ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ
Kanalga Telegram’da o‘tish
2025 yil raqamlarda

133 768
Obunachilar
-1024 soatlar
-1197 kunlar
-58130 kunlar
Postlar arxiv
ሰሞኑን የመንግስት ሚድያዎች እያበዱበት ባለው ጉዳይ ዙርያ አስተያየት ብትሰጥ ላላችሁኝ፣ እኔ የሚድያ እንጂ የድራማ ባለሙያ ስላልሆንኩ ሙያዊ አስተያየት ለመስጠት እቸገራለሁ።
ለመሸፈን የተፈለገ ነገር እንዳለ ግን እርግጥ ነው፣ እንደርስበታለን።
@EliasMeseret
👍 2 153😁 408❤ 168🙏 58😢 28🤔 21😱 5
Photo unavailableShow in Telegram
ጉዳዩን ለማስተባበል የተሄደበት ርቀት እንደ ሀገር የገባንበትን ዝቅጠት ያሳያል!
ማስተባበያው ወጣቷ የዩኒቨርስቲው ተማሪ አልነበረችም አይለንም፣ ብቻ "ዩኒቨርሲቲው የፋርማሲ ትምህርት ሲሰጥ በ2013 የሁለተኛ ዓመት ተማሪ እንዳልነበረው ይገልጻል" ብሎ ለጭብጡ አላስፈላጊ የሆነ ነገር መዞ ክስ ለመመስረት ይዝታል። ለመሆኑ እንደ ተቋም ተማሪዎቹ ሲታገቱ ምን አደረገ?
ኢቢኤስ ላይ የተደረገውን ማስፈራራት ሳይ ትዝ ያለኝ ይህን ዜና በወቅቱ ለ Associated Press ስፅፍ የደረሰብኝ ወከባ ነበር: https://apnews.com/general-news-ab7fd681148f0b7317beaa3b19c9ad1a
አንዴ የታገተ ተማሪ የለም፣ ሌላ ግዜ በሙሉ ተለቀዋል፣ ቆይተው ደግሞ ስድት ብቻ ነው የቀሩት እያሉ ጉዳዩን ሲያምታቱ የነበሩት የመንግስት ባለስልጣናት ነበሩ፣ እኛንም ቢሯቸው እየጠሩ ዜና መስራት እንድናቆም ሲጠይቁ ነበር። አሁን ጉዳዩ ቆይቶ ለህዝብ ሲደርስ ደግሞ ሌላ ማስፈራርያ።
በዚህ አካሄዳቸው ልጅቱንም ሊያስፈራሩ ይችላሉ፣ ስለዚህ በቅርብ እንከታተላለን። ልጅቱን ለማገዝም እንቅስቃሴ እናደርጋለን፣ እስካሁን በስልኳ ለማግኘት ያደረግኩት ሙከራ አልተሳካም።
በነገራችን ላይ፣ የእገታ ዜና ሰልችቶን ዜና ሳይመስለን የምናልፍበት እጅግ አሳዛኝ ሁኔታ ተፈጠረ እንጂ በየሳምንቱ የሚታገቱትም እጣ ፈንታቸው ይሄው የልጅቷ ነው። ባለፈው ሳምንት ብቻ ሁለት ሙሉ አውቶቡስ ህዝብ ታግቷል፣ የሁለት አመት ህፃን ልጅን ጨምሮ።
በቃችሁ ይበለን።
@EliasMeseret
👍 1 755😢 765❤ 111🙏 65😱 40😁 23🤔 15🕊 15
Photo unavailableShow in Telegram
ይህን እገታ ይበልጥ አሳዛኝ የሚያደርገው ለታገቱ ቤተሰቦቻቸው ገንዘብ የሚሰበስቡ ሰዎችን የመንግስት አካላት "ጠላት ልትረዱበት ነው" እና "የታገተ የለም፣ ስም ልታጠፉ ነው" እያሉ ማዋከባቸው ነው።
ይህን የዜጎች ሰቆቃ እያየን ነው የባህር በር፣ የኮሪደር ልማት... ወዘተ ስንባል የማይገርመን።
First things first... የዜጎችን ደህንነት መጀመርያ አስጠብቁ!
