ru
Feedback
አዲስ ነገር መረጃ

አዲስ ነገር መረጃ

Открыть в Telegram

#አዲስ_ነገር_መረጃ #መረጃዎች_በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ Addis Ababa , Ethiopia Buy Ads : https://telega.io/?r=UbutLo2z #ለአስተያየት እና ለማስታወቂያ ስራዎች 👇👇 @Addisnegermereja_bot

Больше
2025 год в цифрахsnowflakes fon
card fon
103 431
Подписчики
-5124 часа
-3077 дней
+12730 день
Архив постов
የደስታ መግለጫ‼️ የ #እስራኤል መንግሥት #ሶማሊላንድን እንደ አገር እውቅና መስጠቱን ይፋ ማድረጉን ተከትሎ፣ በሶማሊላንድ ዋና ከተማ #ሀርጌሳ የታየ ሕዝባዊ የደስታ መግለጫ ትዕይንት። በአገሪቱ ዋና ዋና መንገዶች እና አደባባዮች ላይ የተሰበሰበው ሕዝብ የሶማሊላንድን አረንጓዴ፣ ነጭ እና ቀይ ባለሦስት ቀለም ሰንደቅ ዓላማ ሲያውለበልብ አምሽቷል፤ አንዳንዶችም ባንዲራውን በትከሻቸው ላይ ደርበውት ተስተውለዋል። @Addis_Reporter @Addis_Reporter
Показать все...
2.79 MB
4.89 KB
👍 27 9🤪 4
ወንዶች ከፍቅረኛቸው የሚለያዩባቸው 3 ምክንያቶች ​አክብሮትን ማጉደል  ብዙ ጊዜ ስሜታዊ መራራቅን ያስከትላል። ​የሚገርም ቢመስልም፣ አንድ ወንድ ሙሉ ፍቅርና አድናቆት እያሳየ ቆይቶ፣ በአንድ ቀን ግንኙነቱን ለማቆም መወሰኑ ሊያጋጥም የሚችል ጉዳይ ነው። ​እንዲህ ያሉ ውሳኔዎች አብዛኛውን ጊዜ በድንገተኛ ስሜት የሚወሰኑ አይደሉም፤ አንድ ወንድ ግንኙነቱን ለማቆም ከመወሰኑ በፊት፣ ብዙ ጊዜ ሌሎችን ሳያማክር የፍቅር ግንኙነቱን እያንዳንዱን ገጽታ በጥልቀት ይመረምራል። ​ግንኙነቱ አንድ ወንድ የቀድሞው ዓይነት መተሳሰር ወይም ደህንነት የማይሰማው ደረጃ ላይ ሲደርስ፣ የመለያየት ውሳኔው ለፍቅር አጋሩ  ያልተጠበቀ ሊሆን ይችላል። ​ለእንዲህ ዓይነቱ ሁኔታ የሚዳርጉ ምክንያቶችን መረዳት ችግሮችን ለመከላከልና በግንኙነት ውስጥ ያለውን የሃሳብ ልውውጥ ለማሻሻል ይረዳል። ​ወንዶች ግንኙነትን የሚያቋርጡባቸው ሦስት የተለመዱ ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው። ​1. የአካል ንክኪ መከልከል እና የቸልተኝነት ስሜት ያርቁታል ​የአካል መቀራረብ (Intimacy) በግንኙነት ውስጥ ለስሜታዊ ትስስር ቁልፍ አካል