Wasu Mohammed - ዋሱ መሀመድ
Kanalga Telegram’da o‘tish
እንኳን ደህና መጡ‼ 📌ማስታወቂያ ለማሰራት👉 @WasuMohammed 📌 ቻናሉን ለመቀላቀል 👉 @Wasulife ከልብ አመሰግናለሁ♥🙏
Ko'proq ko'rsatish2025 yil raqamlarda

241 196
Obunachilar
-96724 soatlar
+9 9047 kunlar
+19 31230 kunlar
Postlar arxiv
አምስቱ በእስራት ተቀጡ‼
በምዕራብ ሸዋ እና በሰሜን ሸዋ ሁለት ዞኖች ውስጥ የጠለፋና የእገታ ተግባር የፈፀሙ አምስት ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ።እንደ ምዕራብ ሸዋ ዞን የአደአ በርጋ ወረዳ አቃቢ ሕግ ፅህፈት መግለጫ
1ኛ ተከሳሽ ግርማ ሳሕሉ
2ኛ ተከሳሽ ፀጋ ሐይሉ
3ኛ ተከሳሽ ቶሊ ደጉ የተባሉ ሶስት ተከሳሾች ጥቅምት 11 ቀን 2018ዓም ከቀኑ ዘጠኝ ሠዓት ላይ ለአንደኛው ተከሣሽ በግዳጅ የትዳር አጋሩ ለማድረግ የአስራ አራት ዓመቷን ታዳጊ ከወፍጮ ቤት ስትመለስ ጠብቀው የጠለፋ ተግባር ፈፅመው ለማምለጥ ሲሞክሩ ተጠላፊዋ ባሰማችው የድረሱልኝ ጩኸት ስልጠና ላይ የነበሩ የፀጥታ አካላት ሰምተው ተከታትለው በቁጥጥር ስር ዉለዋል።
ሶስቱም ተከሳሾች በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኃላ በፖሊስ የምርመራ መዝገባቸው በበቂ ማስረጃ ተጣርቶ ለአቃቤ ሕግ የተላከ ሲሆን አቃቤ ሕግም በወንጀል ሕግ ቁጥር 587 ንዑስ አንቀፅ 1 ሴትን በመጥለፍ ወንጀል ክስ መስርቷል፡፡ ክሱን ሲከታተል የቆየው የአደአ በርጋ ወረዳ ፍርድ ቤት ጥቅምት 24-2018ዓ.ም በዋለው ችሎት በሶስቱም ተከሣሾች ላይ በእያንዳዳቸው ላይ በሉለት አመት ከሶስት ወር እስራት እንደተወሰነባቸው የአቃቤ ሕግ ፅህፈት ቤት መግለጫው አመልክቷል።
በተመሳሳይ በወረጃርሶ ወረዳ ሌንጮ ቦርሱ ቀበሌ የጦር መሣርያ በመታጠቅ የእገታ ተግባር ሲፈፅሙ የነበሩ ግለሰቦች በእስራት ተቀጠተዋል።እንደ ወረጃርሶ ወረዳ አቃቤ ሕግ ፅህፈት ቤት መግለጫ ደሬሣ ተሾመ እና ጀማል ደምሴ የተባሉ ሑለት ተከሳሾች ለግዜው እጃቸው ካልተያዙ ሑለት ግብረ አበሮቻቸው ጋር በመሆን የጦር መሣርያ በመታጠቅ መስከረም 25 ቀን 2018 ዓም ሁለት ግለሰቦችን አግተው አፍነው ለመውሠድ ሲሞክሩ በፀጥታ ስራ ላይ በተሠማሩ አካላት በቁጥጥር ስር ሊውሉ ችለዋል።
ፖሊስም በሁለቱ ተከሣሾች ላይ አስፈላጊውን ማስረጃ በማሠባሰብ አጠናክሮ የምርመራ መዝገቡን ለአቃቤ ሕግ የላከ ሲሆን አቃቤ ሕግም ከፖሊስ የተላከውን የምርመራ መዝገብ ተመልክቶ በጦር መሣርያ በመታገዝ የእገታ ተግባር መፈፀምን ጠቅሶ ክስ የመሠረተ ሲሆን ክሱን ሲከታተል የቆየው የወረጃርሶ ወረዳ ፍርድ ቤት ሕዳር 24 ቀን 2018ዓም በዋለው ችሎት አንደኛ ተከሣሽ ደሬሣ ተሾመ ስምንት አመት ከአራት ወር እስራት ሁለተኛ ተከሳሽ ጀማል ደምሴ በስድስት አመት ከስድስት ወራት እስራት እንዲቀጡ የወሠነ መሆኑን የአቃቤ ሕግ ፅህፈት ቤት መግለጫ አመላክቷል።
Via Dagu
❤ 84🙏 15🎉 4😱 3😍 3😢 1
00:31
Video unavailableShow in Telegram
MAF Chicken fried
Bole Michael Traffic Light Road to Bulbula, Beside Jafar Mosque.
