uz
Feedback
Fana Media Corporation S.C (FMC)

Fana Media Corporation S.C (FMC)

Kanalga Telegram’da o‘tish

This is FMC's official Telegram channel. For more updates please visit https://fanamc.com

Ko'proq ko'rsatish
2025 yil raqamlardasnowflakes fon
card fon
207 930
Obunachilar
-6324 soatlar
-2697 kunlar
-86930 kunlar
Postlar arxiv
Photo unavailableShow in Telegram
“ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ታክስ የመሰብሰብ አቅም ላይ ትርጉም ያለው ለውጥ አምጥቷል። አሁን ላይ 58 ሺህ የሚሆኑ ግብር ከፋዮች ግብራቸውን በዲጂታል ስርዓት አማካኝነት እያሳወቁ ይገኛሉ። በቀጣይም በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 አማከኝነት ከተቋማት ጋር ተናባቢና ተመጋጋቢ የዲጂታል ስርዓትን በማጠናከር ታክስ የመሰብሰብ አቅምን ይበልጥ እንዲጠናከር ይሰራል።” ዳዊት ውብሸት የገቢዎች ሚኒስትር ዴኤታ
Hammasini ko'rsatish...
9👍 4
Photo unavailableShow in Telegram
ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 በሲቪል ምዝገባና የዜግነት አገልግሎት ተደራሽነት ላይ ትልቅ ለውጥ አምጥቷል። አግልግሎቱን ከተለያዩ ተቋማት ጋር በማስተሳሰር ረገድም ትልቅ ተሞክሮ የሚሆን ስራ ተከናወኗል።ለአብነትም በአዲስ አበባ ከማዕከል እስከ ወረዳ ትስስር መፍጠር የተቻለ ሲሆን፣ ለስራው የሚያገለግሉ መተግበሪያዎችም በሀገር ውስጥ አቅም የለሙ ናቸው። በዚህም የቤተሰብ ምዝገባ፣ ወሳኝ ኩነት፣የነዋሪዎች አገልግሎትና የማረጋገጥ ስራዎች በዲጂታል ስርዓት ተግባራዊ እየተደረጉ ነው። ይህም በ2030 ተቋማት በዲጂታል አሰራርና በመረጃ የተሳሰሩ እንዲሆኑ ለሚከናወነው ስራ ተሞክሮ መሆን የሚችል ነው። ታዬ ግርማ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር
Hammasini ko'rsatish...
9👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ የንግድ ስርዓቱን ማዘመን የሚያስችሉ ስራዎች የሚከናወኑ ሲሆን ፣ በተለይ የሀገር ውስጥ የኢ-ኮሜርስ ስርዓትንና የንግድ ስራ የሚውሉ ሎጂስቲክስን በማሟላት የንግድ ሰርዓቱ ይበልጥ እንዲሳለጥ ይሰራል። የወጪና ገቢ ንግድ ላይ ያሉ አሰራሮችንም ዲጂታል እንዲሆኑ በማድረግ ዘርፉ ለኢኮኖሚ ያለውን ፋይዳ ይበልጥ እንዲጎለብት ይደረጋል። ይድነቃቸው ወርቁ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ድኤታ
Hammasini ko'rsatish...
14👏 3👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ በዲጂታል 2025 ስትራቴጂ ላይ ቁልፍ ጉዳይ ሆኖ ተተግብሯል። አሁን ላይ 30 ሚሊዮን ዜጎች ፋይዳ መታወቂያ ተመዝግበዋል። በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ላይም ፋይዳ ስትራቴጂካዊ ትኩረት የተሰጠው ሲሆን ሙሉ ለሙሉ ተደራሽ የማድረግ ስራም ይሰራል። በተለይ እስከታችኛው መዋቅር ድረስ ያሉ አገልግሎቶችን ከፋይዳ ጋር በማስተሳሰር በስትራቴጂው የተቀመጡ ግቦችን ለማሳካት በትኩረት ይሰራል። ለዚህ ደግሞ ሁሉም በትብብር ሊሰራ ይገባል። ዮዳሄ አርአያስለሴ የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ዋና አስተባባሪ
Hammasini ko'rsatish...
