es
Feedback
️ ንስር አማራ🦅

️ ንስር አማራ🦅

Ir al canal en Telegram

የተቀደሰን ነገር በእግሩ ለሚረግጥ ፥ተመልሶም ያጎረሰውን እጅ ለሚናከስ ርኩስ መጫወቻ የማይሆን የነቃ ማህበረሰብ እስክንፈጥር ድረስ ብዕራችን አይነጥፍም። አንድ አማራ ለሁሉም አማራ ፥ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ። 💚💛❤️ እኛን በውስጥ ለማናገር @NISIREamhra2 @NISIREamhraa_bot 👈 ይችን አድራሻ ይጠቀሙ🦅 ንስር ዐማራ🦅 #የግፉአን_ድምፅ t.me/NISIREamhra

Mostrar más
2025 año en númerossnowflakes fon
card fon
63 175
Suscriptores
-5024 horas
-2527 días
-80230 días
Archivo de publicaciones
🔥ለህዝብ ደህንነት ሲባል መንገድ ዝግ መሆኑን ስለማሳወቅ‼️ ══════❁✿ ❁══════====== አፋብኃ ቴዎድሮስ እዝ 105ተኛ ኮር 55ተኛ ክ/ጦር በሚያስተዳድራቸው ቀጠናዎች የህዝብን ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል መንገድ የተዘጋ መሆኑን ስለማሳወቅ፣ በሆዱ ተገዝቶ የአብይ አህመድ አሊን ወንበር ለመጠበቅ የሚዝረከረከው የጠላት ሀይል ፋኖን ዘራፊ ነው ለማስባል ፋኖ መሣይ ብልጽግናዎችን በማደራጀት ሹፌሮቻችንን እና ህዝባችንን እያገላታ መሆኑን ደርሰንበታል። በመሆኑም ህዝባችንን እና ሹፌሮቻችንን ከነዚህ ወንበዴዎች ዘረፋና ግድያ መከላከል ያመች ዘንድ ከነገ 13/04/2018 ዓ.ም ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መንገዶች ማለትም፦                    1.ከባህር ዳር ጭንባ ቁንዝላ ደለጎ                    2.ከዱርቤቴ ዝህብስት ወገዳ                    3.ከዱርቤቴ ሀሙሲት ማማላ                 4.ከዱርቤቴ _ቀደምት ላሊበላ ልሁዲ መንገዶች  ዝግ እንደሆኑ ማሳወቅ እንወዳለን ።ህዝባችንም በእነዚህ  ዘራፊ አካላት ላይ እርምጃ ወስደን ፣በማስተካከል በፍጥነት ክፍት ስለምናደርግ፣ እንደወትሮው ሁሉ በትግስት እንድትጠብቁን ስንል በአክብሮት እንጠይቃለን። ማሳስቢያ፦ ይህንን መልክት ጥሶ እገዳ በተጣለባቸው መንገዶች ሲንቀሳቀስ ለሚደርስበት ማንኛውም ችግር ኃላፊነቱን እራሱ ባለቤቱ የሚወስድ መሆኑን በድጋሜ እናሳውቃለን። አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ‼️ ©የአፋብኃ ምዕ/አ/ቀ/ቴዎድሮስ-ዕዝ የ105ኛ ኮር 55ኛ ክ/ጦር ህ/ግንኙነት ‎#ዐንድ_አማራ‼️ #ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️ #ምረር_አማራ💪 #ድል_ለአማራ_ፋኖ💪 #ድል_ለአማራ_ህዝብ💪 13/ዐ4/2018 ዓ.ም @NISIREamhra
Mostrar todo...
96👍 22🙏 2😡 1
🔥#በላይ_ዘለቀ_ሸለቃ ‎ከንጋቱ 11:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 1:00 የቀጠለ ተጋድሎ እያደረገ ነው‼️ ‎ታህሳስ : 12/ 2018 ዓ/ም ‎ ‎የአፋብኃ ምዕ/አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 99ኛ ክፍለጦር በላይ ዘለቀ ሻለቃ ከአማኑኤል ከተማ በሁለት አቅጣጫ ወደ ደብረቀለሞ /ደጋ ቀጠና/ የተንቀሳቀሰው   #የአራሙቻው ሰራዊት በማቻክል ህዝብ እና በበላይ ዘለቀ ሻለቃ ዋጋውን አግኝቶ ወደ መጣበት አማኑኤል ከተማ ተመልሷል። ‎ ‎የማቻክሉ በላይ ዘለቀ ሻለቃ በሌላ አውደ ውጊያ አማኑኤል ከተማ በመግባት በጠላት ላይ የስነልቦና ፣አካላዊ እና ቁሳዊ ጉዳት ማድረስ የተቻለ ሲሆን በርካታ የአረመኔው ሰራዊት #ተደምስሷል። ‎ ‎የተረፈው አታንበሳ/ወተበት ሚካኤል ቤተክርስቲያን ገብቶ ለማምለጥ ቢሞክርም #የማቻክል ተርቦች ተስበው  #እየቀጠቀጡት ነው። ‎አውደ ውጊያው አሁንም እንደቀጠለ ነው። ‎ ‎ድል ለአማራ ፋኖ! ‎አዲስ ትውልድ ፤አዲስ አስተሳሰብ ፤አዲስ ተስፋ ©‎የአፋብኃ ምዕ/ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 99ኛ ክ/ጦ ህዝብ ግንኙነት! ‎#ዐንድ_አማራ‼️ #ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️ #ምረር_አማራ💪 #ድል_ለአማራ_ፋኖ💪 #ድል_ለአማራ_ህዝብ💪 12/ዐ4/2018 ዓ.ም @NISIREamhra
Mostrar todo...
star reaction 13 89👍 25🙏 5💔 5
🔥ሚኒሊክ ዕዝ ልጅ ዕያሱ ኮር የጎፍ ክፍለጦር የብልግናን ስብሰባ መበተን ሲችል በላጎ ተወርዋሪ ሻለቃ ደሴ ዙሪያ ወረዳ እና ኩታበር ወረዳ ባደረጉት ተጋድሎ አራት ቀበሌዎችን መቆጣጠር ችለዋል‼️      ከየጎፍ ክ/ጦር ስበርና መብረቅ ሻለቃ የተውጣጡ አናብስቶች በደቡብ ወሎ ዞን ወረኢሉ ወረዳ ካቤና ጉጉፍቱ ከተሞች ህዝብን ሰብስቦ የውሸት ማደናገሪያ ሊነዛ በነበረው የብልፅግና ሆድ አደረሮች ላይ በድንገት መብረቃዊ ጥቃት በመክፈት ስብሰባውን የበተኑና ህዝቡን የታደጉ ሲሆን ህዝባቸው በሆዳቸው የሸጡ ትርፍ አንጀቶች በቁማቸው እየሸኑ ወደ ወረኢሉ እና ወደ ደሴ አምልጠዋል ሲል አርበኛ ሱልጣን የሱፍ አፋብኀ ሚኒሊክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮር የየጎፍ ክ/ጦር ህዝብ ግንኙነት ለንስር አማራ ገልጿል። 👉በላጎ ተወርዋሪ ሻለቃ ዛሬ ታህሳስ 12/2018 ዓ.ም ንጋት ጀምሮ በደቡብ ወሎ ደሴ ዙርያ ወረዳና ኩታበር ወረዳ ባደረጉት ተጋድሎ ታላቅ ድል ተቀዳጅተዋል:: በተጋድሎዉም በጠላት ይዞታ የነበሩ ከተሞች ነጻ ወጥተዋል። ነጻ የወጡት ከተሞች አያታ፣ፋላ ፣ጽድ ገበያ፣ አጥንት መስበርያ የተባሉ ከተሞች ሲሆኑ በተጋድሎዉም የአብይ አህመድ ዙፋን ጠባቂ መከላከያ፣አድማ ብተና እና ሚሊሻ ከፍተኛ የሆነ ሰብዓዊ ኪሳራ አስተናግደው ሙትና ቁስለኛቸውን ይዘው ወደ ደሴ ፈርጥጠዋል ሲል የዕዙ ህ/ግንኙነት ክፍል ለጣቢያችን ገልጿል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! ©የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ #ዐንድ_አማራ‼️ #ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️ #ምረር_አማራ💪 #ድል_ለአማራ_ፋኖ💪 #ድል_ለአማራ_ህዝብ💪 12/ዐ4/2018 ዓ.ም @NISIREamhra
Mostrar todo...