0937162222
0938924444
1.55 MB
❤ 27👍 6😱 1💩 1
የአንዳንዱ ሰው ተግባር ይገርማል‼
ከመኪና ወንበር ጋር ተሰፍቶ ወደ አሜሪካ ሊሻገር የነበረው ግለሰብ አሳዛኝ ጉዞ‼
ሰሞኑን በሜክሲኮ እና በአሜሪካ ድንበር ላይ የተፈጸመው የኢንሪኬ አጊላር ካንቾላ ጉዳይ፣ ሰዎች ተስፋ ሲቆርጡ ለመሞከር ፈቃደኛ የሆኑትን የከፋ አደጋ ደረጃ የሚያሳይ አስደንጋጭ ክስተት ሆኖ ተዘግቧል። ታሪኩ የብዙዎችን ልብ የነካ ሲሆን፣ በአንድ ጊዜ አስገራሚነትንና ልብን የሚሰብር ሀዘንን የያዘ ነው።
ኢንሪኬ አጊላር ካንቾላ ወደ አሜሪካ ለመሻገር የሞከረው በእጅጉ አደገኛ በሆነ መንገድ ነበር። ራሱን ከመኪና ወንበር ጋር በቀጥታ በመስፋት ውስጥ በመደበቅ ድንበሩን ለማቋረጥ ሞክሮ ነበር። የድንበር ጠባቂ ኤጀንቶች ሚስጥሩን ያገኙበት ሁኔታም እጅግ የሚያስገርም ነው።
በመጀመሪያ፣ በመኪናው ወንበር ላይ ያለው ስፌት ከወትሮው የተለየና ያልተስተካከለ መሆኑን አስተዋሉ። ከዚህም በተጨማሪ ወንበሩ ከሚገባው በላይ ክብደት እንዳለው ተሰማቸው። ይህን ጥርጣሬ ተከትሎ ወንበሩን ሲከፍቱት፣ ኢንሪኬ አጊላር ካንቾላ ከመቀመጫው ፍሬም ውስጥ ተጣጥፎ ተገኝቷል።
ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት፣ ወንበሩ ሙሉ በሙሉ በእሱ ላይ ተገንብቶ እንደገና ስለተሰፋ፣ ካንቾላ ለመንቀሳቀስ ወይም በአግባቡ ለመተንፈስ የሚችልበት ቦታ በጭራሽ አልነበረውም። ይህ ሁኔታ ኢንሪኬ በጉዞው ወቅት ለሕይወት አስጊ በሆነና እጅግ አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ ውስጥ እንደቆየ ያሳያል።
ይህ አሳዛኝ ክስተት ሰዎች ያለ አማራጭ ሲቀሩ እና ጥግ ሲደርሱ የሚደርሱበትን ከፍተኛ የአደጋ ደረጃ በግልጽ ያሳያል። ድንበር ለማቋረጥ ተስፋ በመቁረጥና በጭንቀት ውስጥ ሆነው ራሳቸውን ለሞት አደጋ የሚያጋልጡ ስንት ሰዎች ይኖሩ ይሆን? የኢንሪኬ አጊላር ካንቾላ ታሪክ የብዙ ሰዎችን አይን የከፈተ እና ለረጅም ጊዜ በአዕምሮ ውስጥ የሚቆይ ልብ የሚነካ ታሪክ መሆኑ ተመላክቷል።
via menahariafm
Wasu Mohammed - Mereja
❤ 128😢 34👍 9😱 8💔 5😁 3🎉 3🙊 3👏 2🔥 1😍 1
Photo unavailableShow in Telegram
👌👌👌ቅንጡ አፓርትመንቶችንና የንግድ ሱቆችን ከጊፍት ሪል ስቴት!