ነው። አንዲት ሴት የአካል ንክኪንና መቀራረብን ሁልጊዜ የምትሸሽ ከሆነ ወይም ለዚህ ማነስ ሰበቦችን የምታደርድር ከሆነ፣ ወንዱ የተገለለ የመሆን ስሜት ሊሰማው ይችላል። ይህም የበታችነት ስሜት እንዲፈጠርና በግንኙነቱ ውስጥ ስላለው ቅድሚያ የሚሰጣቸው ነገሮች ጥያቄ እንዲያነሳ ያደርገዋል። ​ፍቅር እንደሌለው የሚሰማው ወንድ ራሱን በአካባቢው ካሉ ሌሎች ሰዎች ጋር ማወዳደር ሊጀምርና በግንኙነቱ ውስጥ ስላለው ቦታ የተሳሳቱ ግምቶችን ሊያዳብር ይችላል። ይህ ማለት ግን የአካል መቀራረብ በግዴታ መሆን አለበት ማለት አይደለም፤ ነገር ግን ሚዛናዊነት እና ለቅርበት የሚታይ የጋራ ፍላጎት ለግንኙነቱ ዘላቂነት ወሳኝ ናቸው። ​2. ቁጥጥር ያፍናቸዋል፣ ያርቃቸዋልም፤ ካንቺ ጋር መወዳደር አይፈልጉም ​ወንዶች የማያቋርጥ የፉክክር ወይም የቁጥጥር ትግል ካለበት ግንኙነት ይልቅ አጋሮች በጋራ የሚሰሩበትን ግንኙነት ይመርጣሉ። አንድ ወንድ ሁልጊዜ ከፍቅረኛው ጋር "መወዳደር" እንዳለበት ወይም የእሷን ፍላጎቶች ለማርካት መሯሯጥ እንዳለበት ከተሰማው፣ ይህ ብስጭትና የድካም ስሜት ይፈጥርበታል። ​በማያቋርጥ ቁጥጥርና ጫና የሚመሩ ግንኙነቶች ወንዱ ራሱን እንዲያገል ያደርጉታል። ትክክለኛው ሚዛን የሚገኘው እርስ በርስ በመደጋገፍና በመረዳዳት ውስጥ ነው - አጋሮች እርስ በርስ መገማገም ወይም መፎካከር ሳይሆን መበረታታትና መነሳሳትን ሊሰጣጡ ይገባል። ​3. ሁልጊዜ የምትነቅፊው ከሆነ ​ለወንዶች ክብር እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው። ባልደረባቸው ለውሳኔዎቻቸው፣ ለአመለካከታቸው ወይም ለሚያደርጉት ጥረት እውቅና እንደማትሰጥ ሲሰማቸው፣ ዋጋ እንደሌላቸው ይሰማቸዋል። ​ከመጠን ያለፈ ትችት፣ የማያቋርጥ ጥያቄዎች እና "እንዲሻሻል" የሚደረግበት ጫና ወንዱ እንዲዋረድ ወይም በግንኙነቱ ውስጥ የታሰረ እንዲመስለው ሊያደርግ ይችላል። ​የክብር መጓደል ብዙ ጊዜ ስሜታዊ መራራቅን ያስከትላል። ​ወንዶች ፍቅረኛቸው  ደጋፊ እንድትሆናቸው ብቻ ሳይሆን፣ እነሱንም እንድትደግፋቸው፣ ጥንካሬዎቻቸውን እንድታውቅላቸውና ውሳኔዎቻቸውን እንድታከብርላቸው ይፈልጋሉ። ​ክብር ባለበት ቦታ ወንድ ልጅ ደህንነት ይሰማዋል፣ ለግንኙነቱም መስዋዕትነት ለመክፈል ይነሳሳል፤ ክብር ከሌለ ግን በጣም ጠንካራ የሚባሉ ስሜቶች እንኳ ሊጠፉ ይችላሉ ሲል "Superwoman" ዘግቧል። @Addis_News @Addis_News
Показать все...
