ግጥም ብቻ 📘
الذهاب إلى القناة على Telegram
✔በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን። ✔ @getem @serenity13 ✔ @wegoch @Words19 ✔ @seiloch @shiyach_bicha ✔ @zefenbicha @leul_mekonnen1
إظهار المزيد2025 عام في الأرقام

65 744
المشتركون
-924 ساعات
-597 أيام
-32030 أيام
أرشيف المشاركات
Repost from ሥዕል ብቻ ©
Photo unavailableShow in Telegram
የካቲት ወርሀ-ገብረ-ክርስቶስ ;
ቅዳሜ የካቲት 29 ቀን 2017 ዓ/ም ከቀኑ 8:30 ሰአት በገብረ ክርስቶስ ሙዚየም 6 ኪሎ ፧ አመታዊው አለማቀፍ የገብረክርስቶስ ቀን በስነ ግጥምና ስነ ጥበብ ደምቆ ይከበራል። ገብረክርስቶስንና ድንቅ ስራዎቹን የምትወዱ ሁሉ ተጋብዛችሁዋል። ፕሮግራሙ በቀጥታ ስርጭት ይተላለፋል።
ምንጭ
አርቲስት በቀለ መኮንን
@Seiloch
👍 13❤ 8
"ድንቄም ቆራጭ"😁😁😁
"""""""""""""""""""""
ከልብ ተሠርንቆ ልውጣ አልውጣ እያለ፤
ያስገባንው ነገር ከአቅም ካየ"ለ።
ይውጣ ምናባቱ ልብን ከበሽተ ካላረገን ደህና፤
አንቅሮ መትፋት ነው ከሚያሳጣን ጤና።
ሰውም እንደዚህ ነው፥
የልባችን እሳት የልባችን ንዳድ ለሱ ከበረደው፤
የፍቅራችን ሙቀት ቀዝቅዞ ከታየው።
ምን ሊያረግ ይቀመጥ ሊሆነን ፈተና፤
ከተመቸው ይሂድ መንገዱ ያውና።
የልባችን መሻት መሻቱ ካልሆነ፤
የመውደድ ፍላቱ ከሱው ከተነነ።
ልቡ የሸፈተን አስረን ላናስቀረው፤
መንገዱ ያውና ይሂድ ከተመቸው።
ብዬ እፎክርና ዝቼ በሃሳቤ፤
አስሮ ያስቀመጠው ይሸነፋል ልቤ።
አድሮ ልመና...ተው ፍታኝ
የቃልህ እስረኛ ነኝ🥹
ምን ላርግ ከእኔ ዘንድ አልሰራም
✍ጦቢያ
ቀን 21
የካቲት፦2017-አርብ
@getem
@getem
@getem
👍 38❤ 15
በየሰፈሩ ሰፍረን
በየአጥሩ ተንጠልጠለን
አድዋን ያህል
አድባር ጥለን
ካምና ርቀን
ዛሬን ንቀን
ነገን ናፍቀን
መራመዱ እየጨነቀን
በየጥጉ ተናንቀን
ቀኑን ማሰብ እስኪያስፈራው
የታለ ባለፈረሱ?
የታለ ባለ ባንዴራው?
የታል የትውልድ አደራው?
አድዋን ያህል ትልቅ ጥለት
አድዋን ያህል ህብር ቀለም
ክብሩ ገብቶን
ፍሬው ታይቶን
ሳንደምቅበት ተያይዘን
ሳንኮራበት ታሪክ መዘን
በጊዜ ፊት እንዲህ ፈዘን
ያከበረን ያስከበረን
ኩራት ሆኖ ያዘለቀን
አድዋ ያህል ዘ ላ ለ ም ቀን
ስሙን መጥራት
ድሉን ማሰብ ተናነቀን?!
By Thomas lemma
@getem
@getem
@paappii
👍 37❤ 29🔥 8😢 3🤩 1
..........
