uz
Feedback
ግጥም ብቻ 📘

ግጥም ብቻ 📘

Kanalga Telegram’da o‘tish

✔በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን። ✔ @getem @serenity13@wegoch @Words19@seiloch @shiyach_bicha@zefenbicha @leul_mekonnen1

Ko'proq ko'rsatish
2025 yil raqamlardasnowflakes fon
card fon
65 744
Obunachilar
-924 soatlar
-597 kunlar
-32030 kunlar
Postlar arxiv
ምኞት ምትጸንሰው ምኞት ፀንሳ ሃጥያትን ትወልዳለች፣ ፑልም ተጀምራ ቁማር ትሆናለች። ለመዝናናት በሚል በተልካሻ ምክንያት፣ ምኞት ትሄዳለች ወደ ትልቅ ሃጥያት። ሃጥያት ሲተነተን በብዙ መንገድ ነው፣ እንደ ሃጥያቱ ብዛት በሲኦልም ሲኬድ የራስ ክፍል አለው። ከሃሳቤ ሳልስት ከፑሉ ሳልወጣ፣ ቁማሩን ተወው እንጂ ከፑል ቤት አትውጣ። By G.hanun @getem @getem @getem
Hammasini ko'rsatish...
😁 27👍 13 4🔥 1😱 1🤩 1
Photo unavailableShow in Telegram
የካቲት ወርሀ-ገብረ-ክርስቶስ ; ቅዳሜ የካቲት 29 ቀን 2017 ዓ/ም ከቀኑ 8:30 ሰአት በገብረ ክርስቶስ ሙዚየም 6 ኪሎ ፧ አመታዊው አለማቀፍ የገብረክርስቶስ ቀን በስነ ግጥምና ስነ ጥበብ ደምቆ ይከበራል። ገብረክርስቶስንና ድንቅ ስራዎቹን የምትወዱ ሁሉ ተጋብዛችሁዋል። ፕሮግራሙ በቀጥታ ስርጭት ይተላለፋል። ምንጭ አርቲስት በቀለ መኮንን @Seiloch
Hammasini ko'rsatish...
👍 13 8
ሀሰት በከበባት ኢ ፍትሀዊ አለም ተከሳሽ በሙሉ ወንጀለኛ አይደለም አይገርምም ...? የሚታዘዙለት ሳርና ንፋሱ ሀጢአት የሌለባት ንፁህ ሳለች ነፍሱ ወንጀለኛ ተብሎ ፤ ተከሳሽ ነበረ ክርስቶስ እራሱ፡፡ By Eyob Z Mariam @getem @getem @paappii
Hammasini ko'rsatish...
99👍 28😢 8
"ድንቄም ቆራጭ"😁😁😁 """"""""""""""""""""" ከልብ ተሠርንቆ ልውጣ አልውጣ እያለ፤ ያስገባንው ነገር ከአቅም ካየ"ለ። ይውጣ ምናባቱ ልብን ከበሽተ ካላረገን ደህና፤ አንቅሮ መትፋት ነው ከሚያሳጣን ጤና። ሰውም እንደዚህ ነው፥ የልባችን እሳት የልባችን ንዳድ ለሱ ከበረደው፤ የፍቅራችን ሙቀት ቀዝቅዞ ከታየው። ምን ሊያረግ ይቀመጥ ሊሆነን ፈተና፤ ከተመቸው ይሂድ መንገዱ ያውና። የልባችን መሻት መሻቱ ካልሆነ፤ የመውደድ ፍላቱ ከሱው ከተነነ። ልቡ የሸፈተን አስረን ላናስቀረው፤ መንገዱ ያውና ይሂድ ከተመቸው። ብዬ እፎክርና ዝቼ በሃሳቤ፤ አስሮ ያስቀመጠው ይሸነፋል ልቤ። አድሮ ልመና...ተው ፍታኝ የቃልህ እስረኛ ነኝ🥹 ምን ላርግ ከእኔ ዘንድ አልሰራም ✍ጦቢያ ቀን 21 የካቲት፦2017-አርብ @getem @getem @getem
Hammasini ko'rsatish...