👉400ሺ ቅድመ ክፍያ ጀምሮ
👉3ሚሊዮን የሚደርስ ቅናሽ
👉 5%-20 ቅድመ ክፍያ
👉55/45 የባንክ ብድር
👉 5%-21%ልዩ ቅናሽ
✔️ባለ 1መኝታ ፦ 64ካሬ- 80ካሬ
✔️ባለ 2መኝታ፦98ካሬ- 141ካሬ
✔️ባለ3መኝታ፦150ካሬ-205ካሬ
⛺️በለገሃር
📌ቦሌ አትላስ
📌በ22 ማዞሪያ
📌6ኪሎ
📌በሲኤምሲ
📌በፈረስ ቤት
በተጨማሪ
☑️የቆሻሻ ማስወገጃ
☑️ባካብ ጀኔሬተር
☑️በቂ ሊፍቶች
☑️ከአፀደህፃናት እሰከ መጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ፣
☑️የገበያ ማዕከላት
☑️የሳይክል መንገድና የስፖርት ማዕከል ያለው
☎️ 0963999444 or
0930649813
❤ 11👏 2🎉 2
‟...የኢትዮጵያን ጠላቶች እንደ ፀጉር ቅማል አንድ በአንድ እናራግፋለን...” ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ
ጠቅላይ ሚንስትሩ ይህንን የተናገሩት 20ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል በሆሳዕና ከተማ ዛሬ እየተከበረ ባለበት ስነ ስርዓት ላይ ነው።
ጠቅላይ ሚንስትር አብይ በበዓሉ ላይ ባደረጉት ንግግር "የኢትዮጵያን ጠላቶች እንደ ፀጉር ቅማል አንድ በአንድ እናራግፋለን.."ሲሉ ተደምጠዋል።በስም የጠቀሱት የለም።"ዴሞክራሲያዊ መግባባት ለሕብረ ብሔራዊ አንድነት'' በሚል መሪ ሐሳብ እየተከበረ በሚገኘው በዓል ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ ከፍተኛ የፌዴራል መንግሥት ሥራ ኃላፊዎች፣ የክልሎች ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ የከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች ተገኝተዋል።
1.40 MB
❤ 136🤣 72👏 18🍌 5😁 4🥴 4🏆 3🙉 2🙊 2👍 1😍 1
መቀሌ‼
ለቀናት ጠፍተው የነበሩት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሌተናል ጄኔራል ታደሰ ወረደ ዛሬ ከዓለም የምግብ ፕሮግራም ተወካይ ጋር በኢትዮጵያ በመቀሌ ተገናኝተው ታይተዋል።
በኢትዮጵያ የዓለም የምግብ ፕሮግራም ተወካይ ዝላታን ሚሊሲች ትግራይን በማገገሚያ ላይ ትኩረት አድርገው እየሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በዓለም የምግብ ፕሮግራም የሚከናወኑ ተግባራትን ለማየት ወደ ትግራይ በመምጣት ደስተኛ መሆናቸው ገልፀዋል።
በትግራይ መልሶ ማቋቋም ላይ ማተኮራቸውን እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።
ከትግራይ ማህበራዊ ደህንነት ጋር በመተባበር የሚከናወኑ ስራዎች የኑሮ ሁኔታን ለማሻሻል እና የመቋቋም አቅምን ለመጨመር ወሳኝ መሆናቸውን ተናግረዋል።
❤ 71🤔 6😁 4🎉 4👍 2😍 2🏆 2💔 2💩 1
00:37
Video unavailableShow in Telegram
ለሚኩራ ክ/ከተማ በሊዝ የተገኘ 126 ካሬ ለቅይጥ አገልግሎት የሚውል ሙሉ ሊዙን ጨምሮ በ5.6ሚሊየን ብር የግልዎ እንዲያደርጉ ተጋብዘዋል።
በ 0993930505 ይደውሉ
18.09 MB
❤ 21👍 4😁 4
00:48
Video unavailableShow in Telegram
የምክርቤቱ አባላት 'ቡጢ' ገጠሙ‼
ይህ ቅዳሜ ዕለት በሶማሊያ ምክር ቤት ሞቃዲሾ ያጋጠመ ክስተት ነው::የፓርላማ አባላቱ ከህግ ባለሙያዎች ጋር ቡጥ ገጥመው ታይተዋል።የግጭቱ ምክንያት አንድ መመሪያ ይፅደቅ አይፅደቅ በሚል የቃላት አለመግባባት እንደተከሰተ ታውቋል።
14.78 MB
😁 113❤ 34🤣 13👍 8👏 7😢 4🏆 3🙈 3😍 2🙊 2
Photo unavailableShow in Telegram
📍አድራሻ - በመሀል ከተማ በኮሊደር ልማቷ ባሸበረቀችው ለቡ ማብራት-ሀይል
💥ሊኖሩበት ቢፈልጉ ሰላሚዊ መንደር፣ ሊያከራዩት ቢያስቡ በጥሩ ወጋ እና መልሰው እንኳን ቢሸጡት በደንብ የሚያተርፉበት!!
💥ስቱዲዮ (59 ካሬ) በ 260ሺህ ብር
💥ባለ አንድ መኝታ (77.3ካሬ) በ 341ሺህ ብር
💥ባለ ሁለት መኝታ (127.2ካሬ) በ 561ሺህ ብር
💥ባለ ሦስት መኝታ (150.5 ካሬ) በ 664ሺህ ብር
💥 ባለ አራት መኝታ (194 ካሬ) በ 855 ሺህ ብር ቅድመ ክፍያ ብቻ
💥 እንዲሁም እስከ 295ካሬ ስፋት ያላቸው ፔንትሃውስ ቤቶችን በምቹ አከፋፈል በተመጣጣኝ ዋጋ ከኛ ያገኛሉ
በተጨማሪም ከ27 - 190 ካሬ ስፋት ያላቸው ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ የንግድ ቦታዎችን እንደምርጫዎ አቀርብንሎት!