ቀለም
ጸሀይ አይደለችም የቸረች ተፈጥሮን
ውበቷ ነው እንጂ ጨለማን ሰውሮን
በነጭና ጥቁር
በበዛበት ህይወት
ተፈጥሮን በረሳ ቀለም በናፈቀው
ጸሀይ አይደለችም
ገላሽን አቅፎ ነው ጓዳዬ የሞቀው
ቤቴ የደመቀው
ያልተጋሩት እቶን
የሚማገዱበት ልክ እንደ ዕሳት ዕራት
ሞቶ የመኖር ብስራት
በብርሀኗ ውስጥ በሚንቦገቦገው
ፍቅርን ልፈልገው
ስዳራሽ እያዩ
ሞቶ ነው እያሉ ህያዋን ሲለዩ
ለዚህ ነው የምልሽ
ቀለም
ጸሀይ አይደለችም የሰጠች ተፈጥሮን
ውበቷ ነው እንጂ ጨለማን ሰውሮን
በሳት ላልተዳሩ
ላልተፋቀሩ!
ቅሉ አይገባቸውም የቀለም አደሱ
የፍቅራቸው ምሱ ?
ዕሳት ዕራት መሆን ጸጋ መች ታደለ
ከሚነድ ወላፈን ጠብታን ያከለ
ለዕሳት ነፍስ የዘራ ስጋውን ሰውቶ
ጸሀይ አይደለችም
ውበቷ ብቻ ነው የሚታየው ጎልቶ
By @mad12titan
@getem
@getem
@getem
👍 15❤ 15🔥 3
ስርአት!
(የሞገሤ ልጅ)
አንተ የእኔ ምትክ፣
የእራሴ መታያ የአብራኬ ክፋይ፣
እንኳንም ወለድኩህ፣
የፈጠረህ ፈቅዶ ዐይኔን በዐይኔ እንዳይ።
አንተ ግን ቸኩለህ፣
መልሰህ መሄድህ ወደመጣህበት፣
ምን ሰይጣን መክሮህ ነው፣
ያረከኝ በሃዘን እንድኮረማመት።
የውልህ ልንገርህ፣
ተወልዶ ማረፉ በሰላሳኛ ቀን፣
ላንተም ኪሳራ ነው፣
ለኔም የእድሜ ልክ ስብራት ሰቀቀን።
ያንተን ጉዳት ላርዳህ፣
ለገነት ከሆነ ሞትህ በዚህ እድሜ፣
እኔም አልገባሁም፣
ካንተ በላይ ኖሬ 55 ቀን ጾሜ።
By @tafachgitm
@getem
@getem
@getem
😢 24👍 18❤ 6👎 2😱 2
............
ትከተይኛለሽ ብዬ ስለማስብ
በሄድኩበት ሁሉ እጅ እንድሰበስብ
መዞር እፈራለሁ
ዞሬ ያጣሁሽ እንደው
ብቻዬን መሆኔስ ምን ነጻነት አለው
ትከተይኛለሽ
በአለሁበት አለሽ
ብዬ ስለማስብ
ትዝታ እንደ ገላ ይዳብሰኝና
አለሄደችም ብዬ
ልቤን አጽና..ና...ና
ጀርባዬን አምናለሁ
አንቺ ከነጠቀኝ
እውነት ምን ዋጋ አለው
ያልኖሩበት ነገ ተስፋው ምን ሊጠቅም
አለሽ ብዬ አምናለሁ
ዞሬ ግን አላቀም
በሄድኩበት ሁሉ
በሳር በገደሉ
እረኛ ያጣ በሬ በኮቴው ሲያደቀው
አንቺን ነሽ በዬ ነው በተስፈ የምስቀው
ጠረንሽ ቢጠፋኝ
ሽቶ ያኮፈሳት ላባም ሴት ፈልጌ
በሴሰኛ ስሜት ጭኗን ተፋትጌ
ሲረካ መንፈሴ
አንቺ ነሽ ብሎ ነው
የሚስቀው ጥርሴ
መቼም ለመኮነን
መዞርም አያሻም ሀጥያት በዝቷል ከፊት
የከፋኝ ጊዜ ነው የማቀው ያንቺን ፊት
ትከተይኛለሽ
ባለሁበት አለሽ
ብዬ ስለማምን
እንትን ተመኝቼ ጌታዬን ስለምን
የሷንም እላለው
ይሰማሽ እንደሆን
እንጃ ምን አውቃለሁ
መሄድ እንደቀላል
መንገዱን ሲያረዝመው
መድረስ አይናፍቅም
አለሽ ብዬ አምናለሁ
ዞሬ ግን አላቅም
By @mad12titan
@getem
@getem
@paappii
👍 28❤ 22🔥 4
ድንገት ያገኘሁት የድሮ ግጥሜ
____
ጀምበር ገባች ፥ መሸ
ያጸዳሁት ቤቴም ፥ መልሶ ቆሸሸ
አልጠፋም መብራቱ
አልተበላም 'ራቱ
አሁንም ክፍት ነው በርና መስኮቱ ።
ለቁር ተጋለጠ ፥ ጓዳዬ እንደ ውጪው
መቼ ነው የምትመጪው ?