21👍 7😁 2😱 2
Photo unavailableShow in Telegram
በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ስነ ምህዳር ማስፋት የሚያስችሉ በርካታ ስራዎች ይከናወናሉ።የራሳችንን ክላውድ ከመጠቀም ባሻገር ውጤታማ የመረጃ አስተዳደር ስርዓት እንዲኖር ይደረጋል። በዚህም በተደራጀ አግባብ መረጃዎች ለወሳኔ አሰጣጥ እንዲውሉ የሚሰራ ሲሆን፣ ከዚህ ጋር በተያያዘ ገለልተኛ ብሔራዊ የመረጃ ባለስልጣን ወደ ስራ እንዲገባ ይደረጋል። ዲጂታል አገልግሎቶት አሰጣጦችን የማናበብንና ወጥ የማድረግ ስራ ላይም ትኩረት ተሰጥቷል። ወርቁ ጋቸና የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር
Hammasini ko'rsatish...
11👍 8👏 2
Photo unavailableShow in Telegram
በዲጂታል 2025 ስትራቴጂ በሳይበር ደህንነት ላይ በርካታ አስቻይ መሰረቶች ተጥለዋል። በዚህም የራሳችንን ክላውድ መሰረተ ልማት በመገንባት በኢትዮጵያ የዲጂታል አገልግሎት መተማመን መፍጠር ተችሏል። ለጸጥታ ተቋማትም የዲጂታል ፎረንሲክ ላብ በመገንባት ወደ ስራ እንዲገባ ተደርጓል። በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 የሳይበር ደህንነት ስትራቴጂካዊ ትኩረት ተሰጥቶታል። በዚህም የማይበገር ቁልፍ የዲጂታል መሰረተ ልማት መገንባት፣ የህዝብ መሰረተ ልማትን ማዘመን፣ የአደጋ ምላሽ መስጫ ማዕከል የማቋቋምና የግል ተቋማትን ያካተተ የሳይበር ደህንነት ስራ እንዲጎለብት ይሰራል። ትዕግስት ሀሚድ የኢንፎርሜሽንና መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር
Hammasini ko'rsatish...
👍 10 3👏 2
Photo unavailableShow in Telegram
ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 በቴሌኮም ዘርፍ በርካታ ውጤቶች የተመዘገቡበት ነው። ለአብነትም የሞባይል ደንበኞች ቁጥርን 97 ሚሊዮን ማድረስ የተቻለ ሲሆን፣ ከዚህም ውስጥ 57 ሚሊዮኑ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ሆነዋል። አንድ ሺህ ሰለሳ ከተሞችም የ4ጂ ኔትወርክ ተደራሽ ሆኗል። በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ የሞባይል ተጠቃሚ ደንበኞች ቁጥር 128 ሚሊዮን የሚደርስ ሲሆን፣ የ5ጂ ኔትወርክ ሽፋንን 100 ፐርስንት ይሆናል። በ2030 የዲጂታል ክፍያን ከአጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት አንጻር አሁን ካለበት ከሰባት እጥፍ በላይ እንዲያድግም በልዩ ትኩረት ይሰራል። ፍሬሕይወት ታምሩ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ
Hammasini ko'rsatish...
21👍 6😁 4👏 3🤔 1
Photo unavailableShow in Telegram
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ወጣቶች ኦሊምፒክ 33 ሜዳሊያ በማግኘት አጠናቀቀች አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በአንጎላ ሉዋንዳ ሲካሄድ በቆየው 4ኛው የአፍሪካ ወጣቶች ኦሊምፒክ 33 ሜዳሊያዎችን በማግኘት አጠናቀቀች፡፡ የውድድሩ የማጠቃለያ መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት የተካሄደ ሲሆን፥ ‎ኢትዮጵያ በውድድሩ 8 ወርቅ፣ 9 የብር እና 16 የነሃስ በጥቅሉ 33 ሜዳልያዎችን አግኝታለች፡፡ ‎ ኢትዮጵያ ቀደም ሲል የ2027ቱን የወጣቶች ኦሊምፒክ እንድታዘጋጅ መመረጧ የሚታወስ ሲሆን፥… https://www.fanamc.com/archives/306570
Hammasini ko'rsatish...