👍 38 15
በየሰፈሩ ሰፍረን በየአጥሩ ተንጠልጠለን አድዋን ያህል አድባር ጥለን ካምና ርቀን ዛሬን ንቀን ነገን ናፍቀን መራመዱ እየጨነቀን በየጥጉ ተናንቀን ቀኑን ማሰብ እስኪያስፈራው የታለ ባለፈረሱ? የታለ ባለ ባንዴራው? የታል የትውልድ አደራው? አድዋን ያህል ትልቅ ጥለት አድዋን ያህል ህብር ቀለም ክብሩ ገብቶን ፍሬው ታይቶን ሳንደምቅበት ተያይዘን ሳንኮራበት ታሪክ መዘን በጊዜ ፊት እንዲህ ፈዘን ያከበረን ያስከበረን ኩራት ሆኖ ያዘለቀን አድዋ ያህል ዘ ላ ለ ም ቀን ስሙን መጥራት ድሉን ማሰብ ተናነቀን?! By Thomas lemma @getem @getem @paappii
Hammasini ko'rsatish...
👍 37 29🔥 8😢 3🤩 1
.......... ቀለም ጸሀይ አይደለችም የቸረች ተፈጥሮን ውበቷ ነው እንጂ ጨለማን ሰውሮን በነጭና ጥቁር በበዛበት ህይወት ተፈጥሮን በረሳ ቀለም በናፈቀው ጸሀይ አይደለችም ገላሽን አቅፎ ነው ጓዳዬ የሞቀው ቤቴ የደመቀው ያልተጋሩት እቶን የሚማገዱበት ልክ እንደ ዕሳት ዕራት ሞቶ የመኖር ብስራት በብርሀኗ ውስጥ በሚንቦገቦገው ፍቅርን ልፈልገው ስዳራሽ እያዩ ሞቶ ነው እያሉ ህያዋን ሲለዩ ለዚህ ነው የምልሽ ቀለም ጸሀይ አይደለችም የሰጠች ተፈጥሮን ውበቷ ነው እንጂ ጨለማን ሰውሮን በሳት ላልተዳሩ ላልተፋቀሩ! ቅሉ አይገባቸውም የቀለም አደሱ የፍቅራቸው ምሱ ? ዕሳት ዕራት መሆን ጸጋ መች ታደለ ከሚነድ ወላፈን ጠብታን ያከለ ለዕሳት ነፍስ የዘራ ስጋውን ሰውቶ ጸሀይ አይደለችም ውበቷ ብቻ ነው የሚታየው ጎልቶ By @mad12titan @getem @getem @getem
Hammasini ko'rsatish...
👍 15 15🔥 3
ስርአት! (የሞገሤ ልጅ) አንተ የእኔ ምትክ፣ የእራሴ መታያ የአብራኬ ክፋይ፣ እንኳንም ወለድኩህ፣ የፈጠረህ ፈቅዶ ዐይኔን በዐይኔ እንዳይ። አንተ ግን ቸኩለህ፣ መልሰህ መሄድህ ወደመጣህበት፣ ምን ሰይጣን መክሮህ ነው፣ ያረከኝ በሃዘን እንድኮረማመት። የውልህ ልንገርህ፣ ተወልዶ ማረፉ በሰላሳኛ ቀን፣ ላንተም ኪሳራ ነው፣ ለኔም የእድሜ ልክ ስብራት ሰቀቀን። ያንተን ጉዳት ላርዳህ፣ ለገነት ከሆነ ሞትህ በዚህ እድሜ፣ እኔም አልገባሁም፣ ካንተ በላይ ኖሬ 55 ቀን ጾሜ። By @tafachgitm @getem @getem @getem
Hammasini ko'rsatish...