45👍 42😢 1
🔥የሳጅን አደም አሊ (አባ ናደው) ክፍለ ጦር ፋኖዎች ታላቅ የጦር ሜዳ ጀብዱ ፈፀሙ:: አንድ ተሽከርካሪ ሙሉ ጠላት ከጥቅም ውጭ ተደርጓል‼️ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ሳጅን አደም አሊ (አባ ናደው) ክፍለ ጦር 1ኛ (ሸዋንግዛው ካሣ) ሻለቃ ፋኖዎች በምዕራብ ወሎ ግንባር ለጋምቦ ወረዳ ውስጥ ከገነቴ ከተማ ወጣ ብሎ የሚገኝ ቦታ ላይ ደፈጣ ጥለው ከደሴ ወደ አማራ ሣይንት በመጓዝ ላይ ያለ የጠላት ኃይልን ድባቅ መተዋል:: ዛሬ ታህሳስ 12 ቀን 2018 ዓ.ም አመሻሽ ላይ የሻለቃይቱ ፋኖዎች በጠላት ላይ በፈፀሙት የደፈጣ ጥቃት ተሽከርካሪው ላይ ያለው ጠላት ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጭ ሆኗል:: በተሽከርካሪው ተጭኖ ሲጓጓዝ ከነበረው የጠላት ኃይል መካከል አንድ አድማ ብተና በህይወት ተርፎ ሲማረክ ሌሎች ዶግ አመድ መሆናቸው ተረጋግጧል:: በአርበኛ አለልኝ ተሰማ የሚመራው የሳጅን አደም አሊ (አባ ናደው) ክፍለ ጦር ሰራዊት በቅርቡ ሪፎርም ሰርቶ ወደ ግዳጅ ከገባ ወዲህ በየዕለቱ በሚባል ደረጃ ታሪክ እየሰራ መሆኑን ልብ ይሏል:: ሰራዊቱ ባለፈው ወር ወታደራዊ እና የፓለቲካ ስልጠና ወስዶ እና ተበውዞ ሁሉም በሚባል ደረጃ ከሰፈሩ ወጥቶ የሚታገልበት ዕድል በመፈጠሩ የተነሳ አሁን ላይ የክፍለ ጦሩ ሰራዊት ተወርዋሪ ከመሆኑ ባሻገር የማድረግ አቅሙ በብዙ እጥፍ ጨምሯል ሲል የክፍለ ጦሩ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ ይመር ሁሴን ለምኒልክ ዕዝ በላከው ሪፓርት ገልጿል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! ©አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ #ዐንድ_አማራ‼️ #ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️ #ምረር_አማራ💪 #ድል_ለአማራ_ፋኖ💪 #ድል_ለአማራ_ህዝብ💪 12/ዐ4/2018 ዓ.ም @NISIREamhra
Mostrar todo...
63👍 24
🔥ማረጉ ተማረ ክፍለ ጦር ከ54 በላይ የአገዛዙን ሰራዊት በመደምሰስ ከ71 በላይ በማቁሰል ታላቅ ድል ተጎናፀፉ‼️ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ላስታ ጄኔራል አሳምነዉ ፅጌ ኮር ማረጉ ተማረ ክፍለ ጦር ባደረገው ከባድ ትንቅንቅና ተጋድሎ በጠላት ላይ የበላይነትን በመቀዳጀት ታላቅ ጀብዱ ፈፀመ። የብርሃኑ ጁላ ሰራዊት ታህሳስ 12/2018 ዓ.ም ከሌሊት ጀምሮ ማረጉ ተማረ ክፍለ ጦርን ለማፈን በሚል በአራት አቅጣጫ ማለትም ከእንጃፋት በዝጊት አዲስ አለም አቅጣጫ፣ከጥጉ ቀበሌ በድፍቋ ፈረስ መጋለቢያ አቅጣጫ፣ከብልባላ መዛርድ በፀዳ ወንዝ አቅጣጫ እና ከላሊበላ በጉርዱ በር ዳጉሶች አቅጣጫ የመጣውን ኃይል ቀድመው መረጃው የደረሳቸው ነበልባሎቹ ወሳኝ ቦታዎችን በመያዝ ከንጋቱ 12:30 ሰዓት እስከ ቀኑ 8:30 ሰዓት ድረስ በየመጣበት አቅጣጫ የጠላትን ኃይል ሲያራግፉት ውለዋል። በክንደ ነበልባሎቹ የአሳምነው ልጆች የተገረፈው የአገዛዙ ወንበር አስጠባቂ ሰራዊት አዲስ አለም ከምትባል ጥንስስ ከተማ ላይ ከ54 በላይ ሲደመሰስ ከ71 በላይ ቁስለኛውን በየሸጡና ሸለቆው እየለቀመ ውሏል። በተያያዘ መረጃ ጄኔራል ኃይሉ ከበዴ ክፍለ ጦር ለማረጉ ተማረ ክፍለ ጦር ደጀንነቱን በማሳየት የደረሰ ሲሆን በድፍቋ አቅጣጫ የመጣውን የብልፅግና ሰራዊት መሃል በመቁረጥ መግቢያ መውጫ እንዳያገኝ በማድረግ ከ20 በላይ በመደምሰስና ከ32 በላይ ቁስለኛ በማድረግ የጄኔራሉ ልጆች ታላቅ ጀብዱ ተጎናፅፈዋል። በመጨረሻም አንድነት ኃይል ነው የሚለውን መርህ በመከተል ማረጉ ተማረ ክፍለ ጦርና ጄኔራል ኃይሉ ከበዴ ክፍለ ጦር በጋራና በመናበብ የጠላትን ኃይል አንገት ያስደፉበት ጥምረት ለሌሎችም አርኣያ የሆነ ቅንጅት ነው ሲሉ የክፍለ ጦር አመራሮች መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር  ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ መምህር ቢሆነኝ ቢያበይን መረጃውን አድርሷል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! ©የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ #ዐንድ_አማራ‼️ #ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️ #ምረር_አማራ💪 #ድል_ለአማራ_ፋኖ💪 #ድል_ለአማራ_ህዝብ💪 12/ዐ4/2018 ዓ.ም @NISIREamhra
Mostrar todo...
