰቡ በከተማዋ ውስጥ በመንግስትና በህዝብ ሀብት የተገነቡ የኮሪደር ልማቶችና የወንዝ ዳር ፕሮጀክቶችን እና ሌሎች መሠረተ ልማቶችን ደህንነት በመጠበቅ ለታለመላቸው ዓላማ ብቻ መገልገልና መጠቀም እንደሚገባም አስታውቋል፡፡ ደንብ ተላልፈው በሚገኙ አካላት ላይ በህጉ መሠረት የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ባለስልጣኑ ለኤኤምኤን በላከዉ መረጃ አስታውቋል። #ዳጉ_ጆርናል
Показати все...
ኢትስዊች እና ማስተርካርድ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የክፍያ አቅምን ለማስፋት ያለመ ስምምነት ተፈራረሙ ኢትስዊች እና ማስተርካርድ የኢትዮጵያን ዲጂታል የክፍያ ሥነ-ምህዳር ለማሳደግ እና ሀገሪቱ ከዓለም አቀፍ የፋይናንስ አውታረ መረብ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ አዲስ የንግድ ስምምነት በዛሬው እለት ተፈራርመዋል።የኢትስዊች ዋና ሥራ አስፈፃሚ  አቶ ይለበሰ አዲስ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት ይህ ሽርክና በኢትዮጵያ ዲጂታል ለውጥ ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ ነው ብለዋል። በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያላቸውን የቀጣይ ትውልድ የክፍያ መፍትሄዎችን ያስተዋውቃል ሲሉ የተናገሩት ዋና ስራ አስፈፃሚው የፋይናንስ ሥነ-ምህዳራችንን ደህንነት እና የመቋቋም አቅም በእጅጉ ያጠናክራል ብለዋል። ስምምነቱ በመላ አገሪቱ የሚገኙ የፋይናንስ ተቋማትን፣ ንግዶችን እና ሸማቾችን የሚጠቅሙ ፈጠራ ያላቸው፣ ደህንነታቸው የተጠበቀ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያላቸው የክፍያ መፍትሄዎችን ለማስተዋወቅ የጋራ ቁርጠኝነትን ያንፀባርቃል። በዚህ አጋርነት ስር ማስተርካርድ እና ኢትስዊች የተለያዩ ዓለም አቀፍ የክፍያ ችሎታዎችን ለማሰስ እና ተግባራዊ ለማድረግ አብረው ይሰራሉ።ሽርክናው ኢትስዊች በማስተርካርድ ኔትወርክ እና በማስተርካርድ ዓለም አቀፍ የክፍያ መግቢያ አገልግሎቶች በኩል በቀጥታ ግንኙነት እንዲኖረው ያደርጋል የተባለ ሲሆን ይህም በማስተርካርድ የምክር አገልግሎቶች የተደገፈ መሆኑ ተገልጿል።ይህም የኢትዮጵያ ንግዶች ዓለም አቀፍ ክፍያዎችን እንዲቀበሉ እና ለድንበር ተሻጋሪ ንግድ እድሎችን እንዲያሰፉ ያስችላቸዋል ተብሏል። በተጨማሪም በዚህ ትብብር የኢትዮጵያ ባንኮች በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለምንም እንከን የሚሰሩ እና በኤቲኤሞች፣ በፖስ ተርሚናሎች እና በኦንላይን ነጋዴዎች ዓለም አቀፍ ተቀባይነትን የሚያቀርቡ የጋራ ብራንድ ያላቸው የቅድመ ክፍያ የጠንካራ ምንዛሬ ካርዶችን እንዲያወጡ ይፈቀድላቸዋል። በቅድስት ደጀኔ #ዳጉ_ጆርናል
Показати все...