✍️ በ10% ቅድመ ክፍያ ብቻ
✍️ ከ 60% የባንክ ብድርጋር እስከ 25 ዓመት
✍️ በተጨማሪም እስከ 35% እንደ አከፋፈሎ ልዩ ቅናሽ ይደረግሎታል
✍️ ሁሉም ቤቶች ተጨማሪ የሰራተኛ ክፍል, ስቶር እና የላውንድሪ ክፍሎች ያሏቸው።
✍️ መንደራችን በውስጥ የያዛቸው ልዩ ልዩ የጋራ መገልገያዎች:
💥 አራት የመንገደኞች እና አንድ የእቃ አሳንሰር
💥 አምስት የዋና ገንዳዋች
💥 አስተማማኝ ና ደህንነቱ የተጠበቀ ሰፊ የመኪና ማቆሚያ
💥 የኤሌክትሪክ መኪና ኃይል መሙያ መሳሪያ
💥 ለተለያዩ ዝግጅቶች የሚሆን የጋራ ቦታ
💥 የቆሻሻ መጣያ (Garbage shooter)
💥 ዘመናዊ የገበያ ማዕከሎች
@Dmcreales
ለበለጠ መረጃ
☎️ 0940625843
❤ 27👏 2👍 1
ሰሞኑን መነጋገሪያ የሆነው ደቡብ ወሎ ለገሂዳ አከባቢ ከመሬት እየፈለቀ የሚገኘውን ድፍድፍ ነዳጅ በተመለከተ:-
📌 በለገሂዳ የተራራማውን ምድር ጥሶ ብቅ ያለው ድፍድፍ ነዳጅ ከዚህ ቀደም Falcon የተሰኘ የነዳጅ አውጪ ኩባኒያ ከመንግስት ጋር ተነጋግሮ የጥናት ሂደት ላይ እያለ ባልታወቀ ምክንያት ቆሟል።
📌 ወሎ ዩኒቨርስቲ በአንድ ወቅት አድርጎት በነበረ ጥናት የነዳጅ ክምችቱ በአንድ ቦታ ከሚገኙ ከፍተኛ የሚባል ተርታ እንደሚመደብ ሲገለፅ ነበር።
📌በደቡብ ወሎ ዞን ለገሂዳ ወረዳ የነዳጅ ክምችት በተፈጥሮ አስገዳጅነት ከከርሰ ምድር በላይ መውጣት ከጀመረ ከ7 አመታት በላይ ቢያስቆጥርም እስካሁን ጥቅም ላይ እንዲውል ባለመሰራቱ አሁንም የነዳጅ ድፍድፉ መሬቱን ሰንጥቆ እየወጣ መሆኑን የደቡብ ወሎ ዞን ማዕድን ሀብት ልማት መምሪያ የማዕድን ስራዎች እና ፍቃድ አስተዳደር ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ጀማል እንዲሪስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ከሠጡት ማብራሪያ ተመልክቻለሁ።
📌ይህን የነዳጅ ክምችት አዋጪነቱ ተጠንቶ ጥቅም ላይ እንዲውል ለማድረግ በተደጋጋሚ ለማዕድን ሚኒስቴር ጥያቄ ሲያቀርቡ መቆየታቸውን ተናግረዋል።
📌አቶ ጀማል እንዲሪስ -" ከዚህ በፊት በወረዳው ያለውን የነዳጅ ክምችት ጥቅም ላይ ለማዋል የተለያዩ ፕሮጀክቶች በግል ተቋማት እና በመንግስት ተቋማት ሲሞካከሩ ነበር። እኛም በየጊዜው ጉዳዩ የሚዲያ ሽፋን እንዲያገኝ ስናደርግ ቆይተናል።
እኛ ማድረግ የምንችለው ጥናት እንዲካሔድበት ግፊት ማድረግ ነው፣ በዚህም መሰረት በ 2011 ዓ.ም ማዕድን ሚኒስቴር በጉዳዩ ላይ ውይይት አካሒዶ ነበር። በሰአቱም ሀብቱ እንዳለ ከመሬት በላይ በምልክት ተጋልጦ እየታየ ስለሆነ ሀገራችን እና የአካባቢውን ማህበረሰብ እንዲጠቀም ለማድረግ ጥናት እንዲካሔድ ጥያቄ አቅርበንላቸው ተቀብለውን ነበር። ጥናት ለማካሔድም እቅድ መያዙን ነግረውናል፣ ከዛን በሗላ ግን ምንም አይነት እንቅስቃሴ እየተደረገ አይደለም።
እንደዞን አሁን ያለን ሃሳብ ጉዳዩ በተለያዩ ሚዲያዎች ሽፋን እንዲያገኝ ማድረግ እና ከላይ ያሉት የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት ሰጥተው ጥናት እንዲያደርጉ ጫና ማሳደር ነው። እኛ አቅደን የማንሰራው ጉዳይ ስለሆነ ፍላጎት እና ሀሳብ ነው ያለን። ምክንያቱም ይህን የመስራት ስልጣን የተሰጠው ማዕድን ሚኒስቴር ብቻ ነው።