77🙏 15👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
🔥አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) ክፍለ ጦር ደቡብ ወሎ ዞን ለጋምቦ ወረዳ ውስጥ 18 የጠላት ኃይል በመደምሰስ ድል ተጎናፀፉ‼️ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ሳጅን አደም አሊ (አባ ናደው) ክፍለ ጦር 1ኛ ሸዋንግዛው ካሣ ሻለቃ ትናንት ታህሳስ 10 ቀን 2018 ዓ.ም ድል ቀንቶታል:: የጠላት ኃይልን ጭኖ ከአማራ ሳይንት ተነስቶ ወደ ለጋምቦ ወረዳ ለመግባት ሲጓዝ የነበረ ኤፍኤስአር ተሽከርካሪ ለጋምቦ ወረዳ ውስጥ ቡሶ ጊዮርጊስ የተባለ አካባቢ ላይ ሲደርስ የሳጅን አደም አሊ (አባ ናደው) ክፍለ ጦር 1ኛ ሸዋንግዛው ካሣ ሻለቃ ኃይል በሰነዘረው ጥቃት 14 የአድማ ብተና አባላት ሲቆስሉ 4 የሚሆኑት በውጊያ መሀል ተደምስሰዋል:: ይህ በውል የታወቀው አሀዝ ሲሆን የተጎጅዎች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ይገመታል:: የጠላት ኃይል በትናንትናው እለት ቁስለኛውን ለማንሳት ቢረባረብም እነ ሞት አይፈሬ የብረት አጥር ሆነው አላስጠጋው ስላሉ ባለፉት 24 ሰዓታት ቁስለኞቹን ለማንሳት ከየአቅጣጫው ያለ የሌለ ኃይሉን ጨምሮ መጥቶ እንደነበርም ነው ሳጅን አደም አሊ (አባ ናደው) ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ፋኖ ይማም ሁሴን ለምኒልክ ዕዝ በላከው ሪፓርት ያስታወቀው:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! ©አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ #ዐንድ_አማራ‼️ #ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️ #ምረር_አማራ💪 #ድል_ለአማራ_ፋኖ💪 #ድል_ለአማራ_ህዝብ💪 12/ዐ4/2018 ዓ.ም @NISIREamhra
Mostrar todo...
66👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
🔥#አስቸኳይና_አፈትላኪ_መረጃ‼️ የጠላት ኃይል ምርጫን አስመልክቶ በመላው አማራ እስከ ታች (ቀበሌ ድረስ) የሰላም ቀጠና መፍጠር ይፈልጋል። ይህም የሚሆነው ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ሰላም ነው ምርጫም ለማድረግ አስቻይ ሁኔታዎች አሉ ለሚል ፕሮፓጋንዳ ያመቸው ዘንድ ነው። ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ ያለ የለለ ኃይሉን በአየር ኃይል በመታገዝ ወረራ እየሞከረ ይገኛል። ለንስር አማራ ከአገዛዙ ሰዎች የደረሳት መረጃ እንደሚያመለክተው  #ከታህሳስ_15 ጀምሮ #ጮቄ_ለበሱን ቀጠና ይዞ እስከ ቢቸና ደብረወርቅ ያለውን ቀጠና #በእግረኛ#በሜካናይዝድና #በአየር_ሀይል የተቀናጀ ሙሉ ኦፕሬሽን ለመስራት ዝግጅቱን ጨርሶ የመጨረሻዋን #ፊሽካ እየተጠባበቀ ይገኛል። ስለሆነም በዚህ ቀጠና የምትንቀሳቀሱ አመራሮችና አባላት የስንቅ ፣ የትጥቅ ፣የስነልቦና እንዲሁም የሚያስፈልገው ሁሉ ዝግጅት እንድታደርጉ ማህበረሰቡም ከወዲሁ ዝግጁ እንዲሆን የንስር አማራ ወታደራዊ ምንጮች መልዕክት አስተላልፈዋል‼️ #ማሳሰቢያ፦ መረጃው ሾልኮ ስለወጣ ዘመቻውን ቀድመው ሊጀምሩ ስለሚችሉ በተጠንቀቅ እንጠብቅ፣ ከተጠቀሰው ቀጠና ውጭ ያላችሁ መላው የአማራ ቀጠናም ከወዲሁ ዝግጁ ይሁን‼️ #ዐንድ_አማራ‼️ #ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️ #ምረር_አማራ💪 #ድል_ለአማራ_ፋኖ💪 #ድል_ለአማራ_ህዝብ💪 12/ዐ4/2018 ዓ.ም @NISIREamhra
Mostrar todo...
👍 71 53😢 6
Photo unavailableShow in Telegram
🔥#የተቋም_እህልን_ለመዝረፍ_የመጠው የአገዛዙ ወራሪ ዘራፊ ኃይል በ64ኛ ክፍለ ጦር ጥምር ኃይል እና 1 ሬጅመንት ተደምስሶል‼️      ታህሳስ 12/2018 ዓ.ም አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር ጥምር ኃይል እና 1ኛ ሬጅመንት ታህሳስ 11/2018 ዓ.ም ከጥዋቱ 12:00 ሰዓት በሸበል በረንታ ሱሃ ተፋሰስ ቀበሌ ልዩ ቦታ ስኩት እየሱስ የተቋም እህልን ለመውሰድ የመጠው የአገዛዙ ወራሪ ዘራፊ ኃይል ላይ F1 ቦንብ የታገዘ የጨበጣ ውጊያ አድረገዋል። በሸበል በረንታ ሱሃ ተፋሰስ ቀበሌ የተቋም እህልን ለመዝረፍ ከቢቸና፣ የዕዱኃ እና መርገጭ ከተማ የተሰባሰበው የአገዛዙ ዘራፊ ኃይል በጀግኖቹ የበላይ ዘለቀ እና የሽፈራው ገርባው ልጆች በአደረጉት ከባድ ተጋድሎ አገዛዙ በየጣሸው ሙት እና ቁሰለኛውን አንጠባጥቦ ያቀደውን እቅድ ሳያሳካ ተቅበዝብዞ ቀረቷል። በዚህ እልህ አስጨራሽ አውደ ውጊያ የአገዛዙ ዘራፊ ሀይል በቁጥር ማወቅ ያልቻልነው በረካታ ሙት እና ቁስለኛ ሆኗል። 64ኛ ክፍለ ጦር ወታደራዊ መሪዎች እና የፋኖ አባላት ባደረጉት ተጋድሎ የአገዛዙ ኃይል ከቢቸና፣ የዕዱኃ መረገጭ ከተማ ተጨማሪ ሀይል በመያዝ በሱሃ ተፋሰስ ቀበሌ የኮሬ የኩበት እና ስኩት እየሱስ ቦታዎች ላይ በየጣሸው እና በየገደሉ የወደቁ ሙት እና ቁስለኞችን በመጫን ወደ መጣበት ቦታ ተመልሶ ሄዶል። ክብር ለጀግኖች ሰማዕታት አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!            ታህሳስ 12/2018 ዓ.ም ©አፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ሕዝብ ግንኙነት #ዐንድ_አማራ‼️ #ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️ #ምረር_አማራ💪 #ድል_ለአማራ_ፋኖ💪 #ድል_ለአማራ_ህዝብ💪 12/ዐ4/2018 ዓ.ም @NISIREamhra
Mostrar todo...