47👍 4🫡 4
የአፍሪካ ህብረት የሶማሊላንድን እውቅና ውድቅ አደረገ። ለሶማሊያ “የግዛት አንድነትና ሉዓላዊነት” ያለውን "ጽኑ ቁርጠኝነት"ም አረጋግጧል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ ሶማሊላንድን እንደ ገለልተኛ ሀገር እውቅና ለመስጠት የሚደረገውን ማንኛውንም እንቅስቃሴ ውድቅ ማድረጋቸውንና ህብረቱ ለሶማሊያ "አንድነት እና ሉዓላዊነት ያለውን ጽኑ ቁርጠኝነት" በድጋሚ አረጋግጠዋል። "ከሶማሊላንድ ጋር በተያያዙ የቅርብ ጊዜ ክስተቶች" ላይ በሰጡት መግለጫ፤ ዩሱፍ እንደተናገሩት የአፍሪካ ህብረት በውህደት ስምምነቱ (Constitutive Act) መርሆዎች ላይ የተመሰረተውን "ረጅም ጊዜ ያስቆጠረ እና ወጥ የሆነ አቋሙን በማያሻማ ሁኔታ በድጋሚ ያረጋግጣል" ብለዋል። ሊቀመንበሩ አክለውም የህብረቱ አቋም በተለይም የአፍሪካ አንድነት ድርጅት (የአሁኑ አፍሪካ ህብረት) እ.ኤ.አ በ1964 ባሳለፈው ውሳኔ መሠረት "ከነፃነት በኋላ የተወረሱ ድንበሮች የማይደፈሩ መሆናቸውን በማክበር" ላይ የተመሰረተ መሆኑን አሳስበዋል። የኮሚሽኑ ሊቀመንበር "ሶማሊላንድን እንደ ገለልተኛ አካል እውቅና ለመስጠት ያለመ ማንኛውንም ተነሳሽነት ወይም እርምጃ በፅኑ ውድቅ ያደርጋሉ" ያለው መግለጫው፤ "ሶማሊላንድ የሶማሊያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ አካል ሆና ትቀጥላለች" ሲል አክሏል። በተጨማሪም እንዲህ ያሉ እርምጃዎች "በአህጉሪቱ ሰላምና መረጋጋት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ የሚያሳድር አደገኛ አርአያነት የመፍጠር አደጋ አላቸው" ብለዋል። @Addisinsider_ETH @Addisinsider_ETH
Показать все...
9💯 8🤣 6🔥 2😨 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
ሰበር ዜና ግብጽ፣ ሶማልያ፣ ቱርክ እና ጅቡቲ የእስራኤልን ውሳኔ ተቃወሙ። እስራኤል ከሰአታት በፊት ለሶማሊላንድ የአገርነት እውቅናን መስጠቷን ተከትሎ አራቱ አገራት ተቃውሟቸውን አሰምተዋል። ከደቂቃዎች በፊትም የጋራ የስልክ ውይይት አድርገዋል። Sirara @Addis_News @Addis_News
Показать все...
🤣 39🔥 5 3👍 1👏 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
የውጭ ሃገር የሥራ ስምሪት ሥራ ዕድል  በሥራና ክህሎት ሚኒስትር ✅ ወደ አውሮፓ (Sweden and Norway) ገበያ ለመግባት ቀደም ብሎ በተጀመረ ጥረት የዝግጅት ምዕራፍ ተጠናቆ ወደ ተግባር ተገብቷል። በመሆኑም በስምምነቱ መሰረት የተጠየቁ የሞያ ዘርፎች የሚከተሉት ናቸው። 1. ካርዲዬሎጂስት  2. የማርኬቲንግ ባለሙያ  3.  ኬሚካል ኢንጅነር  4.  ባስ ድራይቨር  5.  አርክቴክት 6.  አካውንታን 7. አውቶሞቲቭ ቴክኒሽያን ባለሙያ 8.  የላብራቶሪ ቴክኒሺያን 9.  የአይ ቲ ባለሙያ 10. የፋርማሲ ባለሙያ 11.  የሽያጭ ባለሙያ  12. የሶፍትዌር ባለሙያ  13. ሜዲካል ዶክተር  14. የኮምፒተር ጥገና ባለሙያ 15. ነርስ 16. ግራፊክስ ዲዛይነር 17. የፀጉር ባለሙያ   18. የደንበኛ አገልግሎት ባለሞያ ⁉️ ማሳሰቢያ:- VPN ወይም Psiphon መጠቀም ይኖርባችሗል 🟥 ፈጥነው ታች ባለው ሊንክ ይመዝገቡ 👇👇👇👇👇Apply Now👇👇👇👇👇👇👇                         👇👇👇👇          https://reportervacancy.com/labor-and-skill-minister-of-ethiopia-new-jobs-opportunity/ ---------Follow Our Website---------                       👇👇👇👇👇👇          https://reportervacancy.com ----------Join Our Telegram-------                                👇👇👇👇👇      https://t.me/reporter_vacancy
Показать все...