ነዳጁ በትክክል ወጥቶ መሬት ላይ እየታየ ነው፣ በተሰነጠቁ መሬቶች አማካኝነት የወጣው ነዳጅ በአካባቢው የሚገኙ ውሃዎችን እየበከለ ነው። በዚህ የነዳጅ ክምችት ላይ ክልሉም፣ ዞናችንም፣ ወረዳውም ፍላጎታችን ተመሳሳይ ነው።
ወሎ ዩኒቨርሲቲ ከዚህ በፊት የተለያዩ ባለሙያዎችን እና ተማሪዎቹን በስፍራው በመውሰድ ምልከታ አድርጎ ነዳጅ መሆኑን አረጋግጧል። በወቅቱ ባለሙያዎቹ አካባቢው በተዳከመ የመሬት Fault ነዳጁ ወደ ውጪ እንደወጣ ነው ያስረዱት። ነዳጅ ስለመሆኑ የሚያጠራጥር ነገር የለም " ሲሉ ለቲክቫህ ተናግረዋል።
❤ 273👍 41👏 19🙏 17😍 13🙈 7🤝 7😎 4🏆 3💯 2
Ads.
ይህ ከስር ያለው ሚስጥሮች የሚወጡበት ወሳኝ ቻናል ነው።ገብተው ሰብስክራይብ ካደረጉ አነጋጋሪ መረጃዎችን በቅድሚያ ያገኛሉ።👇
https://www.youtube.com/channel/UCmFPL7JZ5i5utdYQXcnPRQw
https://www.youtube.com/channel/UCmFPL7JZ5i5utdYQXcnPRQw
❤ 17
መፈንቅለ መንግስት ተካሄደ‼
በቤኒን የሀገሪቱ ጦር ስልጣን መቆጣጠሩን አስታወቀ።
የቤኒን ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ታሎን በሀይል ከስልጣን መውረዳቸው ተገልጿል።
ጥቂት ወታደራዊ አመራሮች በብሄራዊ ቴሌቪዥን ቀርበው ባደረጉት ንግግር ህገመንግስቱ መታገዱን፣ ሀገሪቱን የሚያዋስኑ ድንበሮች መዘጋታቸውን እና በረራዎች መቆማቸውን ተናግረዋል።
2.41 MB
❤ 105👏 20🕊 12👍 6😢 2🎉 2
Photo unavailableShow in Telegram
ከቃል በላይ ያስረከብናቸው ከ 8 በላይ ሳይቶች ማሳያ ናቸው
#ቴምርሪልስቴት
‼️ሳር ቤት ቫቲካን
🎯65/35 አከፍፈል
👉2መኝታ 81ካሬ ሙሉ ክፍያ 6ሚሊዮን
👉2መኝታ 106ካሬ ሙሉ ክፍያ 7.9ሚሊዮን
👉3መኝታ 139ካሬሙሉ ክፍያ 10.3ሚሊዮን
🎯ቀስ ብሎ ለሚከፍል
👉2መኝታ 81ካሬ
20%ቅድመ ክፍያ 1.86ሚሊዮን
ሙሉ ክፍያ 9.3ሚሊዮን
👉2መኝታ 106ካሬ
20% ቅድመ ክፍያ 2.4ሚሊዮን
ሙሉ ክፍያ 12.1ሚሊዮን
👉3መኝታ 139ካሬ
20%ቅድመ ክፍያ 3.1ሚሊዮን
ሙሉ ክፍያ 15.9ሚሊዮን
‼️አዋሬ
🎯65/35 አከፍፈል
👉 ባለ 1 መኝታ = 78ካሬ = 5.5ሚሊዮን
👉 ባለ 3 መኝታ = 117ካሬ = 8.3ሚሊዮን
👉 ባለ 3 መኝታ = 137ካሬ = 9.7ሚሊዮን
🎯ቀስ ብሎ ለሚከፍል
👉 1መኝታ 78ካሬ
20%ቅድመ ክፍያ 1.7ሚሊዮን
ሙሉ ክፍያ = 8.5ሚሊዮን
👉3 መኝታ 117ካሬ
20%ቅድመ ክፍያ 2.6ሚሊዮን
ሙሉ ክፍያ 12.9ሚሊዮን
👉 157ካሬ =
20% ቅድመ ክፍያ 3.4ሚሊዮን
ሙሉ ክፍያ = 17.2ሚሊዮን
#ልብይበሉ
#ቀሪውን 80% በ 15ዙር ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት
* 30% እና ከዚያ በላይ ለሚከፍሉ፣ ከከፈሉት ላይ 15%_25% ቅናሽ አዘጋጅተናል
ለበለጠ መረጃ
👇👇👇👇👇👇
+251939770177
+251996856273
https://t.me/TemerRealEstateSalesConsultant
WhatsApp. https://wa.me/251939770177
❤ 22👏 2👍 1🔥 1💯 1
"ቤተክርስቲያኗ ከሻብያ ጋር በማበሯ እርምጃ ተወስዷል" የስዊድን ደህንነት