63👍 15
🔥የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው እዝ ከሰም ፪ኛ ኮር ነበልባል ክፍለ ጦር የሥራ ግምገማና ጥልቅ ተሃድሶ በማድረግ የአመራር ሪፎርም አደረገ‼️ በቀን 08/04/18 እና 09/04/2018 ዓ.ም ሁለት የቀን የፈጀ የሥራ ግምገማ በማድረግ የአፋብኃ ሴንትራል ኮማንድ አባልና የአሳምነው እዝ ከፍተኛ አመራር አርበኛ ፖሮፌሰር ማርከው መንግሥቴና የአፋብሃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው እዝ ከሰም ፪ኛ ኮር ዋና ሰብሳቢ መቶ አለቃ ይላቅ ብርሃኔ,  የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አረበኛ ደጉ ተሥፋዬና የሲቪል አሥተዳደር ጉዳዮች ኃላፊ አርበኛ እንዳልካቸው ግርማና ሃምሳ አለቃ ጎሽመው ኃይሌ የከሰም ኮር ወታደራዊ ዋና አዛዥ በተገኙበት የአመራር ሪፎርምና ምደባ ይፋ አድርገዋል። የነበልባል ክ/ጦር አመራሮችም 1ኛ.አርበኛ ሃምሳ አለቃ ፍቃዱ ጥላሁን ___የነበልባል ክፍለ ጦር ዋና ሰብሳቢ 2ኛ.አርበኛ መለሰ ውቤ ___ የነበልባል ከ/ጦር የድርጅት  ጉዳይ ኃላፊ 3ኛ.አስር አለቃ ሸዋቀና ኡርጌሳ የነበልባል ከ/ጦር የሲቪል አሥተዳደር ጉዳዮች ኃላፊ 4ኛ.አርበኛ በላይሁን  አድማሱ___  የነበልባል ከ/ጦር ወታደራዊ  ዋና አዛዥ 5ኛ.አርበኛ እምሽ  በጋሻው____የነበልባል ክ/ጦር ም/አዛዥ ለኦፕሬሽናል 6ኛ.አስር አለቃ ስመኝ አለማየሁ___የነበልባል ክ/ጦር ም/አዛዥ ለአሥተዳደር 7ኛ.አርበኛ ደሴ ሞገሴ___የነበልባል ክ/ጦር ም/አዛዥ ለሎጀስቲክ 8ኛ.አርበኛ ይላቅ ደረጀ___የነበልባል ክ/ጦር ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ 9ኛ.አርበኛ ሀብታሙ በለጠ___የነበልባል ክ/ጦር ፋይናስ ኃላፊ 10ኛ.አርበኛ ሞገስ ገበየሁ____የነበልባል ክ/ጦር ህ/ግንኙነት ኃላፊ 11ኛ.አርበኛ ሸጋው ንጉሴየነበልባል ክ/ጦር ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ 12ኛ.ሃምሳ አለቃ መክት ደበበ___ የነበልባል ክ/ጦር ም/ዘመቻ 13ኛ.አርበኛ በላይ ወልዴ___ የነበልባል ክ/ጦር ት/ት እና ስልጠና ኃላፊ 14ኛ.አርበኛ ሰለሞን ታየ___የነበልባል ክ/ጦር አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ 15.ሀይልዬ ደመቀወታደራዊ ስልጠናና ክህሎት ኃላፊ 16ኛ.አርበኛ ፀጋዬ የሻው_ፐርሶኔል 17ኛ.አርበኛ መርሻ ታዬ_ የነበልባል ክፍለ ጦር ፀኃፊ 18ኛ.መረጃና ደህንነት-----____? 19ኛ.አርበኝት ቃልዬ ነገሰ___ሴቶችና ማህበራዊ ዘርፍ ኃላፊ 20ኛ.አርበኛ ክፍሉ ኬሌቻ___ህክምና ቡድን ኃላፊ 21ኛ.አርበኛ ዋሴ አሰፋፈጠራና ቴክኖሎጂ ኃላፊ 22ኛ.አርበኛ እንግዳ ሰብስቤሚዲያና ሪፖርተር 23ኛ.ኦፕሬተር--------? 24ኛ.አርበኛ ውቤ የሺጥላ_መረጃና መሀንዲስ በኦዲትና ቁጥጥር 1ኛ.አርበኛ ዮሴፍ ግዛው___የነበልባል ክ/ጦር ኦዲትና ቁጥጥር ኃላፊ 2ኛ.አርበኛ ማሙሽ መካሻ___ምክትል ኦዲትና ቁጥጥር 3ኛ.አርበኛ ላቀ በለጠ___ኦዲትና ቁጥጥር    በወታደራዊ ህግ  ክፍል 1ኛ.አርበኛ ወርቅሸት ለማ ወታደራዊ ህግ ክፍል ሀላፊ 2ኛ.መቶ አለቃ አዛለ መኩሪያ_ህግ ክፍል 3ኛ.አርበኛ ስለሺ ሀ/ገብረኤል_ህግ ክፍል ሃብት አሰባሳቢዎች 1ኛ.አርበኛ ፀደቀ አለማየሁ_ሀብት አሰባሳቢ ሀላፊ 2ኛ.አርበኛ መለሰ ሀይሉም/ሀብት አሰባሳቢ በኦርዲናንሥና ንብረት 1ኛ.አርበኛ ኤፍሬም በዛብህ___ኦርዲናንስ ሀላፊ 2ኛ.አርበኛ ሽመልስ ገ/አምላክ___ም/ኦርዲናንስ 3ኛ.አርበኛ ውብሸት ብርሀነ___ንብረት ክፍል ለኦርዲናንስ 4ኛ.አርበኛ ዘውዱ ደምረው___ንብረት ክፍል ለኦርዲናንስ   ግዥዎች 1ኛ.አርበኛ እረታ ዘውዱግዥ ኃላፊ 2ኛ.አርበኛ ማሙሽ ጉዴታግዥ 3ኛ.አርበኛ ዳምጠው ጣሰው___ግዥ 4ኛ.አርበኛ ደሴው___ግዥ   በሰላምና ደህንነት 1ኛ.ዋና ሳጅን ሰይፈ ተስፋ__የህዝብ ደህንነትና ፀጥታ ኃላፊ 2ኛ.አርበኛ ሲሳይ ተሰፋ___ም/የህዝብ ደህንነትና ፀጥታ ኃላፊ    በፋይናንሥ 1ኛ.አርበኛ አማረብህ ሙሉጌታ_ም/ፋይናንስ ሀላፊ 2ኛ.አርበኛ ብረሀኑ በላቸው_ሒሳብ ሰራተኛ ለፋይናንስ 3ኛ.አርበኛ ምስክር የተሻ(ፈረንጁ)_ፀሐፊ ለፋይናንስ      በቀለብና አልባሳት 1ኛ.አርበኛ ብሩክ ገ/ስላሴ(አቢቲ)_ቀለብና እደላ ኃላፊ 2ኛ.አርበኛ አክሊል የተሻ_ቀለብና አልባሳት 3ኛ.አርበኛ ፍቃዱ መኮነን_ቀለብና አልባሳት   በጦር መሳሪያ ጥገና 1ኛ.አርበኛ ደርሰህ ተስፋ_ ጦር መሳሪያ ጥገና ክፍል ኃላፊ 2ኛ.አርበኛ ጥላየ የሺጌታ_ ጥገና   ትራንሥፖርት ሥምሪት 1ኛ.አርበኛ አበባየሁ ነገሰ_ትራንስፖርትና ስምሪት ሀላፊ 2ኛ.አርበኛ ተካበ መስፍን_ም/ትራንስፖርትና ስምሪት   ህግ አገልግሎት 1ኛ.አርበኛ ሽመክት ሙሉጌታ_ህግ አገልግሎት ኃላፊ 2ኛ.አርበኛ ጀማነህ ጎበና_ህግ አገልግሎት 3ኛ.አርበኛ ገዳ ሲሳይ_ህግ አገልግሎት 4ኛ.አርበኛ መንግስቱ ደመቀ_ህግ አገልግሎት 5ኛ.አርበኛ ላቀው ቦሰት_ህግ አገልግሎት 6ኛ.አርበኛ ሲሳይ ማሞ_ህግ አገልግሎት መሆናቸውን ይፋ አድርጓል። 💪ድል ለአማራ ፋኖ!!! 💪ሕልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!! 🙏ክብርና ሞገሥ ለትግሉ ሰማዕታት!! የነበልባል ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ክፍል።      ታህሳሥ 12/04/2018 ዓ.ም #ዐንድ_አማራ‼️ #ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️ #ምረር_አማራ💪 #ድል_ለአማራ_ፋኖ💪 #ድል_ለአማራ_ህዝብ💪 12/ዐ4/2018 ዓ.ም @NISIREamhra
Mostrar todo...