29👍 7
Photo unavailableShow in Telegram
ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ሰው ተኮርና ለሁሉም ሴክተሮች ትኩረት ተሰጥቶ የሚሰራበት ሲሆን በዲጂታል 2025 የተመዘገቡ የዲጂታል መሰረተ ልማቶችን የማስፋፋት ስራውን በተጨባጭ ውጤት የምናሳይበት ጭምር ነው። ስትራቴጂው በግልጽ የአስተዳደር ስርዓት፣ በሚለካ ውጤት እና በተጠያቂነት ላይ ተመስርቶ በቀጣይ አምስት ዓመታት ተግባራዊ ይሆናሉ። ለዚህ ደግሞ ሁሉም የሚመለከተው አካል የጋራ ርብርብ ማድረግ ይጠበቅበታል። ሚሪያም አሊ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የዲጂታል አማካሪ
Hammasini ko'rsatish...
13👍 7🤔 3
ማንቼስተር ሲቲ ዌስትሃምን በማሸነፍ ሊጉን መምራት ጀመረ አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ17ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ማንቼስተር ሲቲ ዌስትሃም ዩናይትድን 3 ለ 0 አሸንፏል፡፡ የማንቼስተር ሲቲን ግቦች ሀላንድ (2) እና ሬይንደርስ ያስቆጠሩ ሲሆን፥ አርሰናል ዛሬ ምሽት ጨዋታውን እስከሚያደርግ ድረስ ሲቲ በ37 ነጥብ ሊጉን መምራት ጀምሯል፡፡ ምሽት 12 ሰዓት በተደረጉ ሌሎች ጨዋታዎች ብሬንትፎርድ ወልቭስን 2 ለ 0 ሲያሸንፍ፥ ቦርንማውዝ ከበርንሌይ 1 ለ 1 እንዲሁም ብራይተን ከሰንደርላንድ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል፡፡ ቶተንሃም ሆትስፐር ከሊቨርፑል ምሽት 2 ሰዓት ከ30 የሚገናኙ ሲሆን፥ የሊጉ መሪ አርሰናል ከኤቨርተን እንዲሁም ሊድስ ዩናይትድ ከክሪስታል ፓላስ በተመሳሳይ ምሽት 5 ሰዓት የሚደረጉ የዛሬ ጨዋታዎች ናቸው፡፡
Hammasini ko'rsatish...
16👍 9🤬 4👏 2
Photo unavailableShow in Telegram
ኢትዮጵያ በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ወደ ታሪካዊ ከፍታ ትሸጋገራለች – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ታሪካዊና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ወደሆነ ከፍታ ትሸጋገራለች አሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 የትግበራ ምዕራፍ ይፋዊ የማጠናቀቂያና የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ትግበራ ይፋዊ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው፡፡ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ… https://www.fanamc.com/archives/306566
Hammasini ko'rsatish...
12👍 1👏 1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የተካሄደው የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ይፋዊ የማስጀመሪያ መርሐ ግብር በምስል፡-
Hammasini ko'rsatish...
👍 23 10😁 4👏 2
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት፡- ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ የታለመለትን ግብ አሳክቶ ተጠናቋል። በዛሬው እለትም ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 በይፋ አስጀምረናል። ተደራሽነትን ማስፋት፣ ለዜጎች እኩል እድል መፍጠር እንዲሁም በዜጎችና ተቋማት መካከል መተማመንን ማጎልበት ደግሞ የስትራቴጂው ቁልፍ መሰረታዊ ትልሞች ናቸው። እነዚህ ትልሞች እንዲሳኩም በተለይ የህዝብ ዲጂታል መሠረተ ልማት ማስፋት ላይ ትልቅ ስራ የሚከናወን ሲሆን፣ ይህም ዲጂታል ቴክኖሎጂ ሰው ተኮር ሆኖ የዜጎችን ኑሮ እንዲያሻሽል ትልቅ አቅም ይፈጥራል። በአጠቃላይ በዲጂታል ኢትዮጵያ የሚከናወኑ ስራዎች የመደመር መንግስት በቀለለ ቢሮክራሲ ታላላቅ ስትራቴጂዎችን እውን ለማድረግ ከያዘው ግብ ጋር የተሳሰሩ ናቸው።
Hammasini ko'rsatish...