📌የስዊድን መንግስት በስዊድን ለኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሚያደርገውን ድጋፍ በማቋረጥ እርምጃ መውሰዱን አሳውቋል።
📌የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በስዊድን የኤርትራ መንግስት ጋር ግንኙነት በመፍጠር በስዊድን የሚኖሩ ዜጎችን መብትና ነጻነት በሚጥስ ተግባር ላይ በመሳተፋቸው እንዲሁም መንግስት የሚሰጣቸውን ድጎማ በተዘዋዋሪ ለሻብያ እንደሚያስተላልፉ የስዊድን ደህንነት አገልግሎት አረጋግጧል። ይህን ተከትሎም ከመንግስት ይሰጣቸው የነበረው ዓመታዊ ድጎማ እንዲቋረጥ መወሰኑን ስዊድን ሄራልድ አስነብቧል።
📌የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በስዊድን በዓመት እስከ 800,000 ክሮነር ($85,100) ገደማ ድጎማ ከስዊድን መንግስት ስታገኝ መቆየቷን መረጃዎችን ዋቢ በማድረግ ጋዜጣው አስነብቧል።ከሻዕቢያ ጋር ንክኪ ያለው ማንኛውም ግለሰብ፣ ቡድን እና ተቋም በአውሮጳ ሃገራት እየታደነ ለፍርድ እየቀረበ ነው።
❤ 109👍 16🙏 9🎉 7👏 6😱 4💔 4🥰 2😢 2
Ads
መሳቅ ከፈለጉ ብቻ ወደ እኛ ኑ አርሂቡ ብለናል‼
እኛ ጋር የምትመጡት ዘና ለማለትና ለመሳቅ ብቻ ነው።ግን ሰብስክራይብ ማድረግ እንዳይረሳ።
https://youtu.be/arxRKpyulvE
ለቀጣይ ለበለጠ መዝናናት ከፈለጋችሁ ብቻ Subscribe አድርጉን።ሊንኩ ከስር ተቀምጧል።
👇 👇 👇 👇
https://youtube.com/@mewamedia?si=WqTGSX0f_-rUm3ua
Mewa Media
የሳቅ ምንጭ
❤ 14
Photo unavailableShow in Telegram
ቫይረስ ወደ ስልኮች እና ኮምፒውተሮች የሚገባባቸው መንገዶች‼
መረጃው ሼር ይደረግ
📌 በዚህ የቴክኖሎጂ ዘመን ኮምፒውተራችን እና ስማርት ስልኮቻችን የሕይወታችን ማዕከል ናቸው። ነገር ግን፣ ጠላፊዎች (Hackers) የእኛን መረጃ እና ንብረት ለመስረቅ የሚጠቀሙባቸው ስውር መንገዶች አሉ።
📌 ቫይረሶችና ማልዌሮች (Malware) ሳናውቅ ወደ መሣሪያችን ሲገቡ፣ ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጭ ሊያደርጉን አልያም ጠቃሚ መረጃዎቻችንን ለሌሎች አሳልፈው ሊሰጡ ይችላሉ።
📌 በተቻለ መጠን ቫይረሶች ወደ ኮምፒውተራችን ገብተው ጉዳት እንዳያደርሱብን ጥንቃቄ ማድረግ ወሳኝ ነው።
🔰 ኮምፒውተር ቫይረሶች የሚገቡባቸውን እና ልንጠነቀቅባቸው የሚገቡ 6ዋና ዋና መንገዶች እነሆ ፦
1. ያልተነበበ የማንቂያ መልዕክት (Notifications) ወጥመድ 🙄
📌 ቫይረስ ከሚገባባቸው ዋነኛው መንገድ የማንቂያ መልዕክቶችን (Pop-up/Notifications) ሳናነብ መክፈት ነው።
📌 ለምሳሌ Your System is Outdated (ስርዓትዎ አርጅቷል) ወይም A unique plugin is necessary (ልዩ ተጨማሪ ፕሮግራም ያስፈልጋል) የሚሉ አስፈሪ ማስታወቂያዎች ሲመጡ የደህንነት ስጋት መኖሩን ሳናውቅ እንዲከፈት የሚጠይቁትን ቅደም ተከተል መከተል። እነዚህ ብዙውን ጊዜ መሣሪያውን ወደ አደገኛ ድረ-ገጽ ይመሩታል።
📌 2. ከማይታመን ምንጭ የወረዱ ሶፍትዌሮች
