Fana Media Corporation S.C (FMC)
الذهاب إلى القناة على Telegram
This is FMC's official Telegram channel. For more updates please visit https://fanamc.com
إظهار المزيد2025 عام في الأرقام

207 919
المشتركون
-6324 ساعات
-2697 أيام
-86930 أيام
أرشيف المشاركات
Photo unavailableShow in Telegram
በደብረብርሃን ከተማ 14 አዳዲስ ፋብሪካዎች ወደ ስራ ገብተዋል
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደብረብርሃን ከተማ በ2018 በጀት ዓመት ብቻ 14 አዳዲስ ፋብሪካዎች ወደ ስራ ገብተዋል። በአምራች ኢንዱስትሪ ብሔራዊ ካውንስል ሰብሳቢ አምባሳደር ግርማ ብሩ የተመራ ቡድን በከተማዋ የአምራች ኢንዱስትሪዎችን የስራ እንቅስቃሴ እየጎበኘ ነው። በጉብኝቱ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል፣ የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ፣ የገቢዎች ሚኒስትር…
https://www.fanamc.com/archives/306583
❤ 15👍 3
Photo unavailableShow in Telegram
የአምራች ኢዱስትሪዎችን ተግዳሮቶች ለመፍታት …
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአምራች ኢንዱስትሪ ብሔራዊ ካውንስል በደብረሃን ከተማ አምራች ኢዱስትሪዎች የሚገጥሟቸውን ተግዳሮቶችን ለመፍታት ያለመ ጉብኝት እያካሄደ ነው። ጉብኝቱ በአምራች ኢንዱስትሪ ብሔራዊ ካውንስል ሰብሳቢ አምባሳደር ግርማ ብሩ የተመራ ሲሆን፤ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል፣ የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ እና የገቢዎች ሚኒስትር አይናለም ንጉሴ ተሳትፈዋል። እንዲሁም የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ…
https://www.fanamc.com/archives/306580
❤ 17👍 4👏 3
Photo unavailableShow in Telegram
የአስቶን ቪላ እና ማንቼስተር ዩናይትድ ጨዋታ ይጠበቃል
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 17ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ጨዋታ ዛሬ ቀጥሎ ሲካሄድ በአሰልጣኝ ኡናይ ኤምሬ የሚመራው አስቶን ቪላ ማንቼስተር ዩናይትድን ያስተናግዳል። አስቶን ቪላ በውድድር ዓመቱ ድንቅ ብቃት በማስመልከት በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ በ33 ነጥብ ሶስተኛ ላይ ሲሆን ወጥ ብቃት ማሳየት የቸገረው ማንቼስተር ዩናይትድ በ26 ነጥብ ሰባተኛ ደረጃ…
https://www.fanamc.com/archives/306577
👍 11❤ 9😁 2
04:27
Video unavailableShow in Telegram
በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 የተቀመጡ ግቦች እንዲሳኩ ሁለት መሠረታዊ አስቻይ ጉዳዮች አሉ - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
አንደኛው የኤሌክትሪክ ተደራሽነት ነው። የኤሌክትሪክ ተደራሽነት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ምግብ ነው ብሎ መውሰድ ይቻላል።
የምንጠቀምባቸው የቴክኖሎጂ ጋጄቶች ኤሌክትሪክ ይፈልጋሉ።
በመሆኑም በሁሉም አማራጮች የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን ማስፋት አለብን። ሁለተኛው የኢንተርኔት ትስስር ነው።
በርካታ ከተሞች የኢንተርኔት ትስስር ተጠቃሚ ሆነዋል። ነገር ግን በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ይህን ትስስር በሁሉም አካባቢዎች ሙሉ ለሙሉ ተደራሽ ማድረግ ይገባል።
ይህ እንደሚቻል አምነን በመስራት ለዜጎቻችን እኩል እድል መፍጠር አለብን።
AQMTfKe_uIc61UJyoVaPNpWfGz8N4sQ0_OCX7IEQiozHJOFAr59_SslX5lvxlFy.mp412.28 MB
❤ 34😱 2👍 1🤔 1
Photo unavailableShow in Telegram