🔥 6 4😁 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
አቶ ታዬ ደንደአ “ ሦስት አዳዲስ  ተደራራቢ የወንጀል ክሶች እንደተከፈተባቸው ” ጠበቃቸው  ተናገሩ ዛሬ ባስቻለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የሕገ መንግሥት እና በሕገ መንግሥት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ችሎት የቀድሞው ምክትል የሰላም ሚኒስትር ታዬ ደንደአ ሦስት አዳዲስ ተደራራቢ ክሶች በዐቃቤ ህግ እንደተከፈተባቸው ጠበቃቸው አበራ ንጉስ ለአዲስ ማለዳ ነግረዋታል፡፡ አንደኛው “ መንግስትን በኃይል ለመጣል በሚደረግ ዝግጅት ላይ ጫካ ካሉት ኃይሎች ጋር ተመጋጋቢ የሆኑ ፕሮፓጋንዳ ፈጽመዋል፤ የፕሮፓጋዳ ድጋፍ አድርገዋል ” የሚል ሲሆን ይህንን ድጋፍ ያደረጉት ደግሞ ሆርን ኮንቨርሴሽን በሚባል የዩቱብ ቻናል ላይ ቀርበው በሰጡት በሦስት ተከታታይ ክፍሎች በተሰራጨው ዝግጅት ላይ ነው፡፡ ሁለተኛው ክስ ደግሞ በተመሳሳይ በተጠቀሰው የዩቱብ ቻናል ላይ መከላከያ ሠራዊት በተለይም ስለሰሜን ዕዝ ጥቃትና ተያያዥ ጉዳዮች  በተመለከተ “ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሉኝ ብለው የተናገሩት በመከላከያ ላይ የተነዛ ሀሰተኛ መረጃ ነው ” በሚል ሲሆን ሦስተኛው ክስም በዚሁ ቻናል በሰጡት አስተያየት ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ታዬ “ ብልጽግና የአንድን ሰው ስልጣን ለማቆየት የተደራጀ ፓርቲ ነው፤ ፓርቲው በአመዛኙ የማፊያ ባህሪ ያለው መንግስት እንዲመሰረት አስተዋጽዖ ያደረገ እንጂ የህዝብን ፍላጎት ለማስፈጸም የተደራጀ ፓርቲ አይደለም፣ በማለት በሀገሪቱ ህገ መንግስት መሰረት የተመረጠውን መንግስት ስም  በማጉደፍ” በሚል ተከስሰዋል፡፡ በእነዚህ ተደራራቢ ክሶች ላይ መቃወሚያ ላይ ለማቅረብና ውሳኔ ለመስጠት ለህዳር 23 ቀን 2018 ዓ.ም ቀጠሮ መሰጠጡንም ተናግረዋል፡፡     አዲስ ማለዳ #ዳጉ_ጆርናል
Показати все...
👎 30 12🤔 2🙏 2👍 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
አቶ ታዬ ደንደአ “ ሦስት አዳዲስ  ተደራራቢ የወንጀል ክሶች እንደተከፈተባቸው ” ጠበቃቸው  ተናገሩ ዛሬ ባስቻለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የሕገ መንግሥት እና በሕገ መንግሥት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ችሎት የቀድሞው ምክትል የሰላም ሚኒስትር ታዬ ደንደአ ሦስት አዳዲስ ተደራራቢ ክሶች በዐቃቤ ህግ እንደተከፈተባቸው ጠበቃቸው አበራ ንጉስ ለአዲስ ማለዳ ነግረዋታል፡፡ አንደኛው “ መንግስትን በኃይል ለመጣል በሚደረግ ዝግጅት ላይ ጫካ ካሉት ኃይሎች ጋር ተመጋጋቢ የሆኑ ፕሮፓጋንዳ ፈጽመዋል፤ የፕሮፓጋዳ ድጋፍ አድርገዋል ” የሚል ሲሆን ይህንን ድጋፍ ያደረጉት ደግሞ ሆርን ኮንቨርሴሽን በሚባል የዩቱብ ቻናል ላይ ቀርበው በሰጡት በሦስት ተከታታይ ክፍሎች በተሰራጨው ዝግጅት ላይ ነው፡፡ ሁለተኛው ክስ ደግሞ በተመሳሳይ በተጠቀሰው የዩቱብ ቻናል ላይ መከላከያ ሠራዊት በተለይም ስለሰሜን ዕዝ ጥቃትና ተያያዥ ጉዳዮች  በተመለከተ “ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሉኝ ብለው የተናገሩት በመከላከያ ላይ የተነዛ ሀሰተኛ መረጃ ነው ” በሚል ሲሆን ሦስተኛው ክስም በዚሁ ቻናል በሰጡት አስተያየት ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ታዬ “ ብልጽግና የአንድን ሰው ስልጣን ለማቆየት የተደራጀ ፓርቲ ነው፤ ፓርቲው በአመዛኙ የማፊያ ባህሪ ያለው መንግስት እንዲመሰረት አስተዋጽዖ ያደረገ እንጂ የህዝብን ፍላጎት ለማስፈጸም የተደራጀ ፓርቲ አይደለም፣ በማለት በሀገሪቱ ህገ መንግስት መሰረት የተመረጠውን መንግስት ስም  በማጉደፍ” በሚል ተከስሰዋል፡፡ በእነዚህ ተደራራቢ ክሶች ላይ መቃወሚያ ላይ ለማቅረብና ውሳኔ ለመስጠት ለህዳር 23 ቀን 2018 ዓ.ም ቀጠሮ መሰጠጡንም ተናግረዋል፡፡     አዲስ ማለዳ #ዳጉ_ጆርናል
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