📌 ከኢንተርኔት የምናወርዳቸው 'በነፃ የሚለቀቁ' ወይም የተሰነጠቁ (Cracked) ፕሮግራሞች ከታማኝ ምንጮች (Official Websites) ካልተገኙ፣ ቫይረስ የመያዝ ዕድላቸው ከፍተኛ ነው።
📌 ወሳኝ ጥንቃቄ ፕሮግራሙን ከጫንን (Install) በኋላ በተደጋጋሚ እንድንጭናቸው የሚጠይቁንንና እያንዳንዱን የኢንተርኔት እንቅስቃሴያችንን ለመረጃ በርባሪዎች አሳልፈው የሚሰጡ ፕሮግራሞችን በፍፁም መጫን የለብንም።
📌 3. ላኪያቸው የማይታወቁ የኢሜይል መልዕክቶች (Phishing)
📌 ማንኛውንም ላኪያቸውን የማናውቃቸውን የኢሜይል መልዕክቶች (በተለይ Attachment- የተያያዘ ፋይል ካላቸው) መክፈት።
📌 ጠላፊዎች ራሳቸውን እንደ ባንክ፣ መንግስት ወይም የታወቀ ኩባንያ አስመስለው አስቸኳይየሚል ርዕስ በመጠቀም አደገኛ ሊንክ ወይም የቫይረስ ፋይል (ለምሳሌ Word/Excel ፋይል) ይልካሉ።
📌ማንኛውንም ኢሜይል ከመክፈታችን በፊት የላኪውን አድራሻ (Email Address) በትክክል መፈተሽ እና የተያያዘ ፋይል ካለ በኦንላይን አንቲቫይረስ መፈተሽ ወሳኝ ነው ።( የአርቲስት እገሌን ጉድ ለማየት ይጫኑ የሚሉት link አትንኩ 😀)
4. የድሮ ሶፍትዌሮችን አለማዘመን (Outdated Software)
📌 የኮምፒውተር ኦፕሬቲንግ ሲስተም (Windows, macOS)፣ የኢንተርኔት አሳሾች (Chrome) እና አንቲቫይረስ ሶፍትዌሮችን በየጊዜው አለማሳደግ (Update አለማድረግ) ችግር ላይ ይጥላል።
📌 አምራች ኩባንያዎች የሚያወጡት አዲስ ዝመና (Update) ከቫይረስ የሚከላከሉ አዲስ የደህንነት በሮች በመዝጋት የተበላሹ ክፍሎችን ለማስተካከል ነው። የድሮ ሶፍትዌሮች ደግሞ ጠላፊዎች የሚያውቁት ክፍት system አላቸው ።
5. በ virus የተጠቁ storage መሳሪያዎችን መጠቀም
📌 ከተበከሉ ኮምፒውተሮች ጋር የተገናኙ ውጫዊ ስቶሬጅ መሳሪያዎችን (ሚሞሪ፣ ፍላሽ ዲስክ፣ ውጫዊ ሃርድ ዲስክ) ኮምፒውተራችን ላይ መሰካት።
📌 አንዳንድ ቫይረሶች በፍላሽ ዲስክ ውስጥ በድብቅ በመቀመጥ ራሳቸውን በሌላ ኮምፒውተር ላይ ወዲያውኑ ይጭናሉ። ስለዚህ፣ ማንኛውንም ውጫዊ መሳሪያ ከመክፈትዎ በፊት አንቲቫይረስ ስካን ማድረግ የግድ ነው።
6. ደካማ የይለፍ ቃሎች እና የማህበራዊ ምህንድስና (Social Engineering)
📌 ቀላል የይለፍ ቃሎችን (ለምሳሌ 123456) መጠቀም ጠላፊዎች የመገመት ዕድል ስለሚሰጣቸው በቀላሉ ገብተው ቫይረስ መጫን ይችላሉ።
📌 የማህበራዊ ምህንድስና ፦ ( Social engineering የሚባለው ) ጠላፊዎች እንደ ጓደኛ ወይም ባንክ ሰራተኛ መስለው በመደወል ወይም በመልዕክት ፓስወርድዎን እንዲነግሯቸው ወይም ኮድ እንዲሰጧቸው ማታለል። ይህ የቴክኖሎጂ ጥቃት ባይሆንም፣ ቫይረስ ለማስገባት መንገድ ይከፍታል ።
Via AndebetMezin
#ዋሱመሐመድ
አሁናዊ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን join በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
❤ 91👍 17👏 6🤣 5😱 4😍 2
Photo unavailableShow in Telegram
👌👌👌ቅንጡ አፓርትመንቶችንና የንግድ ሱቆችን ከጊፍት ሪል ስቴት!