መጽሐፍ ገለጥኩና መልሼ ዘጋሁት
ልጽፍ አሰብኩና ብዕሬን ወረወርኩት
መቆም መንጎራደድ
መቆም መንጎራደድ
መቆዘም መተከዝ ፥ በሐሳብ መሰደድ
ደርሶ ብንን ብንን
ደሞ ቁጭ ብድግ
ካንቺ ውጭ አላውቅም ምን እንደምፈልግ ።
ምኞት ነው ያለኝ ፥ ዝም ብሎ ምኞት
ወይ የማያኖር ፥ ወይ የማያስሞት
ትመጫለሽ እያልኩ በጉጉት ከምኖር
ምናለ በሞትኩኝ ለአንድ ለስድስት ወር ።
@getem
@getem
@paappii
By Hab Hd
❤ 63👍 30😁 24🤩 5😢 4
አታውቂም
(kerim
የተዋቡ አይኖችሽ ካልተፋብኝ እቶን
አፍሽ ካልጠራብኝ የርግማን መዓቱን
በዚህ ሁሉ መሀል
መዓዛሽን ካልማግኩት
ታድያ ምኑን ኖርኩት?
-
-
-
አለም ብትጠፋ
ካንቺ እጦት አይከፋ
አታውቂም
መኖርሽ እንደሚያኖረኝ
አታውቂም
ከሌላም አይቼሽ ደስታ እንደሚያሰክረኝ
ከኔ ደስታ ይልቅ ስለ አንቺ ደስታ
የልቤ መሻት ነው ስላንቺ አዬመታ
አላውቅም
ቅናት ይሉት ስሜት ወዴት ተሰወረ
ልቤስ ስለ እጦቱ ስለምን ታተረ?
(እንዳልኩሽ አላውቅም)
By @poem2513
@getem
@getem
@paappii
❤ 28👍 17🔥 1😢 1
............
ይሁን ካልሽ .....
ይሁን በቃ ትቼዋለው
ልብ ካልወደደ
ይቅር ማለት ምን ዋጋ አለው
ባትነግሪኝም ........
የገፋሽን ጥፋት
አብሮ መሆን ደርሶ ነፍስሽን ካስከፋት
ቃል እየመረኩኝ አልሻም ላባብል
ፊደል እያቀናው ስህተቴን ላስታብል
ይሁን ካልሽ
ይቅር ካልሽ
ይቅር በቃ ትቼዋለው
ልብ ካልወደደ
አብሮ መሆን ምን ዋጋ አለው
መነጣጠል ቢያረክስም
ፍቅርሽን አልከስም
ባትነግሪኝ አውቀዋለው
ኩርፊያሽ ሀቅ እንዳለው
ይቅር ብለሽ
በቃ ብለሽ
መለየት ከመረጥሽ መኖር ተነጥለሽ
ምን እላለው
ልብ ካልወደደ
አብሮ መሆን ምን ዋጋ አለው
By @mad12titan
@getem
@getem
@getem
❤ 28👍 24😢 8🤩 3
...........