የዜናው ሊንክ: https://t.me/meseretmedia/853
@EliasMeseret
😢 1 026👍 405❤ 54🤔 27🙏 25🕊 8😁 4
Photo unavailableShow in Telegram
አለም አቀፍ ተቋማትን በመዝለፍ እና ከሀገሪቱ በማባረር፣ አለም አቀፍ ሴራዎች እየተካሄዱበኝ ነው በማለት በመግለፅ እንዲሁም ለአለም አቀፍ ህግጋት እና መርሆች ደንታ እንደሌለው ለበርካታ አመታት ሲገልፅ የነበረው የኤርትራ መንግስት አሁን ላይ አለም አቀፍ ተቋማትን ድረሱልኝ እያለ ነው።
የሆነ ነገርማ አለ!
@EliasMeseret
😁 409👍 147❤ 22🤔 22😢 10
Photo unavailableShow in Telegram
አቤት ክፋት 😅... Who did this?
@EliasMeseret
😁 720👍 98🤔 59❤ 33🕊 24😢 5
Photo unavailableShow in Telegram
ህዝብ ተራብኩ፣ ተቸገርኩ፣ መኖር ከበደኝ፣ ልጆቼን ማስተማር አቃተኝ ሲል ይህን የእዳ መአት በየግዜው መጫን ማለት ህብረተሰቡ ከዳቦ ውጭ እንዳያስብ አርጎ ለመግዛት ካልሆነ ምን ይባላል?
በየሰፈሩ ለኮሪደር ልማት፣ ለብልፅግና ፅ/ቤት ማሰርያ፣ ለቀይ መስቀል፣ ለሚሊሺያ፣ ለመንገድ ግንባታ... ወዘተ እየተባለ ፍዳውን የሚያየው ሳያንስ አሁን ደግሞ አደጋ ለመከላከል።
@EliasMeseret
😢 1 521👍 318❤ 78🤔 64😁 50😱 21🙏 15🕊 15
Photo unavailableShow in Telegram
ለሁለት እና ሶስት አመታት ጠፍተው የነበሩ የኤርትራ የሶሻል ሚድያ አክተሮች የሰሞኑን የቀጠናውን ውጥረት ተከትሎ አቧራቸውን እያራገፉ ብቅ ብቅ እያሉ ይገኛሉ
አብዛኞቹ ሀሰተኛ መረጃ በማሰራጨት፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ባለስልጣናትን እና ተቋማትን በማጥቃት እና ከትግራይ ተቃናቃኝ ቡድኖች አንዱን (በዶ/ር ደብረፅዮን የሚመራውን) በመደገፍ ላይ ያተኮሩ ናቸው።
ከዚህ በፊት የኢትዮጵያን መንግስት ስንተች የነበረው የውጭ ሀይል ጋብዞ የራሱ ህዝብ ላይ ስላዘመተ ነው፣ አሁንም ችግር ያለበት ሀይል የራሱን ችግር በራሱ ይፍታ እንጂ ከውጭ ሀይል ጋር የሚሞዳሞድ እና ለግጭት የሚጋብዝ ከሆነ ትችት ብቻ ሳይሆን ማጋለጥ እና ድርጊቱን ለህዝብ የማሳወቅ ስራ መስራት አለብን።
የሚያሳዝነው መንግስት በየክፍለ ከተማው እና ቀበሌው ያደራጃቸው 30 ሺህ 'የሚድያ ሰራዊት' የሚላቸው አብዛኛው ስራቸው ገፆች ላይ እየገቡ የተሰጣቸውን ኮመንት ከመለጠፍ የዘለለ እውቀትም፣ ትምህርትም፣ ልምድም የሌላቸው ናቸው፣ እንዲህ አይነት የኤርትራን hostile ፕሮፖጋንዳን ለመመከት ብቁ አይደለም።
ሁላችንም ግን ባለስልጣንን ወይም ፓርቲን ሳይሆን ሀገርን ከእንዲህ አይነት ጥቃት መከላከል አለብን።
@EliasMeseret
👍 990😁 110❤ 108😢 20🙏 15🤔 13🕊 9😱 7
#Update ውጤት... 4,244 ሰው ወይም 67 ፐርሰንቱ "ኧረ ምኑ ጉደኛ ዜና አንባቢ ነው" ብሏል።
@EliasMeseret
😁 1 447👍 164❤ 58🤔 20😱 3😢 3🕊 3
Photo unavailableShow in Telegram
ከሁለት ደርዘን በላይ የውጭ ሀገራት በትግራይ ያለው ሁኔታ 'አሳስቧቸው' መግለጫ ሲያወጡ የፌደራል መንግስት ቢያንስ እንኳን እንደነሱ መግለጫ ማውጣት ለምን አልቻለም ወይም አልፈለገም... ያውም ራሱ የሾመው አስተዳደር 'ተገለበጥኩ' እያለ?