79👍 23🎉 2
🔥#በድሮን_የታገዘ_ዉጊያ_በሰከላ_ወረዳ_ተካሄደ‼ የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 44ኛ ክፍለ ጦር እና 109ኛ ኮር 77ኛ ክፍለ ጦር ጥምር ሀይል በድሮን የታገዘዉን ተጋድሎ በመቋቋም ከተለያዬ አካባቢ ተሰባስቦ የመጣውን በርካታ አረመኔ ቡድን አጉት ላይ ደምስሶታል‼ በትላንትናው ዕለት ታህሳስ 11/2018 ዓ.ም ከቀኑ 9:30 እስከ ምሽት 1:00 ድረስ በተደረገዉ እልህ አስጨራሽ ትንቅንቅ ሰከላ ወረዳ አጉት ቀበሌ ዙሪያ ከሚገኙ ሁለት አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ መሽጎ የሚገኘውን ዙፍን ጠባቂ ሰራዊት የያዘዉ የድንጋይ ካብ ሳያተርፈው ተደምስሷል። ለተከታታይ 3 ሰሃት በተደረገዉ የእጅ በእጅ የቦምብ ትንቅንቅ ለማትቀረዋ የነገ ነፃነት፤ ጀግኖቹ 44ኛ እና 77ኛ ክፍለ ጦር ነበልባሎች ዉድ ዋጋ በመክፈል ጡት ቆራጩን ቡድን፣ ጡትና ምላስ ብልት በቆረጠበት፤አሰቃቂ ድርጊት በፈፀመበት ሰከላ ቀጠና አጉት ላይ ቀብረዉ አስቀርተዉታል። አረመኔው ቡድን ለሳምንት ሲቆፍር ሲዘጋጅበትና አንገት ድረስ ሲሰራዉ የሰነበተዉ ምሽግ በነበልባሎቹ ሲደረማመስ መድረሻ ያጣዉ ወንበዴ ቡድን በእግር አልችል ብሎ በድሮን የታገዘ ዉጊያ በማድረግ ተከታታይ ሁለት የድሮን ቅንቡላ ቢጠቀምም ከመደምሰስ አላተረፈዉም። ቤተክርስቲያንን፣ንፁሃንንና፣ተራራ ላይ ጉድጓድ እንደ ቀበሮ በመቆፈር ለማምለጥ የሚሞክረዉ ዙፋን ጠባቂዉ ሰው በላው ቡድን በጀግኖች ከባድ ምት ተደቁሶ በቆፈረዉ ጉድጓድ አፈር ለብሶ ቀርቷል። በ105ኛ ኮር 44ኛ ክ/ጦር እና በ109ኛ ኮር 77ኛ ክ/ጦር ጥምር ሀይል የደረሰበትን ሽንፈት መቋቋም ያቃተው ጡት እና ምላስ ቆራጩ የጠላት ሀይል ከሽንዲና ከተለያዬ ቦታ በማሰባሰብ መቀበሪያው ወደ ሆነው ወደ ሰከላ ወረዳ አጉት ከተማ ተጨማሪ ሀይል አስገብቷል። #ላንጨርስ_የጀመርነዉ_ትግል_የለም_ድላችን_ቅርብ_ነዉ_እንበርታ💪 #በደማችን_ታሪካችንን_እናድሳለን💪 ©የ44ኛ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት ‼ #ዐንድ_አማራ‼️ #ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️ #ምረር_አማራ💪 #ድል_ለአማራ_ፋኖ💪 #ድል_ለአማራ_ህዝብ💪 12/ዐ4/2018 ዓ.ም @NISIREamhra
Mostrar todo...
104👍 26👏 2🙏 2
🔥#ትውልዱ_ሁሉ_የትውልዱ_ምልክት_አይሆንም‼️ በየትኛውም ሀገርና ታሪክ ውስጥ የትውልዳቸውን እጣ ፈንታ የበየኑ እና የታሪክን እጥፋት ያሰመሩ ግለሰቦች የትውልዶቻቸው ምልክት ተደርገው ይወሰዳሉ።በአዲሱ ትውልድ እየተቃኘ የሚገኘው የአማራ ህዝብ ትግል ብያኔም ከዚህ የተለየ አይሆንም።እንደረመጥ የሚያንገበግብ ህዝባዊ አላማቸውን በውስጣቸው ይዘው ሰርክ የሚታትሩ እና ከሩቅ የሚያንፀባርቅ ርዕይን አንግበው ትውልዱን በዓላማቸው ጥላ ስር ለማሰባሰብ ያለመታከት ቀን ከሌት እየተጉ የሚገኙ ምልክቶቻችን አሉ።ትውልዱ እስከወዲያኛው ይድን ዘንድ ጥቂት ከጊዜና ከአድማስ ቀድመው የሚያስቡ አስበውም የሚራመዱ የትውልዱ መገለጫ ምልክቶች ካሉ በቂ ነው።ሌላውና እልፍ እንዲሆን የሚጠበቀው እነኚህ የትውልዱ ምልክቶች ያሰመሩለትን የመድህን ሀዲድ ተከትሎ የሚራመድ አብዛኛው ጊዜውን፣ ጉልበትን፣ ሀብቱንና አዕምሮውን የዕለት ከዕለት ችግሮችን በመፍታትና በማስተዳደር ላይ እንዲያውል ይጠበቅበታል እንጅ እኔም በአቅሜ የትውልዱ ምልክት ካልሆንኩ ወደሚል መታበይ ውስጥ እንዲገባ አይጠበቅበትም።ስለሆነም አዲሱ ትውልድ እስከወዲያኛው ህልውናው ተረጋግጦ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ሰማይ ስርም ሆነ በሰብዕና ካርታ ውስጥ ሚና ያለው ተዋናይ እንዲሆን ካስፈለገ ጥቂት ባለ ራዕይ መሪዎች እና ዕልፍ ተልዕኮ ፈፃሚ አስተዳዳሪዎችን ሊያፈራ ይገባል። ©አርበኛ ዳሞት አለኸኝ 206ኛ ኮር ሰብሳቢ #ዐንድ_አማራ‼️ #ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️ #ምረር_አማራ💪 #ድል_ለአማራ_ፋኖ💪 #ድል_ለአማራ_ህዝብ💪 11/ዐ4/2018 ዓ.ም @NISIREamhra
Mostrar todo...
104👍 51👏 10
Photo unavailableShow in Telegram
🔥#ሰባት የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ ወታደሮች ሐውጃኖ ክፍለ ጦርን ተቀላቀሉ‼️ የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት 83ኛ ክፍለ ጦር አራት አባላትና ሶስት የሪፐብሊካን ጋርድ አባላት በአጠቃላይ ሰባት ሰራዊት ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ምስራቅ አማራ ኮር 1 ሐውጃኖ ክፍለ ጦርን የተቀላቀሉ ሲሆን አመራሮችም አቀባበል አድርገውላቸዋል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!        ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! ©የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ #ዐንድ_አማራ‼️ #ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️ #ምረር_አማራ💪 #ድል_ለአማራ_ፋኖ💪 #ድል_ለአማራ_ህዝብ💪 11/ዐ4/2018 ዓ.ም @NISIREamhra
Mostrar todo...