ሊቨርፑል ቶተንሃምን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ17ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ሊቨርፑል ቶተንሃም ሆትስፐርን 2 ለ 1አሸንፏል፡፡
የሊቨርፑልን ግቦች ኢሳክ እና ኤኪቲኬ ሲያስቆጥሩ፥ ሪቻርልሰን ቶተንሃምን ከሽንፈት ያልታደገችውን ብቸኛ ግብ ከመረብ አሳርፏል፡፡
በቶተንሃም በኩል ዣቪ ሲሞንስ በመጀመሪያው አጋማሽ እንዲሁም ክሪስታን ሮሜሮ በጨዋታው መገባደጃ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብተዋል፡፡
❤ 31👍 19😁 5
Photo unavailableShow in Telegram
“ስታርት አፕና የዲጂታል ክህሎት ልማት ለዲጂታል 2030 ስትራቴጂ መሳካት ትልቅ ሚና ከሚጫወቱ ጉዳዮች መካከል ተጠቃሾች ናቸው። በተለይ የዲጂታል ክህሎትን ለማሳደግ ወሳኝ አቀጣጫዎች ተቀምጠዋል። በዚህም በ2030 ከሀገሪቷ አጠቃላይ ህዝብ 70 በመቶ የሚሆነው የዲጂታል እውቀት እንዲኖረው፣ 80 በመቶ የሚሆነው የመንግስት ሰራተኛ የዲጂታል ክህሎት የተላበሰ እንዲሆን፣ 10 ሚሊዮን ዜጎች የዲጂታል ስልጠና እንዲወስዱ በልዩ ትኩረት የሚሰራ ይሆናል። ከዚህ በተጨማሪ 5 ሺህ ስታርት አፖች ወደ ስራ እንዲገቡና በዲጂታል ዘርፍ ለ1 ሚሊዮን ዜጎች የስራ እድል እንዲፈጠርም የሚሰራ ይሆናል። በሌላ በኩል በ2030 ከሀገር ወስጥ አጠቃላይ ምርት ዲጂታል ዘርፍ ገቢ 12 በመቶ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል።”
ሙሉቀን ቀሬ
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ደኤታ
❤ 18👍 4
Photo unavailableShow in Telegram
“ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ታክስ የመሰብሰብ አቅም ላይ ትርጉም ያለው ለውጥ አምጥቷል። አሁን ላይ 58 ሺህ የሚሆኑ ግብር ከፋዮች ግብራቸውን በዲጂታል ስርዓት አማካኝነት እያሳወቁ ይገኛሉ። በቀጣይም በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 አማከኝነት ከተቋማት ጋር ተናባቢና ተመጋጋቢ የዲጂታል ስርዓትን በማጠናከር ታክስ የመሰብሰብ አቅምን ይበልጥ እንዲጠናከር ይሰራል።”
ዳዊት ውብሸት
የገቢዎች ሚኒስትር ዴኤታ
❤ 9👍 4
Photo unavailableShow in Telegram
ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 በሲቪል ምዝገባና የዜግነት አገልግሎት ተደራሽነት ላይ ትልቅ ለውጥ አምጥቷል። አግልግሎቱን ከተለያዩ ተቋማት ጋር በማስተሳሰር ረገድም ትልቅ ተሞክሮ የሚሆን ስራ ተከናወኗል።ለአብነትም በአዲስ አበባ ከማዕከል እስከ ወረዳ ትስስር መፍጠር የተቻለ ሲሆን፣ ለስራው የሚያገለግሉ መተግበሪያዎችም በሀገር ውስጥ አቅም የለሙ ናቸው። በዚህም የቤተሰብ ምዝገባ፣ ወሳኝ ኩነት፣የነዋሪዎች አገልግሎትና የማረጋገጥ ስራዎች በዲጂታል ስርዓት ተግባራዊ እየተደረጉ ነው። ይህም በ2030 ተቋማት በዲጂታል አሰራርና በመረጃ የተሳሰሩ እንዲሆኑ ለሚከናወነው ስራ ተሞክሮ መሆን የሚችል ነው።
ታዬ ግርማ
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር
❤ 9👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ የንግድ ስርዓቱን ማዘመን የሚያስችሉ ስራዎች የሚከናወኑ ሲሆን ፣ በተለይ የሀገር ውስጥ የኢ-ኮሜርስ ስርዓትንና የንግድ ስራ የሚውሉ ሎጂስቲክስን በማሟላት የንግድ ሰርዓቱ ይበልጥ እንዲሳለጥ ይሰራል። የወጪና ገቢ ንግድ ላይ ያሉ አሰራሮችንም ዲጂታል እንዲሆኑ በማድረግ ዘርፉ ለኢኮኖሚ ያለውን ፋይዳ ይበልጥ እንዲጎለብት ይደረጋል።
ይድነቃቸው ወርቁ
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ድኤታ
❤ 14👏 3👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ በዲጂታል 2025 ስትራቴጂ ላይ ቁልፍ ጉዳይ ሆኖ ተተግብሯል። አሁን ላይ 30 ሚሊዮን ዜጎች ፋይዳ መታወቂያ ተመዝግበዋል። በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ላይም ፋይዳ ስትራቴጂካዊ ትኩረት የተሰጠው ሲሆን ሙሉ ለሙሉ ተደራሽ የማድረግ ስራም ይሰራል። በተለይ እስከታችኛው መዋቅር ድረስ ያሉ አገልግሎቶችን ከፋይዳ ጋር በማስተሳሰር በስትራቴጂው የተቀመጡ ግቦችን ለማሳካት በትኩረት ይሰራል። ለዚህ ደግሞ ሁሉም በትብብር ሊሰራ ይገባል።