ለማንኛውም ጦርነት አሟሟቂዎች በየሶሻል ሚድያው የሚሉትን ሳይሰማ ህዝብ "ጦርነት በቃን" ሊል ይገባል።
#NoToWar
@EliasMeseret
👍 901🕊 155😁 64❤ 46🤔 27🙏 25😢 24
ከዚህ ቪድዮ ምን እንማራለን?Anonymous voting
- ሀ: የመድረክ አጋፋሪነት እና ጋዜጠኝነት እንደተምታታበት
- ለ: መድረክ መምራት የጋዜጠኝነት መስዋዕትነት መክፈል እንዳልሆነ
- ሐ: ዜና አንባቢው ከዚህ ቀደም 'ጋዜጠኝነት እውነት መናገር አይደለም' ማለቱን መርሳቱ
- መ: ኧረ ምኑ ጉደኛ ዜና አንባቢ ነው
😁 1 515👍 147😢 49🤔 47❤ 32😱 22🙏 5🕊 3
00:42
Video unavailableShow in Telegram
ከዚህ ቪድዮ ምን እንማራለን?
1.24 MB
😁 877👍 65😢 48🤔 35❤ 22😱 10🕊 1
ሊንኩ አልከፍት ላላችሁ በ PDF ለማንበብ ⬇️
https://acrobat.adobe.com/id/urn:aaid:sc:EU:bc814da0-6b8c-44b2-ae7c-b023525823ef
👍 52😁 13❤ 7
Photo unavailableShow in Telegram
ዋሽንግተን ፖስት በትናንትናው እለት በዲሲ እና አካባቢው ያሉ ስምንት የኢትዮጵያን ምግብ የሚያቀርቡ ሬስቶራንቶች ላይ ዳሰሳ ሰርቶ ነበር
ከነዚህ መሀልም የወዳጄ ዲጄ ፋትሱ (ሱራፌል ሽፈራው) አዲስ ሬስቶራንት የሆነው Eatopia ተካቷል። የሀገር ልጅ በሰው ሀገር ለፍቶ ሰርቶ እንዲህ ሲከብር እና የሀገሩን ባህል ሲያስተዋውቅ ደስ ይላል። በርቱ!
ዳሰሳውን ለማንበብ: https://www.washingtonpost.com/food/2025/03/11/best-ethiopian-restaurants-dc/
@EliasMeseret
👍 663❤ 127🙏 25😁 15
Photo unavailableShow in Telegram
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የጠ/ሚር ፅ/ቤት ገፅ ላይ ያለውን ፖስት አላየውም መሰል የአፕሉ ጉዳይ በ VAR ይታይልኝ እያለ ነው።
መረጃውን በማስረጃ የሞገቱትን ለማሸማቀቅ?