የፊሊፒንስ ፕሬዝዳንት ማርኮስ በሙስና ቅሌት ሰባት ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናገሩ በደቡብ ምስራቅ እስያዊቷ ሀገር ፊሊፒንስ በጎርፍ መከላከል ፕሮጀክቶች ላይ በተከሰተው የተንሰራፋ የሙስና ቅሌትን ተከትሎ በተደረገው ምርመራ ሰባት ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የፊሊፒንስ ፕሬዝዳንት ፈርዲናንድ ማርኮስ ጁኒየር ተናግረዋል። ተጠርጣሪዎቹ ከተዘረፈው የመሠረተ ልማት ግንባታዎች ላይ እጃቸው እንዳለበትና በስፋት በሚጠበቀው ልዩ የጸረ ሙስና ፍርድ ቤት ሳንዲጋንባይያን ከተከሰሱት ከ12 በላይ ሰዎች መካከል ናቸው። በቁጥጥር ስር የዋሉት ፕሬዝዳንቱ ማርኮስ ቅሌትን ለማጣራት ኮሚሽን ካቋቋሙ ከሁለት ወራት በኋላ ነው። የፋይናንስ ዲፓርትመንት ሀገሪቱን ይህው የምዝበራ ቅሌት እስከ 118.5 ቢሊዮን ፔሶ ወይን 2 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር እንዳከሰራት ገልጿል። ይህንኑ የሙስና ቅሌት ተከትሎ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተጠያቂነት እንዲሰፍን በዋና ከተማዋ ማኒላ ጎዳናዎች ለተቃውሞ ሰልፍ መውጣታቸው ይታወሳል። ማርኮስ ሰኞ እለት በፌስቡክ ባሰራጩት የቪዲዮ መልዕክት ላይ ሁለት የሚፈለጉ ተጠርጣሪዎች እጃቸውን ለመስጠት ዝግጁ ሲሆኑ ሰባቱ ግን በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል።ማርኮስ በደርዘን በሚቆጠሩ የሙስና ክሶች የተያዙ ሴናተሮች፣ የምክር ቤት አባላት እና ሀብታም የኮንስትራክሽን ኩባንያ ባለቤቶች እንደሚያዙ ቃል ገብተዋል። በመጪው እሁድ በፊሊፒንስ ይህንኑ የአስተዳደሩን የሙስና ቅሌት ለመቃወም የታቀደው ሰልፍ በሀገሪቱ ከፍተኛ ተፅእኖ ባላት ሮማ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የሚደገፈ እንደሆነ ተሰምቷል። በስምዖን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
Показати все...
4😁 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
በአለርት ሆስፒታል ለ15 ቀን የሚቆይ ነፃ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ህክምና ሊሰጥ ነው የአለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ነፃ የዓይን ሞራ ግርዶሽ (ካታራክት) ህክምና ከ ህዳር 15 ቀን 2018 ጀምሮ እንደሚሰጥ እና  ህክምናውን ማድረግ የሚፈልጉ  በሙሉ በዓይን ህክምና ማዕከሉ በመገኘት  ቅድመ ምርመራ ማድረግ እንደሚችሉ ተገልፆል፡፡ በአለርት ኮምፕረሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አለምሰገድ ጫኔ ከብስራት ሬዲዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለፁት ህክምናው ከ20 በላይ በሚሆኑ ባለሙያዎች ከህዳር 15 ጀምሮ እንደሚሰጥ ገልፀዋል፡፡የዓይን ሞራ ግርዶሽ ህክምናው በአዲስ አበባ ከተማ እንዲሁም በዙሪያዋ የሚገኙ የማኅበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ በመሆኑ በአካል በመምጣት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ ተብሏል፡፡ ይህ አገልግሎት በነጻ የሚሰጥ ሲሆን ምንም አይነት የእድሜ ገደብ የሌለው ሲሆን እንደ ችግሩ ሁኔታ ቀዶ ህክምና  የሚያስፈልጋቸው ከተሰሩ በኋላ ለተወሰነ ቀን በሆስፒታሉ እንዲቆዩ በማድረግ በቀጠሮ እንዲመጡ ይደረጋል ሲሉ ዳሬክተሩ ገልፀዋል፡፡ ማኅበረሰቡም ይህንን ዕድል እንዲጠቀም ከህዳር 15 ቀን 2018 ዓ.ም  ጀምሮ ለአስራ አምስት ቀናት ያህል ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ ማታ 11፡00 ሰዓት ድረስ  በነፃ በሆስፒታሉ አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ ሲሉ  በአለርት ኮምፕረሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አለምሰገድ ጫኔ  ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡ ሳምራዊት ስዩም #ዳጉ_ጆርናል
Показати все...
20👍 2