352 831
Obunachilar
-4824 soatlar
+967 kunlar
+1 45930 kunlar
Postlar arxiv
#AAU
List of Graduate Programs for 2nd Semester 2025-26 AY Admission
List_of_Graduate_Programs_for_2nd_Semester_2025_26_AY_Admission.xlsx0.22 KB
❤ 10
Photo unavailableShow in Telegram
#ያኔት_ኮሌጅ
በ6 ኪሎ ካምፖስ እና በሰፈረ ሰላም ካምፓስ በምዝገባ ላይ ነን!
BSc Fields of Study:
→ BSc in Medical Laboratory Science
→ BSc in Pharmacy
→ BSc in Nursing
TVET Programs:
→ Nursing
→ Medical Laboratory
→ Pharmacy
→ Accounting and Finance
→ Hardware & Networking Service
→ Radiography
የCPD ማዕከል አገልግሎት
☎️ 0929969696 / 0996828282
አድራሻ፦
📍 መሳለሚያ ሰፈረ ሰላም ንጉሴ ቱሩፊ ህንፃ
📍 6 ኪሎ ካምፓስ ያሬድ ሙዚቃ ት/ቤት አጠገብ
Telegram: @Yanet6kiloc
❤ 40👍 1😱 1
Photo unavailableShow in Telegram
#JimmaUniversity
ጅማ ዩኒቨርሲቲ በአዲስ አበባ ካምፓሱ የድኅረ-ምረቃ ተማሪዎችን በመቀበል በድጋሜ ሥራ አስጀምሯል።
በርካቶች ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ በላኩት መልዕክት የካምፓሱን የአዲስ አበባ አድራሻ ጠይቀዋል፡፡
የካምፓሱ አድራሻ፦
ካዛንቺስ፣ ከራዲሰን ብሉ ሆቴል ፊት ለፊት፣ የቀድሞው ዘመን ባንክ ዋና ቢሮ የነበረበት
ስልክ ቁጥር
0978464748 / 0979464748
Email: info@alliance-academy.com
ካምፓሱ በፕሮጀክት ማኔጅመንትና ፋይናንስ፣ በቢዝነስ አስተዳደር እንዲሁም በሄልዝ ሞኒተሪንግ እና ኢቫሉዌሽን የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራም ተማሪዎችን ተቀብሏል፡፡
@tikvahuniversity
❤ 111👍 13👎 3😱 3
Photo unavailableShow in Telegram
#WerabeUniversity
2ኛው የኢትዮጵያ "አጠቃላይ" ዩኒቨርሲቲዎች ማኅበር ጠቅላላ ጉባኤ በወራቤ ዩኒቨርሲቲ ይካሔዳል፡፡
ጉባኤው ረቡዕ ታህሳስ 01/2018 ዓ.ም በወራቤ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት እንደሚካሔድ ተገልል፡፡
ማኅበሩ በመጋቢት 2017 ዓ.ም መመስረቱ ይታወሳል፡፡
@tikvahuniversity
❤ 31😢 5👍 3👎 3🙏 2
Photo unavailableShow in Telegram
የጥናታዊ ጽሑፍ አሰራር እና አቀራረብ (Research Methods and Analysis) ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን!