@EliasMeseret
😁 942👍 86❤ 27😢 6🙏 4
Photo unavailableShow in Telegram
ከስህተቱ በኋላ እርምት ማድረግ እንዲሁም ወደፊት ተመሳሳይ ሁኔታ እንዳይከሰት ትምህርት ሆኖ ማለፉ መልካም ነው
ይሁንና አሁንም በበርካታ የመንግስት ተቋማት፣ ባለስልጣናት እና ኤጀንሲዎች በኩል የሚለቀቁ መረጃዎች ሀሰተኛ መረጃዎች አንዳንዴ ይቀርቡባቸዋል፣ አብዛኞቹም ስህተታቸውን ሳያርሙ ህዝብን እንዳሳሳቱ በዛው ይቀራሉ።
ኢትዮጵያ ቼክ ከዚህ በፊት እንዲህ አይነት ችግሮችን ለመቅረፍ ለመንግስት ቢሮዎች በሶሻል ሚድያ አጠቃቀም ዙርያ በነፃ ስልጠና ለመስጠት ጥሪ አርጎ ነበር።
ግብዣው አሁንም ክፍት ነው።
@EliasMeseret
👍 470😁 150❤ 37🙏 5🤔 4😱 2
Photo unavailableShow in Telegram
በማህበራዊ ሚድያ ጩኸት እና በመጨረሻም ቢሆን በመንግስት አካላት ጥረት 32 ወገኖቻችን ከሚያንማር ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል
እዛ ሀገር ሄደው መውጫ ያጡ ዜጎቻችን ቁጥር 1,320 አካባቢ እንደሆነ ራሳቸው ወጣቶቹ ነግረውኛል፣ አሁንም ከፍተኛ ጥረት ካልተደረገ ያሉበትን ችግር በቃላት ለመግለፅ ይከብዳል። በተስፋ መቁረጥ ራሳቸውን ለማጥፋት እየሞከሩ ያሉ ብዙዎች ናቸው።
እስከመጨረሻው ድምፅ እንሁናቸው።
@EliasMeseret
👍 654❤ 70😢 59🙏 51😱 8🕊 7😁 2
ተተኳሽ እና ድሮን...!
እስቲ ለትውልዱ የሚጠቅሙ አዳዲስ ዩኒቨርስቲዎች፣ የኢንደስትሪ ፓርኮች፣ የመንገድ ግንባታዎች፣ የማዳበርያ ፋብሪካዎች፣ የሀይል ማመንጫ ግድቦች ወዘተ ይጀመሩ እና እኛም በስፋት እናመስግን።
መቼ ነበር ግን እንዲህ አይነት ግንባታዎች ተጀመሩ የሚል ዜና ለመጨረሻ ግዜ የሰማነው?
@EliasMeseret
👍 1 717😢 209❤ 129😁 93🙏 65🤔 41🕊 21😱 14
Photo unavailableShow in Telegram
አሸዋውን 'ሳታቆሽሽ መልስ' ተብሎ ከኮሪደር ልማት ለዛሬ ምሽት ተውሶት ነው አሉ፣ ያስደፋው ራሱ ሸራ ላይ ነው 🤔
በሉ ልተኛበት!
Sura D Qayel
@EliasMeseret
😁 1 707👍 168❤ 45🤔 25😱 17🙏 8🕊 5
Photo unavailableShow in Telegram
እድሜ ለመሠረት ሚድያ ዜና የአፍሪካ ግዙፉ ሚድያ ዋና መስሪያ ቤት ግንባታ ዛሬ ምሽት በመዲናችን ተጀምሯል 🤣
የዜናው ሊንክ: https://www.facebook.com/share/p/1ALnzEu5R2/
@EliasMeseret
😁 1 017👍 101❤ 34🤔 21🕊 7🙏 5😱 1
መንግስት በቅርቡ ካሳካቸው አበይት ጉዳዮች አንዱ የባህር በር ጥያቄን የማይታሰብ ተደርጎ ይቆጠር የነበረውን ማስቀረቱ ነው
እርግጥ ነው የሶማሊላንዱ አካሄድ ዲፕሎማሲያዊ ብስለት የጎደለው ነበር፣ በዛ ላይ አንዳንድ ጦርነት የናፈቃቸው አክቲቪስቶች የወደብን ጉዳይ በቀጥታ ከደም መፋሰስ ጋር ሲያያይዙት እያየን ነው።
አሁንም ጉዳዩ በብስለት ከተያዘ፣ ለሀገር ውስጥ ችግሮች አስፈላጊው መፍትሄ በፍጥነት ከተሰጠ እና ጉዳዩን የሁሉም ኢትዮጵያዊ አጀንዳ ማድረግ ከተቻለ የወደብ ጉዳይ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ጉዳይ ነው።
@EliasMeseret
👍 1 257❤ 179😁 154🤔 34🙏 22🕊 21😱 5