ዮዳሄ አርአያስለሴ
የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ዋና አስተባባሪ
❤ 21👍 7😁 2😱 2
Photo unavailableShow in Telegram
በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ስነ ምህዳር ማስፋት የሚያስችሉ በርካታ ስራዎች ይከናወናሉ።የራሳችንን ክላውድ ከመጠቀም ባሻገር ውጤታማ የመረጃ አስተዳደር ስርዓት እንዲኖር ይደረጋል። በዚህም በተደራጀ አግባብ መረጃዎች ለወሳኔ አሰጣጥ እንዲውሉ የሚሰራ ሲሆን፣ ከዚህ ጋር በተያያዘ ገለልተኛ ብሔራዊ የመረጃ ባለስልጣን ወደ ስራ እንዲገባ ይደረጋል። ዲጂታል አገልግሎቶት አሰጣጦችን የማናበብንና ወጥ የማድረግ ስራ ላይም ትኩረት ተሰጥቷል።
ወርቁ ጋቸና
የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር
❤ 11👍 8👏 2
Photo unavailableShow in Telegram
በዲጂታል 2025 ስትራቴጂ በሳይበር ደህንነት ላይ በርካታ አስቻይ መሰረቶች ተጥለዋል። በዚህም የራሳችንን ክላውድ መሰረተ ልማት በመገንባት በኢትዮጵያ የዲጂታል አገልግሎት መተማመን መፍጠር ተችሏል። ለጸጥታ ተቋማትም የዲጂታል ፎረንሲክ ላብ በመገንባት ወደ ስራ እንዲገባ ተደርጓል።
በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 የሳይበር ደህንነት ስትራቴጂካዊ ትኩረት ተሰጥቶታል። በዚህም የማይበገር ቁልፍ የዲጂታል መሰረተ ልማት መገንባት፣ የህዝብ መሰረተ ልማትን ማዘመን፣ የአደጋ ምላሽ መስጫ ማዕከል የማቋቋምና የግል ተቋማትን ያካተተ የሳይበር ደህንነት ስራ እንዲጎለብት ይሰራል።
ትዕግስት ሀሚድ
የኢንፎርሜሽንና መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር
👍 10❤ 3👏 2
Photo unavailableShow in Telegram
ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 በቴሌኮም ዘርፍ በርካታ ውጤቶች የተመዘገቡበት ነው። ለአብነትም የሞባይል ደንበኞች ቁጥርን 97 ሚሊዮን ማድረስ የተቻለ ሲሆን፣ ከዚህም ውስጥ 57 ሚሊዮኑ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ሆነዋል። አንድ ሺህ ሰለሳ ከተሞችም የ4ጂ ኔትወርክ ተደራሽ ሆኗል። በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ የሞባይል ተጠቃሚ ደንበኞች ቁጥር 128 ሚሊዮን የሚደርስ ሲሆን፣ የ5ጂ ኔትወርክ ሽፋንን 100 ፐርስንት ይሆናል። በ2030 የዲጂታል ክፍያን ከአጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት አንጻር አሁን ካለበት ከሰባት እጥፍ በላይ እንዲያድግም በልዩ ትኩረት ይሰራል።
ፍሬሕይወት ታምሩ
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ
❤ 21👍 6😁 4👏 3🤔 1
Photo unavailableShow in Telegram
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ወጣቶች ኦሊምፒክ 33 ሜዳሊያ በማግኘት አጠናቀቀች
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በአንጎላ ሉዋንዳ ሲካሄድ በቆየው 4ኛው የአፍሪካ ወጣቶች ኦሊምፒክ 33 ሜዳሊያዎችን በማግኘት አጠናቀቀች፡፡ የውድድሩ የማጠቃለያ መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት የተካሄደ ሲሆን፥ ኢትዮጵያ በውድድሩ 8 ወርቅ፣ 9 የብር እና 16 የነሃስ በጥቅሉ 33 ሜዳልያዎችን አግኝታለች፡፡ ኢትዮጵያ ቀደም ሲል የ2027ቱን የወጣቶች ኦሊምፒክ እንድታዘጋጅ መመረጧ የሚታወስ ሲሆን፥…
https://www.fanamc.com/archives/306570
❤ 29👍 7
Photo unavailableShow in Telegram
ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ሰው ተኮርና ለሁሉም ሴክተሮች ትኩረት ተሰጥቶ የሚሰራበት ሲሆን በዲጂታል 2025 የተመዘገቡ የዲጂታል መሰረተ ልማቶችን የማስፋፋት ስራውን በተጨባጭ ውጤት የምናሳይበት ጭምር ነው።