😢 24👍 18 6👎 2😱 2
............ ትከተይኛለሽ ብዬ ስለማስብ በሄድኩበት ሁሉ እጅ እንድሰበስብ መዞር እፈራለሁ ዞሬ ያጣሁሽ እንደው ብቻዬን መሆኔስ ምን ነጻነት አለው ትከተይኛለሽ በአለሁበት አለሽ ብዬ ስለማስብ ትዝታ እንደ ገላ ይዳብሰኝና አለሄደችም ብዬ ልቤን አጽና..ና...ና ጀርባዬን አምናለሁ አንቺ ከነጠቀኝ እውነት ምን ዋጋ አለው ያልኖሩበት ነገ ተስፋው ምን ሊጠቅም አለሽ ብዬ አምናለሁ ዞሬ ግን አላቀም በሄድኩበት ሁሉ በሳር በገደሉ እረኛ ያጣ በሬ በኮቴው ሲያደቀው አንቺን ነሽ በዬ ነው በተስፈ የምስቀው ጠረንሽ ቢጠፋኝ ሽቶ ያኮፈሳት ላባም ሴት ፈልጌ በሴሰኛ ስሜት ጭኗን ተፋትጌ ሲረካ መንፈሴ አንቺ ነሽ ብሎ ነው የሚስቀው ጥርሴ መቼም ለመኮነን መዞርም አያሻም ሀጥያት በዝቷል ከፊት የከፋኝ ጊዜ ነው የማቀው ያንቺን ፊት ትከተይኛለሽ ባለሁበት አለሽ ብዬ ስለማምን እንትን ተመኝቼ ጌታዬን ስለምን የሷንም እላለው ይሰማሽ እንደሆን እንጃ ምን አውቃለሁ መሄድ እንደቀላል መንገዱን ሲያረዝመው መድረስ አይናፍቅም አለሽ ብዬ አምናለሁ ዞሬ ግን አላቅም By @mad12titan @getem @getem @paappii
Hammasini ko'rsatish...
👍 28 22🔥 4
ድንገት ያገኘሁት የድሮ ግጥሜ ____ ጀምበር ገባች ፥ መሸ ያጸዳሁት ቤቴም ፥ መልሶ ቆሸሸ አልጠፋም መብራቱ አልተበላም 'ራቱ አሁንም ክፍት ነው በርና መስኮቱ ። ለቁር ተጋለጠ ፥ ጓዳዬ እንደ ውጪው መቼ ነው የምትመጪው ? መጽሐፍ ገለጥኩና መልሼ ዘጋሁት ልጽፍ አሰብኩና ብዕሬን ወረወርኩት መቆም መንጎራደድ መቆም መንጎራደድ መቆዘም መተከዝ ፥ በሐሳብ መሰደድ ደርሶ ብንን ብንን ደሞ ቁጭ ብድግ ካንቺ ውጭ አላውቅም ምን እንደምፈልግ ። ምኞት ነው ያለኝ ፥ ዝም ብሎ ምኞት ወይ የማያኖር ፥ ወይ የማያስሞት ትመጫለሽ እያልኩ በጉጉት ከምኖር ምናለ በሞትኩኝ ለአንድ ለስድስት ወር ። @getem @getem @paappii By Hab Hd
Hammasini ko'rsatish...
63👍 30😁 24🤩 5😢 4
አታውቂም (kerim የተዋቡ አይኖችሽ ካልተፋብኝ እቶን አፍሽ ካልጠራብኝ የርግማን መዓቱን በዚህ ሁሉ መሀል መዓዛሽን ካልማግኩት ታድያ ምኑን ኖርኩት? - - - አለም ብትጠፋ ካንቺ እጦት አይከፋ አታውቂም መኖርሽ እንደሚያኖረኝ አታውቂም ከሌላም አይቼሽ ደስታ እንደሚያሰክረኝ ከኔ ደስታ ይልቅ ስለ አንቺ ደስታ የልቤ መሻት ነው ስላንቺ አዬመታ አላውቅም ቅናት ይሉት ስሜት ወዴት ተሰወረ ልቤስ ስለ እጦቱ ስለምን ታተረ? (እንዳልኩሽ አላውቅም) By @poem2513 @getem @getem @paappii
Hammasini ko'rsatish...