102👍 28🎉 8💔 5😢 3🙏 1
Photo unavailableShow in Telegram
🔥#ለሚመለከተው_ሁሉ‼️ ታሕሳስ 11/2018 ዓ.ም አማራ ላይ የተደቀነን የህልውና አደጋ ለመቀልበስና የተከፈተብንን ጦርነት በድል በመወጣት አማራን ብሎም መላው ኢትዮጵያውያን የፍትህ ፣ የነፃነትና የእኩልነት... (ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብት ) የሚከበርበት ስርዓተ መንግስት ለመገንባት ትንቅንቅ ከጀመርን እንሆ ሁለት አመት ከአምስት ወር አስቆጥረናል። በእነዚህ ግዜያት በርካታ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ መስዋዕትነት ከፍለን ከተበታተነ አሰራር ፣ ከውስን ሰራዊትና መሳሪያ ዛሬ ላይ አንዲት ሀገር ሊኖራት የሚገባ የመሳሪያ አይነት ፣ሰራዊት እንዲሁም መዋቅር ላይ እየደረስን እንገኛለን። በዚህ ሂደት ትግላችን የጉዞ #ሀዲዱን ጠብቆ በፍጥነት #ይምዘገዘግ ዘንድ ሌት ከቀን የሚሰሩ ጀግኖች እንዳሉ ሁሉ ትግላችን እንዲከስም የትግላችንን የጉዞ #ሀዲድ ቢችሉ ትግሉ አፈር ድሜ እንዲበላ ሀዲዱን #ድልድዩ ላይ #መደርመስ ካልቻሉ ደግሞ ሀዲዱነ መስመሩን በመቀየር ዋጋ እያስከፈሉንና ሊያስከፍሉን ሌት ከቀን እየሰሩ ያሉ ከቲም መሪ እስከ ከፍተኛው መዋቅር የተሳሰረ ውስብስብ አጥፊ ቡድን እንዳለ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ስለሆነም #ዘመቻ_ማጥራት በአመራሮች ላይ እንዲደረግና የትግል ሾተላዩ ብድን እየተነቀለ እንዲወጣ በትህትና እንጠይቃለን‼️ እነዚህ ቡድኖች፦ 👉ታጋይንና ህዝብን የሚያሳላች ተግባር መፈፀም 👉የወገንን እንቅስቃሴ ለጠላት አሳልፎ በመስጠት በእግረኛ ወይንም በአየር ኃይል ጥቃት ማስከፈት! 👉ወንድም ከወንድሙ እንዲተኳኮስ ትዛዝ መስጠት፣ አልቀበልም ያለን በሴራ ማፅዳት! 👉ሀቀኛ ታጋዮችንና አመራሮችን ንፁህ የትግል ሜዳ በማቆሼሽ ከትግሉ ለማራቅ መሞከር ሲበዛም በሴራ ማሰርና ማፅዳት 👉የራስን ቡድን ለማደራጀት መሞከር እነዚህንና መሰል ነገሮች እየሰሩና እያሰሩ በመሆኑ በድርጅቱ አሰራር መሰረትና የአማራን ትግል ከግንዛቤ ያስገባ እርምጃ እንዲወሰድ በሚዲያችን ፣በታጋዩና በአማራ ስም በትህትና እንጠይቃለን‼️ መላው የአፋብኃ ዕዝ የሚመለከት ቢሆንም በዋናነት ለአፋብኃ ምዕራብ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ይድረስ!! 👉ለአርበኛ ዘመነ ካሴ የአፋብኃ ሴንተራል ኮማንድ አባልና የቴዎድሮስ ዕዝ ሰብሳቢ! 👉ለሻለቃ ዝናቡ ልንገራው የአፋብኃ ሴንተራል ኮማንድ አባልና የቴዎድሮስ ዕዝ ወታደራዊ አዛዥ! 👉ለ፻ አለቃ አበበ ሰውመሆን የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ ዘመቻ መምሪያ! 👉ለሚለከተው ሁሉ! ©ንስር አማራ #ዐንድ_አማራ‼️ #ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️ #ምረር_አማራ💪 #ድል_ለአማራ_ፋኖ💪 #ድል_ለአማራ_ህዝብ💪 11/ዐ4/2018 ዓ.ም @NISIREamhra
Mostrar todo...
182👍 32💯 8🫡 6👏 5💔 5🙏 1
🔥#ለአዲስ_ቅዳም_ከተማ_እና_አካቢዉ #ኗሪዎች_የተላለፈ_ግልፅ_ማስጠንቀቂያ‼️ ከዉሾ ጋር የተገኘ ዉሾ ነዉ!!! ከሰሞኑ በፀረ አማራዉ አብይ አህመድ ተቀዳሚ ጋሻ ጃግሬ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ የሚመራ የአሸባሪዉ ብልፅግና ቡድን በአንዳንድ የጎጃም ከተሞች እየተዟዟረ የቃየልን መቅበዝበዝ በመተግበር ላይ እንደሆነ ይታወቃል። ከዚህ ጋር በተያያዘ ደመ ጠጪዉ ቡድን የፊታችን ሰኞ ታህሳስ 13/2018 ዓ/ም #አዲስ_ቅዳም ከተማ ዉስጥ በመገኘት የእብድ ዉሻ ለሀጩን ሊያዝረበርብ መዘጋጀቱን ደርሰንበታል። ይህ ፀረ አማራ ቡድን አዲስ ቅዳም ከተማ እና አካባቢዉ በሚኖር ህዝባችን ላይ ሊተፋ ላሰበዉ የክፉ ልክፍት ልሀጭ ተግባሩም ሁኔታዎችን እንዲያመቻቹለት ከማህበረሰቡ ዉስጥ የተወሰኑ ግለሰቦችን መልምሎ የተለያዩ ተልዕኮዎችን እንደሰጣቸዉ ከዉስጥ ቀኘወቻችን ማረጋገጥ ችለናል። የተልዕኮ አይነት እና ተልኮ ተቀባይ ግለሰቦችን በተወሰነ መልኩ ስንገልፅም፦ ተልዕኮ 1 <የስብሰባ ወቅት  ተናጋሪ> ይህ የባንዳነት ተልዕኮ ከተሰጣቸዉ ዉስጥ፦ 1ኛ  እጅጉ አያሌው |የታገል እጅጉ አባት| 2ኛ አዳሙ ሁነኛው |ጥቃቅን| 3ኛ ተሰማ ማሩ 4ኛ አለሙ ስዬም 5ኛ ሳምሶን እጅጉ |የታገል እጅጉ ወንድም| 6ኛ እሱባለው ገድፈዉ 7ኛ ቢረስ ከበደ 8ኛ አበባዉ ላቀ ተልዕኮ 2 <የስብሰባ ሎጅስቲክ አመቻች ኮሚቴ> በዚህ የባንዳነት ተግባር ከሚሳተፉት መካከል 1ኛ አዱኛ በላይ 2ኛ ግርማ ክንዴ 3ኛ አለማየሁ ሞገስ 4ኛ አበራ ይመር ተልዕኮ 3 <ደብል_ኤጀንት> 1ኛ በቃሉ መለሰ |የገቢዎች ባለሙያ|  እና ቢጫ ካርድ ላይ የሚገኙ ግለሰቦች ሲሆን ሌሎች ተልዕኮዎችንም የተቀበላችሁ ግለሰቦች መኖራችሁን ተልዕኮዉን ከሰጣችሁ ግለሰብ እኩል መረጃዉ አለን። በመሆኑም ከላይ ስማችሁ የተዘረዘረም ሆነ ስማችሁ ያልተዘረዘረ ግለሰቦች በዚህ ተግባር መገኘት በፀረ አማራነት እንደሚያስፈርጅ ማሳወቅ እንወዳለን። እንዲሁም የአዲስ ቅዳም ከተማ እና አካባቢው ኗሪ ማህበረሰባችን ከዚህ ፀረ አማራ ጉባዔ ባለመሳተፍ ጉባዔውን ተከትሎ ከሚደርስ ማንኛውንም አይነት አደጋ እራሳችሁን እንድታተርፉ ወገናዊ የሆነ ማሳሰብ ይድረሳችሁ ብለናል። አዲስ ትዉልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ! ©የአፋብኃ ቴዎድሮስ እዝ 105ኛ ኮር 44ኛ ክ/ጦር  ፲/አ ኤፍሬም አጥናፉ ሻለቃ ታህሳስ 11/2018 ዓ/ም #ዐንድ_አማራ‼️ #ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️ #ምረር_አማራ💪 #ድል_ለአማራ_ፋኖ💪 #ድል_ለአማራ_ህዝብ💪 11/ዐ4/2018 ዓ.ም @NISIREamhra
Mostrar todo...