6
Фото недоступноПоказать в Telegram
የ2 አመት ህፃን ልጁን ከደፈረ በኋላ በጨርቅ ያነቃት አባት በእስራት ተቀጣ በሐረሪ ክልል ድሬ ጠያራ ወረዳ  ውስጥ ነዋሪ የሆነ ፍሮምሳ አብዱሰመድ የተባለ የ30አመት ተከሳሽ ከለሊቱ 6 ሰአት ላይ የወንጀል ድርጊቱን የፈፀመው። ተከሳሽ  የ2አመት ህፃን ልጁን በተኛችበት  ከደፈራት በኋላ አንገቷን በማነቅ ለመግደል መሞከሩን የሐረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ዳሬክተር የሆኑት ኮማንደር አበበች ሽዋረጋ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል። ተከሳሽ ከደፈራት በኋላ  ለወላጅ አባቱ ልጄ በተኛችበት ሞታለች በማለት ይናገራል የህፃኗ አያት የሆኑት አባትም  እንዴት ጤነኛ የነበረች ልጅ ልትሞት ቻለች ብለው ሄደው ሲመለከቷት መደፈሯንና የታነቀችበት አንገቷ የተከረከረ መሆኑን ይመለከታሉ አባት ያልታመመች ልጅ እንዴት ልትሞት ትችላለች በማለት ዱላ በማንሳት አንተን ከመግደሌ በፊት ያደረከውን ንገረኝ ብለው ሲያስፈራሩት ከደፈራት በኋላ ለመግደል እንዳነቃት ለወላጅ አባቱ እንደተናገረና አባት ይዘውት ለህግ እንዳቀረቡት ተገልጿል ። በሐረሪ ክልል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ሲጣራ ቆይቶ መዝገቡን ለጠቅላይ አቃቢ ህግ በመላክና በማስከፈት ታህሳስ 17/4/ 2018 በዋለው ችሎት በ25 አመት እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን  ኮማንደር አበበች ሽዋረጋ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል። Via : dagu @Addis_Reporter @Addis_Reporter
Показать все...
💔 32 12🤔 6😢 5👍 3
Фото недоступноПоказать в Telegram
"የእስራኤልን እርምጃ መግታት አልችልም" ትራምፕ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እስራኤል ለሶማሊላንድ የሰጠችውን እውቅና ማስቆም እንደማይችሉ ተናገሩ። ትራምፕ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ "የእስራኤልን እርምጃ መግታት አልችልም" ብለዋል። ፕሬዚዳንቱ "ለመናገር ያክል አስተያየት የለኝም" ሲሉ ዝርዝር ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዋል። አሜሪካ ለሶማሊላንድ እውቅና ለመስጠት ያላትን ፍላጎት በተመለከተ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ "እኛ እያሰብንበት ነው፣ ሁሌም ትልቅ ውሳኔዎችን ነው የማሳልፈው፣ ደግሞም ትክክል ይሆናሉ" በማለት ተናግረዋል። "የሶማሊላንድ ጉዳይ እንደምታውቁት ውስብስብ ነው" ሲሉ ተደምጠዋል።   #newsmax @Addis_News @Addis_News
Показать все...
👍 23🤪 5 3
01:08
Видео недоступноПоказать в Telegram
👉 ከ8 በላይ ሳይቶችን ገንብቶ ያስረከበው ቴምር ፕሮፐርቲ አሁንም በድጋሜ አዳዲስ ሳይቶችን ለሽያጭ አቅርቧል ። 📍 ሳር ቤት #በ35%ቅናሽ! (በ100% ክፍያ) 👉 ባለ 2 መኝታ = 81ካሬ = 5.7ሚ 👉 ባለ 2 መኝታ = 106ካሬ = 7.9ሚ 👉 ባለ 3 መኝታ = 139ካሬ = 10.3ሚ 👉 ባለ 3 መኝታ = 153ካሬ = 11.4ሚ #በ20% ቅድመ ክፍያ (በግንባታ ሂደት ለሚከፍሉ) 👉 81ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 9.3ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (1.8ሚሊዮን) 👉 106ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 12.1ሚ                  ቅድመ ክፍያ = 20% (2.4ሚሊዮን) 👉 139ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 15.9ሚ                  ቅድመ ክፍያ = 20% (3.1ሚሊዮን) 📍 አዋሬ #በ35%ቅናሽ! (በ100% ክፍያ) 👉 ባለ 1 መኝታ = 78ካሬ = 5.5ሚሊዮን 👉 ባለ 3 መኝታ = 117ካሬ = 8.3ሚሊዮን 👉 ባለ 3 መኝታ = 137ካሬ = 9.7ሚሊዮን 👉 ባለ 3 መኝታ = 145ካሬ = 10.3ሚሊዮን #በ20% ቅድመ ክፍያ (በግንባታ ሂደት ለሚከፍሉ) 👉 78ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 8.5ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (1.7ሚሊዮን) 👉 135ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 14.8ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (2.9ሚሊዮን) 👉 157ካሬ = ሙሉ ክፍያ = 17.2ሚሊዮን                  ቅድመ ክፍያ = 20% (3.4ሚሊዮን) ⩩ ቀሪውን 80%፤ በግንባታ ሂደት፤ ያለምንም ወለድና የግንባታ እቃዎች ጭማሪ፤ በኢትዮጵያ ብር ከፍለው የሚጨርሱት። ⩩ 30% እና ከዚያ በላይ ለሚከፍሉ፤ ከከፈሉት ላይ ከ15 -25% ቅናሽ አዘጋጅተናል። ለበለጠ መረጃ ;- 0940464607 0994003949
Показать все...