ከመቅደስ ቆመን ነጠላ አዘቀዘቅን
ልንፈትንህ ብለን ትቢያ ላይ ወደቅን
አስቲ ከላህ ከዙፈንህ
ይሄን ድንጋይ ዳቦ አድርገው
ቃልህን ሳይሆን
የለት እንጀራ ነው ልጄ የሚያስፈልገው
በተጣበቀ አንጀት
በጎደለ ማጀት
እምነት ምን ይሰራል ተራራ የሚነቅል
ወንጌል ምን ይበጀል የማይሞላ ከቅል
ቀንቤሬ ቆፈሮ ማጭድ ከላረሰ
በሬ ተጠግርሮ ለምለም ካልጎረሰ
ጎደሎ ማጀቴን ድንጋይ ልሰግስገው
እውነት ካለህ ? ዳቦ አድርገው
ወንጌልህን ሳይሆን
የለት እንጀራ ነው ልጄ የሚያስፈልገው
ሰማይ እንደላም ጡት
ወተት ካዘነበ ከጸባኦት መንበር
ከትከሻ አውርጄ ሞፈርና ቀንበር
ነጠላ አዘቅዝቄ ከቤትህ ገደምኩኝ
ልፈትንህ ብዬ ከትቢያ ወደኩኝ
ካለህ አንድ ጠጠር
ወይ ጸጉሬን ባርከህ የሳምሶንን አርገው
የገፋኝን ሁሉ ዶግ አመድ ላድርገው
ወይ እሱም ካልሆነ
እምነት ሆኖኝ ጠጠር ወንጭፍ አብጅቼ
ዶሮ ላሳድበት ጎልያድ ትቼ
By @mad12titan
@getem
@getem
@paappii
❤ 22👍 13🔥 4👎 3
ቤት እማ ጨዋ ነሽ፣
እንኳን ሌላ ሌላ እኔንም አታይም፣
ግን እድሜ ለሱሱ፣
ወተሽ ወዳጅ ካየሽ አታልፊም አትተይም።
የሸመገለን ወንድ፣
በሰለቸ ዐይንሽ ዕያየሽ ወጠምሻ፣
የሱን መድሃኒት፣
አርገሽ ለቀን ያዝሽው የኔን ማስታገሻ።
By @tafachgitm
@getem
@getem
@getem
😁 8👍 4❤ 4
የልጅነት ፍቅር እንደምን ያሰኛል
መቼም አልተዉህም ሀሳብ አይግባህ
እንጠለጠል ነበር ብችል ከጀርባህ
ስህተት አልነበረም እኔን መምረጥህ
በምክንያት ነው የገባሁት ከልብህ
አልቀየምህም ብትጠነቀቅ
ማየት ግን አልችልም ስትጨናነቅ
እንደምፈልግህ እባክህ እወቅ
ውስጥህን አድምጠው እኔን ሲናፍቅ
ትንሽ አደግ ሲሉስ?
ያኔ ልቤ አንተን እየመረመረ
አሁን እንደሆንከው ይፈራ ነበረ
ፍቅር አመሉ ነው ባደረበት አካል
መሸነፍ ሊያስተምር ጦርነት ይፈጥራል
By Mahlet
@getem
@getem
@getem
👍 23❤ 5👎 2
..........
አፍቃሪሽ በሙሉ
ቅኔ ሲቀኝልሽ
ዜማ ሲያወርድልሽ
እኔም በተራዬ
ሰምተሽ የማታቂው
ምን ልዘምርልሽ
አይተሽ ያልገፋሽው
ምን ልገብርልሽ
እጅ መንሻ እንዲሆን
እጣንና ከርቤ
ወይ ሽቶ ና ሰንደል
መሰዋት አቅርቤ
ባንቺው መጀን ልበል
በፈጠረኝ አምላክ
ለፈጠራት ሴት ስል
በስምሽ ልታበል
ካልበቃት ዝማሬ
ኩሩ ልቧን ማርኮት
ነፍሴን ገበርኩላት
ፍቅር ሆኖኝ አምልኮት
አፍቃሪሽ በሙሉ
ባንቺው መጀን ሲሉ
ካንቺ የሚደበቅ የለም አንዲት ነገር
ባልሰማሽው ቋንቋ ማፍቀሬን ልናገር
ከዘለላ ጸጉርሽ
በመላ ቆንጥሬ
ባንቺው መጀን እያልኩ
መጥቻለሁ ፍቅሬ
By @mad12titan
@getem
@getem
@paappii
❤ 32👍 25🔥 8😁 6