ስትራቴጂው በግልጽ የአስተዳደር ስርዓት፣ በሚለካ ውጤት እና በተጠያቂነት ላይ ተመስርቶ በቀጣይ አምስት ዓመታት ተግባራዊ ይሆናሉ።
ለዚህ ደግሞ ሁሉም የሚመለከተው አካል የጋራ ርብርብ ማድረግ ይጠበቅበታል።
ሚሪያም አሊ
በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የዲጂታል አማካሪ
❤ 13👍 7🤔 3
ማንቼስተር ሲቲ ዌስትሃምን በማሸነፍ ሊጉን መምራት ጀመረ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ17ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ማንቼስተር ሲቲ ዌስትሃም ዩናይትድን 3 ለ 0 አሸንፏል፡፡
የማንቼስተር ሲቲን ግቦች ሀላንድ (2) እና ሬይንደርስ ያስቆጠሩ ሲሆን፥ አርሰናል ዛሬ ምሽት ጨዋታውን እስከሚያደርግ ድረስ ሲቲ በ37 ነጥብ ሊጉን መምራት ጀምሯል፡፡
ምሽት 12 ሰዓት በተደረጉ ሌሎች ጨዋታዎች ብሬንትፎርድ ወልቭስን 2 ለ 0 ሲያሸንፍ፥ ቦርንማውዝ ከበርንሌይ 1 ለ 1 እንዲሁም ብራይተን ከሰንደርላንድ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል፡፡
ቶተንሃም ሆትስፐር ከሊቨርፑል ምሽት 2 ሰዓት ከ30 የሚገናኙ ሲሆን፥ የሊጉ መሪ አርሰናል ከኤቨርተን እንዲሁም ሊድስ ዩናይትድ ከክሪስታል ፓላስ በተመሳሳይ ምሽት 5 ሰዓት የሚደረጉ የዛሬ ጨዋታዎች ናቸው፡፡
❤ 16👍 9🤬 4👏 2
Photo unavailableShow in Telegram
ኢትዮጵያ በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ወደ ታሪካዊ ከፍታ ትሸጋገራለች – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ታሪካዊና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ወደሆነ ከፍታ ትሸጋገራለች አሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 የትግበራ ምዕራፍ ይፋዊ የማጠናቀቂያና የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ትግበራ ይፋዊ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው፡፡ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ…
https://www.fanamc.com/archives/306566
❤ 12👍 1👏 1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የተካሄደው የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ይፋዊ የማስጀመሪያ መርሐ ግብር በምስል፡-
👍 23❤ 10😁 4👏 2
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት፡-
ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ የታለመለትን ግብ አሳክቶ ተጠናቋል። በዛሬው እለትም ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 በይፋ አስጀምረናል። ተደራሽነትን ማስፋት፣ ለዜጎች እኩል እድል መፍጠር እንዲሁም በዜጎችና ተቋማት መካከል መተማመንን ማጎልበት ደግሞ የስትራቴጂው ቁልፍ መሰረታዊ ትልሞች ናቸው። እነዚህ ትልሞች እንዲሳኩም በተለይ የህዝብ ዲጂታል መሠረተ ልማት ማስፋት ላይ ትልቅ ስራ የሚከናወን ሲሆን፣ ይህም ዲጂታል ቴክኖሎጂ ሰው ተኮር ሆኖ የዜጎችን ኑሮ እንዲያሻሽል ትልቅ አቅም ይፈጥራል። በአጠቃላይ በዲጂታል ኢትዮጵያ የሚከናወኑ ስራዎች የመደመር መንግስት በቀለለ ቢሮክራሲ ታላላቅ ስትራቴጂዎችን እውን ለማድረግ ከያዘው ግብ ጋር የተሳሰሩ ናቸው።
❤ 15👏 9🥰 2👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
በአየር ፀባይ ምክንያት የተወሰኑ የሀገር ውስጥ በረራዎች ይቋረጣሉ – የኢትዮጵያ አየር መንገድ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች በተከሰተው ጭጋጋማና ለበረራ አመቺ ያልሆነ የአየር ፀባይ ምክንያት የተወሰኑ የሀገር ውስጥ በረራዎች ይቋረጣሉ አለ፡፡ አየር መንገዱ ባወጣው መግለጫ በአሁኑ ወቅት ያጋጠመው የአየር ፀባይ ለተወሰኑ ቀናት የሚቀጥል መሆኑን ከሚቲዎሮሎጂ መረጃ መሰረት ለማወቅ ተችሏል ብሏል፡፡ በዚህ ምክንያት ወደተወሰኑ የሀገራችን ክፍሎች የሚያደርጋቸውን…
https://www.fanamc.com/archives/306559
❤ 10👍 6