15👏 9🥰 2👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
በአየር ፀባይ ምክንያት የተወሰኑ የሀገር ውስጥ በረራዎች ይቋረጣሉ – የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች በተከሰተው ጭጋጋማና ለበረራ አመቺ ያልሆነ የአየር ፀባይ ምክንያት የተወሰኑ የሀገር ውስጥ በረራዎች ይቋረጣሉ አለ፡፡ አየር መንገዱ ባወጣው መግለጫ በአሁኑ ወቅት ያጋጠመው የአየር ፀባይ ለተወሰኑ ቀናት የሚቀጥል መሆኑን ከሚቲዎሮሎጂ መረጃ መሰረት ለማወቅ ተችሏል ብሏል፡፡ በዚህ ምክንያት ወደተወሰኑ የሀገራችን ክፍሎች የሚያደርጋቸውን… https://www.fanamc.com/archives/306559
Hammasini ko'rsatish...
10👍 6
Hammasini ko'rsatish...
5👍 3
Photo unavailableShow in Telegram
ቼልሲ ከኒውካስል ዩናይትድ ጋር አቻ ተለያየ አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ17ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ከሜዳው ውጭ ኒውካስል ዩናይትድን የገጠመው ቼልሲ 2 ለ 2 አቻ ተለያይቷል፡፡ ባለሜዳው ኒውካስል በቮልትማደ ሁለት ግቦች 2 ለ 0 ሲመራ ቢቆይም፥ ቼልሲ በሪስ ጀምስ እና ዦአዎ ፔድሮ ግቦች ነጥብ ተጋርቶ ወጥቷል፡፡ የሊጉ መርሐ ግብር ሲቀጥል ማንቼስተር ሲቲ ከዌስትሃም፣… https://www.fanamc.com/archives/306556
Hammasini ko'rsatish...
20👏 2
Photo unavailableShow in Telegram
ገናን ከፋና #ዲጂታል፣ ከፋና #ፖድካስት፣ ከፋና #ቴሌቪዥን፣ ከፋና #Plus እና ከ13 #ሬዲዮዎች ጋር ያድርጉ! ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን
Hammasini ko'rsatish...
6👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
የተቀናጀና በጥናት ላይ የተደገፈ መፍትሔ የሚጠይቀው የፍልሰት ጉዳይ… አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የፍልሰት ችግርን በዘላቂነት ለመፍታት ተቋማዊ ትብብርና በጥናት ላይ የተደገፈ ምላሽ መስጠት ይገባል አሉ የትምህርት ሚኒስቴር አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ ክንደያ ገ/ህይወት (ፕ/ር)፡፡ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በፍልሰት ጉዳይ ላይ ያተኮረ የመጀመሪያውን ዓለም አቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ አካሂዷል። ክንደያ ገ/ህይወት (ፕ/ር) በመድረኩ ላይ ተገኝተው… https://www.fanamc.com/archives/306553
Hammasini ko'rsatish...
6👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ተጨባጭ ውጤት የተገኘበት የእቀባ እርሻ ዘዴ… አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአፈር ለምነትንን በማሻሻልና ውሃን በማቀብ በአነስተኛ ወጪ ከፍተኛ ምርት ማስገኘት የሚያስችለውን የእቀባ እርሻ ዘዴ በመጠቀም ተጨባጭ ውጤት ተገኝቷል አለ የክልሉ ግብርና ቢሮ፡፡ የቢሮው ምክትል ኃላፊ አድማሱ አወቀ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንዳሉት፥ የአየር ንብረት ለውጥና ሌሎች የተፈጥሮ ክስተቶች የሚያስከትሉትን ተጋላጭነትን ለመቋቋም የእቀባ እርሻ… https://www.fanamc.com/archives/306550
Hammasini ko'rsatish...
17👍 1
Hammasini ko'rsatish...
💩 2 1👍 1