120👍 42🏆 6💔 6
Photo unavailableShow in Telegram
🔥#ዙ23ቱ_ከእነ_ተኳሾቹ_ወደሙ💪 ፅናት ክፍለ ጦር የጠላት ዙ23 የወደመበትና ተኳሾቹ ሙሉ ለሙሉ በተደመሰሱበት ተጋድሎ ድል ተጎናፀፉ::   በድል ታጅቦ ተጠናክሮ በቀጠለው የደጋው መብረቅ ኮር ተጋድሎ ፅናት ክፍለ ጦር ዙ23ቱን በዲሽቃ በማውደምና እውክታ እንዲገጥመው ብሎም ከውጊያ ሜዳ እንዲወጣ በማድረግ በተጨማሪም ተኳሾቹን ሙሉ ለሙሉ በመደምሰስ እንዲሁም በርካታ እግረኛ ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ታላቅ ድል አስመዝግበዋል:: ታህሳስ 10/2018 ዓ/ም ከዚሃ መልስ እስከ ግሸን፤ከደላንታን ወረዳ እስከ ተሪ ጥላት አድማሱን አስፍቶ ከፅናት ክፍለ ጦር አናብስቶች ጋር ግጥሚያ አድርጎ የዋለ ሲሆን፤ የአማራ ህዝብ የቁርጥ ቀን ልጆች የሆኑት ፋኖዎች የፋሽስቱን ዙ23 በድሽቃ በመምታት እውክታ እንዲገጥመው ያደረጉት ሲሆን  ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ የፋሽስቱ ሰራዊቶች ሙትና ቁስለኛ ሆነዋል:: ከፅናት ክፍለ ጦር ያልጠበቀው ድብደባ የደረሰበት የጥቁሩ ፋሽስት ሰራዊቶች እግሬ አውጭኝ በማለት በሶስት አቅጣጫ ፈርጥጦ ወደመጣበት የተመለሰ ሲሆን በተጋድሎው ተተኳሽና የተለያዩ ሬሽኖች ሲማረክ፤ ሬሽኖቹን የተመረዙ ሊሆኑ ስለሚችሉ በማለት ወዳውኑ ጥቅም ላይ እዳይውል ተደርጓል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን! ©የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) የደጋው መብረቅ ኮር ህ/ግ ክፍል #ዐንድ_አማራ‼️ #ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️ #ምረር_አማራ💪 #ድል_ለአማራ_ፋኖ💪 #ድል_ለአማራ_ህዝብ💪 10/ዐ4/2018 ዓ.ም @NISIREamhra
Mostrar todo...
169👍 12😢 3😍 2🙏 1💔 1
🔥#ጥብቅ_የጥንቃቄ_መልዕክት❗️ #ሸር ይደረግ ከክልል እሰከ ቀበሌ ያለዉ የብልፅግና መዋቅር በክልል እና በዞን ደረጃ ለወረዳ አመራሩ የተሰጠ ተዕልኮ 1, ሁሉም አመራር ነፃ በወጡ ቀጠናዎች በከፈተኛ ደረጃ የምርጫ ዝግጅት ማድረግ አለባቹህ። 2,ህዝብን ማወያየት እና ፋኖን ከህዝብ መነጠል 3, ፋኖን አውግዞ ማስረዳት ለህዝብ 4, በሃገር ሽማግሌዎች ፋኖዎችን ማስከዳት 5, ቀበሌዎችን ማዋቀር 6, በቀበሌ የኢህአዴግ እና የደረግ አመራሮችን መያዝ አለባቹህ 7,ወሳኝ ወሳኝ የፋኖ መረጃዎችን ማሳደድ ግራ እና ቀኝ 8,የምረጫ ታዛቢዎችን ማዘጋጀት አለባቹህ 9,ለ7ኛው ሀገራዊ ምረጫ የፀጥታ ሃይል በከፈተኛ ደረጃ ማዋቀር 10,የፀጥታ ሀይል የስነልቦና ግንባታ መስጠት 11,ገቢ መሰብሰብ 12, በከፈተኛ ደርጃ ኬላዎችን ማጠናከር 14,በለሊት ከፋኖ ካምፕ ማጥቃት 15, ኦፒዎችን ከፋኖ ውስጥ ማዘጋጀት 16, አንዳንድ የብልፅግና አመራሮች አፋቹህ ብልፅግና ልባቹህ ግን ፋኖ የሆናችሁ መቆጠብ አለባቹህ። 17, ከፋኖዎች ውስጥ አመራር ገሎ እንዲመጣ ማዋቀረ አለባቹህ 18,የመታገያ ሚዲያዎችን ማሰደግ እና መደገፋ 19,የተቋም ንብረቶችን መለየት 20, የኮሩን አደረጃጀት በሴራ ማዳከም እና መበተን አለባቹህ 21, የአገለሉ የፋኖ ሽፋታዎችን ስቦ ማምጣት አለባቹህ። የሚል ትዛዝ ከብልፅግናው መንደር ትዛዝ ወርዷል‼️ #ማሳሰቢያ❗️ ውድ የፋኖ አመራሮች እና አባሎች ለብልፅግና አመራር እንደ ቃሪያ ካለበለብከው አወዳደቃችን ይከፋል በኛ ስነ ልቦና እየገቡ እነሱ የአሸነፉ እንዳይመስላቹህ ባዶ ቀፎ የቀራቸው የኛ አንድነት ብቻ ነው የሚጎለን፣ አንድነቱ በፍጥነት ይቋጭና ወደ ሙሉ ማጥቃት ይሸጋገር ይህ ካልሆነ ዋጋ ያስከፍላል‼️ #ዐንድ_አማራ‼️ #ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️ #ምረር_አማራ💪 #ድል_ለአማራ_ፋኖ💪 #ድል_ለአማራ_ህዝብ💪 10/ዐ4/2018 ዓ.ም @NISIREamhra
Mostrar todo...
106👍 26🙏 9
🔥#የምርኮ_ማስረጃ‼️ አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒሊክ ዕዝ ምስራቅ አማራ ኮር 2 ታጠቅ ክፍለ ጦር መርሳ ግንባር ታህሳስ 8/2018 ዓ.ም የማረኩት አንድ ብሬን እና 23 ክላሽ ከበርካታ ተተኳሽ እና ሌሎች ወታደራዊ ቁሳቁሶች ጋር በምስል ማስረጃ! #ዐንድ_አማራ‼️ #ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️ #ምረር_አማራ💪 #ድል_ለአማራ_ፋኖ💪 #ድል_ለአማራ_ህዝብ💪 10/ዐ4/2018 ዓ.ም @NISIREamhra
Mostrar todo...