👉 Stata, SPSS እና NVivo ሶፍትዌሮችን በመጠቀም Quantitative እና Qualitative ሪሰርቾችን መስራትን በአንድ ላይ አካቶ የሚሰለጥኑበት
👉 ከፕሮፖዛል ቀረፃ ጀምሮ ሪሰርች አሰራር ቴክኒኮችን አካቶ እስከ ሪሰርች ሪፖርት አቀራረብ ያለውን አሰራር የሚሰለጥኑበት
👉 ልምድ ባላቸው የጥናታዊ ፅሑፍ ባለሙያዎች የሚሰጥ ስልጠና
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
Telegram: https://t.me/sagetraininginstitute
TikTok: https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
❤ 40👍 3🥰 2🙏 1
ናሽናል አቪዬሽን ኮሌጅ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን 1628 እጩ ተመራቂዎችን አስመርቋል።
የኮሌጁ ባለቤትና ስራ አስፈጻሚ ካፒቴን አበራ ኮሌጃቸው የስልጠና ዘርፎቹን በማስፋት በጤናው ዘርፍ በቅድመ ምረቃ ፕሮግራም በነርሲንግና በፋርማሲ ስልጠና መስጠት መጀመሩን ገልፀዋል።
ከሲቪል አቬሽን ባለስልጣን እውቅና ባገኘበት የአውሮፕላን ጥገና ቴክኒሻንነት (Aircraft maintenance technician) ተማሪዎችን ተቀብሎ በማሰልጠን የመጀመሪያውን ባች በማስመረቅ የመጀመሪያው የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋም መሆን እንደቻለ ተናግረዋል።
በቅርቡም ናሽናል ዩኒቨርስቲ ለመሆን እየሰሩ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
ለ12ኛ ዙር ከተመረቁት እጩ ሰልጣኞች ውስጥ በሁለተኛ ዲግሪ በኢንተርናሽናል ትሬድ፣ በኢኮኖሚክስ እና በሎጅስቲክስ፣ በሰፕላይ ቼይን ማኔጅመንት 130 እጩ ተመራቂዎች ናቸው።
በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም ደግሞ በአቬሽን ማኔጅመንት፣ በአካውንቲንግና ፋይናንስ፣ በሆቴል ማኔጅመንትና ማርኬቲንግ ማኔጅመንት 93 እጩ ተመራቂዎች ናቸው።
በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና በደረጃ IV በአካውንቲንግና ፋይናንስ፣ ፍሮንት ኦፊስ፣ ሀርድዌርና ኔትወርክ ሰርቪስ፣ማርኬቲንግና ሴልስ ማኔጅመንት ፣ ነርሲንግ እና ፋርማሲ 1035 ሰልጣኞች ተመርቀዋል።
በሠርተፍኬት ስልጠና በኤርክራፍትና ሜንቴናንስ ቴክኒሻን (ፓወር ፕላንት፣ኤር ፍሬም፣ አቪኦኒክስ)፣ ኤርላይን ካቢን ክሪው፣ ፍላይት ኦፕሬሽን ኦፊሰር እና በቲኬቲንግና ሪዘርቬሽን ያሰለጠናቸውን 370 ሲሆኑ በድምሩ 1628 እጩ ሰልጣኞች መሆናቸውን ገልጸዋል።
@tikvahuniversity
❤ 136👍 9😱 5👎 4🥰 1👏 1
Photo unavailableShow in Telegram
ጅማ ዩኒቨርሲቲ በአዲስ አበባ ካምፓሱ የድኅረ-ምረቃ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ጀምሯል።
ካምፓሱ በፕሮጀክት ማኔጅመንትና ፋይናንስ፣ በቢዝነስ አስተዳደር እንዲሁም በሄልዝ ሞኒተሪንግ እና ኢቫሉዌሽን የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራም ተማሪዎችን ተቀብሏል።
የአዲስ አበባ ካምፓሱ ከዚህ ቀደም ከ2005 እስከ 2011 ዓ.ም ከ1800 በላይ ተማሪዎችን አስተምሮ ማስመረቁ ተገልጿል።
ካምፓሱ በቀጣይ በሌሎች የትምህርት መስኮች ለማስተማር አዲስ አበባ ካዛንቺስ በሚገኘው የዩኒቨርሲቲው ካምፓስ ተማሪዎችን በመመዝገብ ላይ እንደሆነ ተገልጿል።
@tikvahuniversity
❤ 153👍 27👎 15😢 6😱 4👏 3
Photo unavailableShow in Telegram
#ጥቆማ
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ "የኒውክሊየር ኃይል ለዘላቂ ልማት በኢትዮጵያ" የሚል የውይይት መድረክ አዘጋጅቷል።
መድረኩ በኢትዮጵያ የኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽን፣ የዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኃይል ኤጀንሲ እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትብብር የተዘጋጀ ነው።
የዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኃይል ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሚካይል ቹዳኮቭ ገለጻውን የሚያቀርቡ ይሆናል።
መድረኩ ነገ ህዳር 29/2018 ዓ.ም ከሰዓት 8:00 ሰዓት በዋናው ግቢ የኢትዮጵያ ጥናት ኢንስቲትዩት ራስ መኮንን አዳራሽ ይካሔዳል።
@tikvahuniversity
❤ 124👍 9👎 2
#ጥቆማ
#UnityUniversity
ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ለጠቅላላ ትምህርት እና ለቴክኒክና ሙያ ዘርፍ በተለያዩ የሙያ መስኮች ብቃት ያላቸው ባለመያዎችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።
➤ የሥራ መደብ፦ መምህራንና የተለያዩ ሙያዎች
➤ ተፈላጊ ባለሙያዎች ብዛት፦ 43
➤ ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ፦ ዲፕሎማ (ለሁለት የሥራ መደቦች) እና የመጀመሪያ ዲግሪ
➤ የሥራ ልምድ፦ 2 ዓመት እና 5 ዓመት በላይ
➤ የሥራ ቦታ፦ ገርጂ አካዳሚ፣ ቡራዩ አካዳሚ፣ አዳማ ካምፓስ እና ደሴ ካምፓስ
የማመልከቻ ጊዜው የሚያበቃው፦
ታህሳስ 11/2018 ዓ.ም
የተቀመጡ መስፈርቶችን የምታሟሉና ፍላጎት ያላችሁ አመልካቾች ሲቪ እንዲሁም የትምህርት ማስረጃዎችን በመያዝ እስከ ታህሳስ 11/2018 ዓ.ም ድረስ ማመልከት እንደምትችሉ ተገልጿል፡፡
(ተጨማሪ መረጃ ከላይ ከተያያዘው የዩኒቨርሲቲው ማስታወቂያ ይመልከቱ፡፡)
@tikvahuniversity
❤ 148👍 20😱 6🙏 5👏 4😢 1
በርካታ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች “የቃልኪዳን ቤተሰብ ፕሮጀክት“ በ2018 ዓ.ም አስጀምረዋል፡፡
ፕሮጀክቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተግባራዊ ሆኖ ውጤታማ የሆነ ፕሮግራም ሲሆን፤ አዲስ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ ተማሪዎች ተቋሙ ከሚገኝበት ከተማ ነዋሪዎች ጋር ጥብቅ ትስስር የሚፈጥሩበት ነው።
ፕሮጀክቱን በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ለማስጀመር ሰላም ሚኒስቴር እና ትምህርት ሚኒስቴር ስምምነት ማድረጋቸው ይታወሳል።
ፕሮጀክቱን በዚህ ዓመት ካስጀመሩ በርካታ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል መቱ ዩኒቨርሲቲ አንዱ ነው፡፡
ዩኒቨርሲቲው የአንደኛ ዓመት ተማሪዎችን ከቃልኪዳን ቤተሰቦቻቸው ጋር የማስተሳሰር መርሐግብር አካሒዷል። ተማሪዎቹ እና የቃልኪዳን ቤተሰቦቻቸውን በፊርማ እና በቃለ-መሃላ ማስተሳሰር ተችሏል።
የቃልኪዳን ቤተሰብ ፕሮጀክት ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ወደ ዩኒቨርሲቲዎች በሚሔዱ ተማሪዎች መካከል የባህልና የቋንቋ ትስስርን ለማጠናከር እንደሚያግዝ ይታመናል።
ምስል፦ መቱ ዩኒቨርሲቲ
@tikvahuniversity
❤ 90👍 16🙏 2😱 1
Photo unavailableShow in Telegram
የቋንቋ ስልጠና ምዝገባ ላይ ነን!
ስልጠናዎቹ በሦስት ደረጃ ተከፍለው መሰረታዊ (A1 and A2)፣ ማዕከላዊ (B1 and B2) እና ከፍተኛ ደረጃ (C1 and C2) ይሰጣሉ።
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
የበለጠ ይጠብቁ ...
💥 ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 💥
Facebook: https://www.facebook.com/sagetraininginstitute
Telegram: https://t.me/sagetraininginstitute
TikTok: https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
❤ 53🥰 2👏 2👍 1
ለአማራጭ መምህርነት ስልጠና ምዝገባ አድርገዋል?