👉400ሺ ቅድመ ክፍያ ጀምሮ
👉3ሚሊዮን የሚደርስ ቅናሽ
👉 5%-20 ቅድመ ክፍያ
👉55/45 የባንክ ብድር
👉 5%-21%ልዩ ቅናሽ
✔️ባለ 1መኝታ ፦ 64ካሬ- 80ካሬ
✔️ባለ 2መኝታ፦98ካሬ- 141ካሬ
✔️ባለ3መኝታ፦150ካሬ-205ካሬ
⛺️በለገሃር
📌ቦሌ አትላስ
📌በ22 ማዞሪያ
📌6ኪሎ
📌በሲኤምሲ
📌በፈረስ ቤት
በተጨማሪ
☑️የቆሻሻ ማስወገጃ
☑️ባካብ ጀኔሬተር
☑️በቂ ሊፍቶች
☑️ከአፀደህፃናት እሰከ መጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ፣
☑️የገበያ ማዕከላት
☑️የሳይክል መንገድና የስፖርት ማዕከል ያለው
☎️ 0963999444 or
0930649813
❤ 19👍 3🔥 1👏 1
00:36
Video unavailableShow in Telegram
በለቅሶ የተገለፀው ድጋፍ ብዙዎችን ያነጋገረ ቢሆንም እኝህ የጉለሌ ክ/ከተማ ነዋሪ :-
"መንግስታት አይቻለሁ! እንደዚህ ወርዶ በሚንስትር ደረጃ፣ በካቢኔ ደረጃ ያናገረን የለም። መንግስት መሬት ላይ እየሰራ ያለው አስመስዬ እየደገፍኩ ሳይሆን ከልቤ ነው የምደግፈው።" በማለት እየተሰራ ያለውን ልማት እያለቀሱ አድንቀዋል።
6.44 MB
🤣 224❤ 83🤪 22🍌 14😁 13👍 12👏 10🙊 6😱 5💔 1
አስፈራርቶ ከሾፌሮች ገንዘብ ሲቀበል የነበረው ተቀጥቷል‼
እንጨት ጠርቦ የጦር መሣሪያ በማስመሰል ሹፌሮችን በማስፈራራት አስገድዶ ገንዘብ የተቀበለው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ።
ሚያዚያ 18/08/2016 ዓ. ም ከቀኑ በግምት 10፡00 ሰዓት ሲሆን በ አነደድ ወረዳ ጉዳለማ ቀበሌ ማይት ተብሎ ከሚጠራው ልዩ ቦታ ተከሳሽ አቶ ትትናው ዘላለም ከደብረ ማርቆስ ወደ ደጀን እና ከደጀን ወደ ደብረማርቆስ እየሄዱ የነበሩ በስምና በታርጋ ካልተለዩ የጭነት መኪና አሽከርካሪዎች ገንዘብ አስገድዶ እየዘረፈ ባለበት በመንግስት የፀጥታ ሃይሎች በቁጥጥር ስር እንደዋለ የወረዳው ፖሊስ ፅ/ቤት አስታውቋል።
ተከሳሹ በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን እና በሙሉ ሀሳቡና በፈቃዱ የወንጀሉን ድርጊት ውጤት በመቀበል እንጨት ጠርቦ የጦር መሳሪያ አስመስሎ በመያዝ በሀይል በማስገደድ ተሽከርካሪዎችን መንገድ ዘግቶ በማስቆም በመዝርፍና አስገድዶ ገንዘብ በመቀበል በፈፀመው ወንጀል ተከሷል።
ተከሳሽ ትትናው ዘላለም በአነደድ ወረዳ በወንጀል ምርመራ ክፍል ምርመራ ሲጣራበት ቆይቶ የምርመራ መዝገቡ ለሚመለከተው የፍትህ አካላት በመላክ ለአብክመ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ደብረ ማርቆስ ምድብ ችሎት ዛሬ ህዳር 26/2018 ዓ/ም በዋለው ችሎት አቶ ትትናው ዘላለም የተባለው ግለሰብ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ 2 ዓመት ከ2 ወር እስራት እንደተወሰነበት ተገልፆል።
መረጃው የምስራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምርያ ሚዲያና ኮሙንኬሽን ነው።
❤ 82😁 34👍 12👏 8👌 3😱 2🤩 1💔 1