86👍 20🏆 9
Photo unavailableShow in Telegram
🔥#መንገድ_ተከፍቷል‼️ ከነገ ታህሳስ 11/2018 ዓ.ም ጀምሮ ከጎንደር ከተማ አዲዘመን መንገድ ለመንገደኞች ክፍት ተደርጓል!!   ከማጥራትና ማብቃት ተልዕኮ ጋር በተያያዘ   የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) በላይ ዘለቀ ዕዝ ዳ/ቴዎድሮስ ፭ኛ ኮር ከታህሳስ 01/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታህሳስ 10/2018 ዓ.ም ከጎንደር ከተማ አዲዘመን ድረስ ዝግ እንዲሆን ተደርጎ የማጥራትና ማብቃት ስራ እየተከወነ ቆይቷል። በተለያዩ ዕኩይ ፍላጎቶች በመስመሩ እየተገኙ መንገደኞችን ያንገላቱ የነበሩ ቅጥረኛ ወሮበሎች ላይ በተወሰደ ርምጃ አንፃራዊ ለውጥ የታየ ቢሆንም ቀሪ ስራዎችን እየሰራን እንገኛለን። ስለሆነም የሚከተሉትን ማሻሻያዎች በጊዜያዊነት አስቀምጠናል። 1ኛ .መንገዱ ከነገ ታህሳስ 11/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለመንገደኞች ክፍት እንዲሆን፣ 2ኛ.ላልተወሰነ ጊዜ በኮሩ ፈቃድ ተጥለው የነበሩ ኬላዎች እንዲነሱ፣ 3.በኮሩ የበላይ አመራር ስምሪት ከተሰጠው አካል ውጭ ማንኛውም የታጠቀ አካል በመስመሩ 5 ኪ.ሜ ርቀት እንዳይገኝ፣ ትዕዛዙን ተላልፎ በተገኘ ማንኛውም የታጠቀ አካል ላይ የማያዳግም እርምጃ እንዲወሰድ፣ 4ኛ.መንገደኞች እና ማህበረሰቡ የተለመደውን ቀና ትብብር እንዲያደርግልን ሲል አፋብኃ በላይ ዘለቀ ዕዝዳ/ቴዎድሮስ ፭ኛ ኮር መልዕክቱን አስተላልፏል። #ዐንድ_አማራ‼️ #ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️ #ምረር_አማራ💪 #ድል_ለአማራ_ፋኖ💪 #ድል_ለአማራ_ህዝብ💪 10/ዐ4/2018 ዓ.ም @NISIREamhra
Mostrar todo...
86👍 14🙏 9🎉 2
🔥ካላኮርማ ክፍለ ጦር 5ኛ ሻለቃ ቃኝ ራያ ቆቦ ሮቢት ከተማ በመግባት የደፈጣ ጥቃት ፈፅመው ድል አስመዘገቡ‼️ ምስራቅ አማራ ኮር 2 ካላኮርማ ክፍለ ጦር 5ኛ ሻለቃ ቃኞች ራያ ቆቦ ወረዳ ሮቢት ከተማ ቀን 10:00 አካባቢ በመግባት ወደ ቆቦ ከተማ መውጫ ወይለት ድልድይ ላይ ኬላ ወጥረው ከነበሩ ዙፋን ጠባቂዎች ላይ የደፈጣ ጥቃት በመፈፀም እስከ አስር የሚደርሱትን ሙትና ቁስለኛ አድርገው ድል አስመዝግበዋል:: በተጨማሪም ራያ ቆቦ አቧሬ አካባቢ ይንቀሳቀሱ የነበሩ ስድስት ዙፋን ጠባቂ ሰራዊቶች ላይ አካባቢው ላይ የነበሩ ፋኖዎች በፈፀሙባቸው የደፈጣ ጥቃት ወደማይቀረው ተሸኝተዋል:: በዚህም በሁሉም የቤተ-አማራ አካባቢዎች የተጠናከረ የደፈጣ ጥቃት በመፈፀም ጠላትን ረፍት የመንሳት የማዋከብና አማራጭ አጥቶ እንዲኮበልል የማድረጉ ተጋድሎ ተጠናክሮ ቀጥሏል! መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! ©የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) #ዐንድ_አማራ‼️ #ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️ #ምረር_አማራ💪 #ድል_ለአማራ_ፋኖ💪 #ድል_ለአማራ_ህዝብ💪 10/ዐ4/2018 ዓ.ም @NISIREamhra
Mostrar todo...
40👍 10
🔥#አረጋ_ከበደ_ለጥቂት_አመለጠ‼ በአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 44ኛ ክፍለ ጦር ቲሊሊ ከተማ ላይ በተፈፀመው የሞርተር ድብደባ ሎሌው አረጋ ከበደና ግብረ አበሮቹ የጀመሩትን ስብሰባ አቋርጠው ለጥቂት በመትረፍ ወደ እንጅባራ  ፈርጥጠዋል። የብልፅግናው ሎሌ በዙፋን አስጠባቂ ሰራዊቱ ታጅቦ፤ በዙ23 እና በአረመኔ ሰራዊቱ ተከቦ፤ ቲሊሊ ከተማ ላይ ህዝባዊ የዲስኩር ስብሰባ ሊያደርግ በተቀመጠበት ጥቂት ደቂቃ ልዩነት ከወደ ፋኖ በተወሰደ የሞርተር ጥቃት አዳራሹ ላይ ሁከት በተፈጠረበት ቅፅበት በየት እንደ ወጣ ሳይታወቅ ስብሰባዉን በትኖት ፈርጦጥ እንጅባራ ከተማ እንዲገባ  ተገዷል። አረመነው ቡድን ባለፉት ቀናት በፉነተሰላምና ቡሬ ላይ የተፋውን ቅርሻት ዛሬም  ቲሊሊ ለመድገም ቢያስብም አይደፈሬዎቹ 105ኛ ኮር 44ኛ ክፍለ ጦር ነበልባሎች አስተንፍሰውታል። አረጋ ከበደና ግብረ አበሮቹ የጀመሩትን ስብሰባ በትነው ከቲሊሊ አዳራሽ በመውጣት በፓትሮል ተሳፋረው ፈጣም ወንዝ እንደተሻገሩ በተፈፀመው ተከታታይ ጥቃት አስፓልት ጫፍ በወደቀው የሞርታር ቅንቡላ ለትቂት ማምለጥ ችለዋል። በአንድ አፍ ፋኖን አጥፍተነዋል፣በትነነዋል፤ በሌላ አፍ ደግሞ በጫካ ያሉ ወንድሞቻችንን "ኑ" በሏቸው እያለ ሲያለዝን የከረመው አረጋና ተላላኪ ሎሌዎቹ፤ ያሰማሩት ጡት ቆራጭ ቡድን ጫካ ውስጥ የቀበሮ ጉድጓድ ቆፍሮ እንዳይወጣ ሁኖ ባለበት በዚህ ሰሃት 44ኛ ክፍለ ጦር ቲሊሊ ከተማን ከቦ ሲያስጨንቀው፣ በሞርታር ሲደበድበው፣ ፋኖ ግዙፍ ሀይል መሆኑን ተረድቶ፤ተጨንቆ ተጠቦ በዙ_23፣ በብረት ለበስ ፔምፔ ታጅቦ ለማድረግ ያሰበውን  ስብሰባ ማካሄድ ሳይችል ለጥቂት ህይወቱን አትርፎ ፈርጥጧል። የተሰበሰበው ካድሬም ከገቡበት አዳራሽ እኔ ልውጣ እኔ፤ ነፍስ ውጭ ነፍስ ግቢ ሩጫ በማድረግ ወደ የመጡበት ያሰቡትን ሳያሳኩ በጭንቀት ተውጠው አምልጠዋል። የነበረውን ሁነትም በግድ በጉልበት የተሰበሰበው ህዝብ በትዝብት ሲከታተል ቆይቶ መሳቂ መሳለቂያ አድርጓቸዋል። ዛሬ ታህሳስ 10/2018ዓ.ም እውነትም፤ ሀሞት ጀግንነትም ፣ሀይልም መሳሪያም፣ ትክክለኛ መንግስትዊ ቁመና የት ላይ እንዳለ ህዝቡ ያየበት፣ የታዘበበት ክስተት ሁኖ በድል ተመዝግቧል። አሁንም እንላለን፦#ይዘገያል_እንጅ_አህያ #የጅብ_ናት💪 ©✍️የ44ኛ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት ፋኖ አለበል አወቀ #ዐንድ_አማራ‼️ #ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️ #ምረር_አማራ💪 #ድል_ለአማራ_ፋኖ💪 #ድል_ለአማራ_ህዝብ💪 10/ዐ4/2018 ዓ.ም @NISIREamhra
Mostrar todo...
107👍 34😍 1