ትምህርት ሚኒስቴር በተለያዩ የሙያ ዘርፎች በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቀው የመምህርነት ሙያን መቀላቀል ለሚፈልጉ አመልካቾች የአንድ ዓመት ስልጠና ለመስጠት ከህዳር 16/2018 ዓ.ም ጀምሮ ምዝገባ እያደረገ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡
ስልጠናው በተመረጡ ስድስት ዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጥ ሲሆን፤ ስልጠናውን በቀን መርሐግብር የሚወስዱ ተማሪዎች የትምህርት ወጪያቸው ሙሉ ለሙሉ በመንግሥት እንደሚሸፈን ተገልጿል።
ኦንላይን የመመዝገቢያ ሊንኮች፦
➫ ጅማ ዩኒቨርሲቲ፦ https://portal.ju.edu.et
➫ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ፦ https://portal.hu.edu.et/Home/AvailablePrograms
➫ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፦ https://forms.gle/6t1BNV9S67oXwzBv9
➫ ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ፦ https://forms.gle/Y7Hksp5Ymk7Nx7d9A
➫ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ፦ https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSfQcnu1ThOSSsUp9d3XI80NszyyETOwtJPxWNRh68izA7Gd2A/viewform?usp=header
➫ መቐለ ዩኒቨርሲቲ፦
https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSdRwj89yQ50AiUeZZeDe8tr8aJ5GQZO4B0IqUVJzJJCNJzWPQ/viewform
🔔 የተቀመጡት ሊንኮቹ ይሰራሉ፡፡ ካስቸገሩዎት ግን ቆየት ብለው በተለያዩ ሰዓታት ይሞክሯቸው፡፡
@tikvahuniversity
❤ 148👎 25😱 5🙏 3👍 1👏 1
በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርት ለተመደቡ ተማሪዎች ዘግይተው ጥሪ ያደረጉ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን በመቀበል ላይ ይገኛሉ፡፡
ለታህሳስ የመጀመሪያ ሁለት ሳምንታት ጥሪ ያደረጉ ዩኒቨርሲቲዎች ያሉ ሲሆን፤ የተወሰኑ ዩኒቨርሲቲዎች አሁንም ለተማሪዎቻቸው ጥሪ አለማድረጋቸውን ቲክቫህ ታዝቧል፡፡ እነዚህ ዩኒቨርሲቲዎች ጥሪ ሲያደርጉ የምናደርሳችሁ ይሆናል፡፡
ምስል፦ ኦዳ ቡልቱም፣ ሠመራ፣ ደብረ ታቦር እና ወሎ ዩኒቨርሲቲዎች
@tikvahuniversity
❤ 69🙏 6
Photo unavailableShow in Telegram
3 ቀን ብቻ ቀረው! ቀጣይ ሚሊየነር ማን ይሆን? 🏆💚 ዛሬውኑ የበሽ ጥቅልን ይግዙ! ሚሊየነር የመሆን ዕድልዎን ያስፉ!
📲 የM-PESA መተግበሪያን አሁኑኑ ያውርዱ፦
https://onelink.to/ewsb22
የቴሌግራም ቦታችን፦
https://t.me/official_safaricomet_bot
ወደ *777*0# ይደውሉ ወይም በM-PESA የበሽ ጥቅል ይግዙ!
#SafaricomEthiopia
#MPESASafaricom
#furtheraheadtogether
#Besh
❤ 29👍 1😱 1🙏 1
Photo unavailableShow in Telegram
#DambiDolloUniversity
በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርት ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ታህሳስ 21 እና 22/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡
ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ ከ8-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ የ12ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ መጠኑ 3x4 የሆነ የቅርብ ጊዜ 8 ፎቶግራፍ፣
➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ እና የትራስ ልብስ፡፡
@tikvahuniversity
❤ 78👎 57👍 8
Photo unavailableShow in Telegram
የህንፃ ኤሌክትሪክ፣ የዲሽ መስመር እና የሲሲቲቪ (CCTV) ካሜራ ዝርጋታ ስልጠና ምዝገባ ላይ ነን!
🔔 ፈጥነው ይመዝገቡ!
👉 ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና
👉 Security Solution ዝርጋታ በተጨማሪነት የሚሰጥበት
👉 ከትምህርት ቢሮ የCOC ምዘና የተዘጋጀለት
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
Telegram: https://t.me/sagetraininginstitute
TikTok: https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
❤ 42🙏 4👍 3🥰 3
Photo unavailableShow in Telegram
#ጥቆማ
#UnityUniversity
ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ በከፍተኛ የትምህርት ዘርፉ የሚያገለግሉ በተለያዩ የሙያ መስኮች ብቃት ያላቸው መምህራንን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።
➤ የሥራ መደብ፦ አካዳሚክ አስተዳዳሪ፣ ረዳት ፕ/ር እና መምህራን
➤ ተፈላጊ ባለሙያዎች ብዛት፦ 24
➤ ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ፦ ከሁለተኛ ዲግሪ ጀምሮ
➤ የሥራ ልምድ፦ 2 ዓመት እና 5 ዓመት በላይ
➤ የሥራ ቦታ፦ ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ (አዲስ አበባ፣ አዳማ እና ደሴ)
የማመልከቻ ጊዜው የሚያበቃው፦
ታህሳስ 21/2018 ዓ.ም
የተቀመጡ መስፈርቶችን የምታሟሉና ፍላጎት ያላችሁ አመልካቾች ሲቪ እንዲሁም የትምህርት ማስረጃዎችን በመያዝ እስከ ታህሳስ 21/2018 ዓ.ም ድረስ ማመልከት እንደምትችሉ ተገልል፡፡
(ተጨማሪ መረጃ ከላይ ከተያያዘው የዩኒቨርሲቲው ማስታወቂያ ይመልከቱ፡፡)
@tikvahuniversity
❤ 117👎 20😢 1
Photo unavailableShow in Telegram
ዕድልዎን በ በሽ ይሞክሩ! ዛሬውኑ በሽ ይግዙ እና እስከ 1 ሚሊዮን ብር የማሸነፍ ዕድሎን ከፍ ያድርጉ።
*777*0# ላይ አሁኑኑ ይደውሉ! ዛሬውኑ የበሽ ጥቅሎችን እየገዙ በሽልማት ይንበሽበሹ!