28👍 17🔥 1😢 1
. ተንበርክኮ መድረስ ተጎንብሶ መንገስ አቀርቅሮ ሹመት አሽቀንጥሮ ድሎት ጸሎት እስኪበሩ ማንከስ እስኪስቁ ማልቀስ እስኪይዙ ማጣት እስኪረቱ ችሎት ጸሎት By Rediet Aseffa @getem @getem @paappii
Hammasini ko'rsatish...
59👍 12🔥 7
አይ አንቺ ጨረቃ . . . ስንቱን ሰዉ ታዘብሽዉ? ስንቱን አደመጥሽዉ? የከፋዉ እንደሆን ላንቺ      የሚያወጋዉ፤ በልቡ ያለዉን ሚስጥራቱን    ሁሉ  የሚዘረግፈዉ፤    እስቲ ልጠይቅሽ? ምን ቢያይብሽ ነዉ? By ዔደን ታደሰ @ediwub @getem @getem
Hammasini ko'rsatish...
👍 31 7🤩 2
የተመደበልኝ ዘመን ከባከነ የተሰፈረልኝ ቀን አልቆ ከሆነ ተፈጥሮን ደጅ ልጥና ባዲስ መንገድ ትስራኝ ባዲስ የፍጥረት ውል:: መስኮትሽ ላይ ሆና ስትዘምር የምትዉል ድንቢጥ ወፍ ታድርገኝ:: ብኖር አንቺን አየሁ ከመሞት ምን ሊገኝ ። በዕውቀቱ ስዩም @getem @getem @paappii
Hammasini ko'rsatish...
40👍 19🔥 6🤩 3
............ ይሁን ካልሽ ..... ይሁን በቃ ትቼዋለው ልብ ካልወደደ ይቅር ማለት ምን ዋጋ አለው ባትነግሪኝም ........ የገፋሽን ጥፋት አብሮ መሆን ደርሶ ነፍስሽን ካስከፋት ቃል እየመረኩኝ አልሻም ላባብል ፊደል እያቀናው ስህተቴን ላስታብል ይሁን ካልሽ ይቅር ካልሽ ይቅር በቃ ትቼዋለው ልብ ካልወደደ አብሮ መሆን ምን ዋጋ አለው መነጣጠል ቢያረክስም ፍቅርሽን አልከስም ባትነግሪኝ አውቀዋለው ኩርፊያሽ ሀቅ እንዳለው ይቅር ብለሽ በቃ ብለሽ መለየት ከመረጥሽ መኖር ተነጥለሽ ምን እላለው ልብ ካልወደደ አብሮ መሆን ምን ዋጋ አለው By @mad12titan @getem @getem @getem
Hammasini ko'rsatish...
28👍 24😢 8🤩 3
Anyone Mumbai to addis Ababa inbox me, it's for k....✋ @paappii
Hammasini ko'rsatish...
👍 7
መንገድ መሆን ------------------------- ጠልቼሽ አይደለም ጥላኝ ሄደች ብዬ: የማልጨነቀው መንገድሽ ስለሆንኩ: የመጣሽ ግዜ ነው: መሄድሽን የማውቀው:: By belay bekele weya @getem @getem @paappii
Hammasini ko'rsatish...