25.16 MB
4
Фото недоступноПоказать в Telegram
ምድር በጎርፍ ትጠፋለች በማለት በኖህ መርከብ በተመሰለችው መርከብ በሺዎች ያሳበሰበው የጋናው ነቢይ የጥፋቱ ቀን ተራዝሟል አለ። ‎ ‎በጋና ኩማሲ ወደ አራት ሺ ሰው ገና ተሰርታ ባላለቀችው መርከብ ከምድር ጥፋት ለመዳን የመጣ ሲሆን የጋናው ነቢይ እቦህ ኖህ ሁሉም ሰው ወደየሀገሩና ወደየመንደሩ እንዲመለስ ነግሯል። ‎ ‎"ዛሬ ዓለም አያበቃላትም" ብሏል። ‎ ‎ለ21 ቀናት ከጸለየና ከጦመ በኋላ፣ አምላክ ለሕዝቦቹ ጊዜ እንዲሰጣቸው እንደተማጸነና አምላክም ጸሎቱን ሰምቶ የጥፋቱን ቀን እንዳራዘመው ገልጿል። ‎ ‎"ይህ ሀሰተኛ ነቢይ ነው" የሚል ትችት የቀረበበት ነቢይ፥ ከ“እግዚአብሔር ሰዎች” ጋር ካደረገው ጸሎት በኋላ፣ እግዚአብሔር ሁሉንም ሰው የሚያስተናግዱ ተጨማሪ መርከቦች እንዲገነቡ ተጨማሪ ጊዜ እንደፈቀደላቸው ገልጿል። ‎ ‎@seledadotio @seledadotio
Показать все...
🤣 95 14
Фото недоступноПоказать в Telegram
የአፍሪካ ህብረት እስራኤል ለሶማሊላንድ የሰጠችውን እውቅናን ውድቅ አደረገ የአፍሪካ ህብረት ለሶማሊያ አንድነት እና ሉዓላዊነት ያለውን የማይናወጥ ቁርጠኝነት አለው ብሏል ባወጣው መግለጫ። ​የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሀሙድ አሊ ዩሱፍ በሶማሊላንድን በተሰጠ እውቅና ላይ ከባድ ስጋት አለኝ ብለዋል። የኮሚሽኑ ሊቀመንበር በአፍሪካ ህብረት መስራች ህግ መርሆዎች ላይ የተመሰረተውንና በተለይም በ1964ቱ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ውሳኔ የጸደቀውን "ከነጻነት በኋላ የተወረሱ ድንበሮች የማይደፈሩ የሚለውን የቆየና ጽኑ የአፍሪካ ህብረት አቋምን እደግፋለው ብለዋል። ​ሊቀመንበሩ ሶማሊላንድ የሶማሊያ ፌደራላዊ ሪፐብሊክ አካል ናት በማለት ሶማሊላንድን እንደ ገለልተኛ አካል እውቅና ለመስጠት የሚደረጉ ማናቸውንም ውጥኖች ወይም እርምጃዎች ውድቅ አድርገዋል።
Показать все...