📲 የM-PESA መተግበሪያን አሁኑኑ ያውርዱ፦ https://onelink.to/ewsb22
የቴሌግራም ቦታችን 👉🏽 https://t.me/official_safaricomet_bot
#SafaricomEthiopia
#MPESASafaricom
#furtheraheadtogether
#besh
❤ 17👏 1
Photo unavailableShow in Telegram
#FellowshipOpportunity
በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሜዲካል ኮሌጅ የውስጥ ደዌ ህክምና ትምህርት ክፍል ብቁ አመልካቾችን ለ2018 ዓ.ም Adult Nephrology Fellowship ፕሮግራም አወዳድሮ መቀበል ይፈልጋል።
ለዚህ ዓመት ሦስት (3) የፌሎውሺፕ ዕድሎች መኖራቸውን ኮሌጁ ገልጿል።
የማመልከቻ ጊዜ የሚያበቃው፦
ታህሳስ 06/2018 ዓ.ም
የቅበላ መስፈርት፦
➫ ከታወቀ የህክምና ትምህርት ተቋም በህክምና ዲግሪ ያለው ያላት,
➫ በ Internal medicine የሬዚደንሲ ፕሮግራም ያጠናቀቀ/ች፣
➫ Internist ሆኖ/ሆና ለሁለት ዓመት ያገለገለ/ች፣
➫ የቅበላ ምልመላ ሒደት የሚያጠናቅቁ፣
➫ በኢትዮጵያ የውስጥ ደዌ ህክምና ለመስጠት ተመዝግቦ ፈቃድ ያለው/ያላት፣
➫ ጥሩ አዕምሯዊና አካላዊ ጤና ያላት/ያለው፣
➫ አጭር የፍላጎት መግለጫ ማስገባት፣
የማመልከቻ አማራጮች፦
ፍላጎት ያላችሁ አመለልካቾች በ Internal ህክምና ትምህርት ክፍል በአካል በመቅረብ ወይም በኢሜል አድራሻዎች ayantu17@yahoo.com / lejahamza@yahoo.com ማመልከት ይችላሉ፡፡
አመልካቾች ሊያሟሏቸው የሚገቡ፦
➫ የማመልከቻ ደብዳቤ
➫ የቅርብ ጊዜ CV
➫ የትምህርት ማስረጃዎች (ዲግሪ እና የውጤት መግለጫ)
➫ ሁለት የድጋፍ ደብዳቤዎች
➫ የስፖንሰርሺፕ ደብዳቤ (በመንግሥት ስፖንሰር ለምትደረጉ)
➫ የድኅረ ምረቃ መግቢያ ፈተና (GAT) ውጤት
ለበለጠ መረጃ፦
➫ Dr. Ayantu Tesfaye 0911890635
➫ Dr. Leja Hamza 0917804057
የፅሑፍ እና የቃል ፈተና የሚሰጥባቸው ጊዜያት በቀጣይ ይገለጻል የተባለ ሲሆን፤ ትምህርት ታህሳስ 06/2018 ዓ.ም ይጀመራል ተብሏል፡፡
@tikvahuniversity
❤ 100😱 5👎 2🙏 2
Photo unavailableShow in Telegram
የድረ-ገጽ እና የሞባይል መተግበሪያ ማበልፀግ (Full-Stack Website and Mobile Application Development) ስልጠና ምዝገባ ላይ ነን!
👉 ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና
👉 ፕሮግራሚንግ ትምህርቶችን አካቶ ከ UI/UX ዲዛይን ጋር የሚሰጥ
👉 Front-end እና Back-end በአንድ ላይ እስከ Deployment ያካተተ
👉 በተግባር ድረ-ገጾች እና ሞባይል መተግበሪያዎችን እያበለፀጉ የሚሰለጥኑበት
☎️ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ እና ቁ.2 መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
Telegram: https://t.me/sagetraininginstitute
TikTok: https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
❤ 36🥰 4👏 2🙏 1