25🔥 7👍 6😱 2
........... ከመቅደስ ቆመን ነጠላ አዘቀዘቅን ልንፈትንህ ብለን ትቢያ ላይ ወደቅን አስቲ ከላህ ከዙፈንህ ይሄን ድንጋይ ዳቦ አድርገው ቃልህን ሳይሆን የለት እንጀራ ነው ልጄ የሚያስፈልገው በተጣበቀ አንጀት በጎደለ ማጀት እምነት ምን ይሰራል ተራራ የሚነቅል ወንጌል ምን ይበጀል የማይሞላ ከቅል ቀንቤሬ ቆፈሮ ማጭድ ከላረሰ በሬ ተጠግርሮ ለምለም ካልጎረሰ ጎደሎ ማጀቴን ድንጋይ ልሰግስገው እውነት ካለህ ? ዳቦ አድርገው ወንጌልህን ሳይሆን የለት እንጀራ ነው ልጄ የሚያስፈልገው ሰማይ እንደላም ጡት ወተት ካዘነበ ከጸባኦት መንበር ከትከሻ አውርጄ ሞፈርና ቀንበር ነጠላ አዘቅዝቄ ከቤትህ ገደምኩኝ ልፈትንህ ብዬ ከትቢያ ወደኩኝ ካለህ አንድ ጠጠር ወይ ጸጉሬን ባርከህ የሳምሶንን አርገው የገፋኝን ሁሉ ዶግ አመድ ላድርገው ወይ እሱም ካልሆነ እምነት ሆኖኝ ጠጠር ወንጭፍ አብጅቼ ዶሮ ላሳድበት ጎልያድ ትቼ By @mad12titan @getem @getem @paappii
Hammasini ko'rsatish...
22👍 13🔥 4👎 3
ቤት እማ ጨዋ ነሽ፣ እንኳን ሌላ ሌላ እኔንም አታይም፣ ግን እድሜ ለሱሱ፣ ወተሽ ወዳጅ ካየሽ አታልፊም አትተይም። የሸመገለን ወንድ፣ በሰለቸ ዐይንሽ ዕያየሽ ወጠምሻ፣ የሱን መድሃኒት፣ አርገሽ ለቀን ያዝሽው የኔን ማስታገሻ። By @tafachgitm @getem @getem @getem
Hammasini ko'rsatish...
😁 8👍 4 4
የልጅነት ፍቅር እንደምን ያሰኛል መቼም አልተዉህም ሀሳብ አይግባህ እንጠለጠል ነበር ብችል ከጀርባህ ስህተት አልነበረም እኔን መምረጥህ በምክንያት ነው የገባሁት ከልብህ አልቀየምህም ብትጠነቀቅ ማየት ግን አልችልም ስትጨናነቅ እንደምፈልግህ እባክህ እወቅ ውስጥህን አድምጠው እኔን ሲናፍቅ ትንሽ አደግ ሲሉስ? ያኔ ልቤ አንተን እየመረመረ አሁን እንደሆንከው ይፈራ ነበረ ፍቅር አመሉ ነው ባደረበት አካል መሸነፍ ሊያስተምር ጦርነት ይፈጥራል By Mahlet @getem @getem @getem
Hammasini ko'rsatish...
👍 23 5👎 2
.......... አፍቃሪሽ በሙሉ ቅኔ ሲቀኝልሽ ዜማ ሲያወርድልሽ እኔም በተራዬ ሰምተሽ የማታቂው ምን ልዘምርልሽ አይተሽ ያልገፋሽው ምን ልገብርልሽ እጅ መንሻ እንዲሆን እጣንና ከርቤ ወይ ሽቶ ና ሰንደል መሰዋት አቅርቤ ባንቺው መጀን ልበል በፈጠረኝ አምላክ ለፈጠራት ሴት ስል በስምሽ ልታበል ካልበቃት ዝማሬ ኩሩ ልቧን ማርኮት ነፍሴን ገበርኩላት ፍቅር ሆኖኝ አምልኮት አፍቃሪሽ በሙሉ ባንቺው መጀን ሲሉ ካንቺ የሚደበቅ የለም አንዲት ነገር ባልሰማሽው ቋንቋ ማፍቀሬን ልናገር ከዘለላ ጸጉርሽ በመላ ቆንጥሬ ባንቺው መጀን እያልኩ መጥቻለሁ ፍቅሬ By @mad12titan @getem @getem @paappii
Hammasini ko'rsatish...
32👍 25🔥 8😁 6