16🤣 8😨 2💔 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
ሰሜን ኮሪያ እና ሩሲያ በዩክሬን ጦርነት ውስጥ ደምን፣ ሕይወትን እና ሞትን ተጋርተዋል ሲሉ ኪም ጆንግ ኡን ተናገሩ የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ለሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ባስተላለፉት የአዲስ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት፤ ሰሜን ኮሪያና ሩሲያ በዩክሬኑ ጦርነት ውስጥ "የደም፣ የሕይወት እና የሞት" ትስስር አላቸው ብለዋል። ​ በሰሜን ኮሪያ የዜና ወኪል በታተመው በዚህ መልዕክት፤ ኪም 2025 በፒዮንግያንግ እና በሞስኮ መካከል ያለው ጥምረት "በአንድ ቦይ ውስጥ በጋራ በፈሰሰ ደም፣ በሕይወት እና በሞት" የጠነከረበት "በእውነትም ትርጉም ያለው ዓመት" ነው ብለዋል። የደቡብ ኮሪያ እና የምዕራባውያን የስለላ ድርጅቶች ፒዮንግያንግ በዩክሬን ጦርነት ከሞስኮ ጎን ተሰልፈው እንዲዋጉ በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን መላኳን ቀድመው ዘግበው ነበር። ሰሜን ኮሪያ ባለፈው አመት ሚያዚያ  ወር ላይ ወታደሮቿ የሩሲያን ወታደራዊ ዘመቻ ለመደገፍ መሰማራታቸውን እና አንዳንዶቹም በውጊያው ላይ መገደላቸውን አረጋግጣለች። ​በታህሳስ ወር መጀመሪያ ላይ ፒዮንግያንግ በነሐሴ ወር ውስጥ ከዩክሬን ድንበር አቅራቢያ በሚገኘው የኩርስክ ክልል ፈንጂዎችን ለማጽዳት ወታደሮችን ልካ እንደነበር አምናለች። ወታደራዊ ክፍሉ ወደ ሀገር ሲመለስ ታህሳስ 4 ቀን ኪም ባደረጉት ንግግር፥ በ120 ቀናት ቆይታቸው ቢያንስ ዘጠኝ የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች መገደላቸውን ተናግረዋል። @Addis_News @Addis_News
Показать все...
19👏 9🤣 4
Фото недоступноПоказать в Telegram
🌟🌟ታላቅ የገና በዓል ቅናሽ በካሬ 78,000 ብር ✅እንዲሁም ሙሉ ክፍያ ለሚከፊል በካሬ 54,800 🔷 በ10 % ቅድመ ክፍያ 🔷 50 %  የባንክ ብድር  የተመቻቸለት 📍Location እንግሊዝ ኢንባሲ አጠገብ  ውብ እይታ (Top View) ያላቸው ቤቶች በሽያጭ ላይ እንገኛለን 👉ከባለ 2 መኝታ- ባለ4 መኝታ ✅ ህንፃው ላይ ያሉ ተጨማሪ አገልግሎትች   ‎👉5 ሰፋፊ ሊፍት /elevator   ‎👉የቆሻሻ መጣያ/garbage chute   👉አውቶማቲክ ጀኔረተር/ automatic       generator    ‎👉ሰገነት/terrace    ‎👉የመኪና ማቆምያ/car parking     👉 ጂም , እስፖ    👉 የዋና ገንዳ    👉 የልጆች መጫወታ ✨ባለ 2 መኝታ ‎           138     ካሬ ‎           157.3   ካሬ ‎           163.6   ካሬ ‎ ✨ባለ 3 መኝታ            152.4  ካሬ            158.1  ካሬ ‎           187.6  ካሬ            211.5  ካሬ ‎ ✨ባለ 4 መኝታ            240.7 ካሬ ‎           258.4 ካሬ ‎        📞 ለበለጠ መረጃ ይደውሉ ‎                 0973559591                  0919489575                  Telegram -@Homef17                            https://t.me/lijhop7
Показать все...
7
Фото недоступноПоказать в Telegram
በጃፓን አንድ የ38 ዓመት ሰው በቢላ  በፈጸመው ጥቃት 15 ሰዎች ቆሰሉ ጥቃቱ የደረሰው​ በሚሺማ ከተማ  በጎማ ፋብሪካ በሚሰሩ ሰራተኞች ላይ ነው። እንደ ማይኒቺ  ጋዜጣ ዘገባ ከሆነ  ትናንት አርብ በደረሰው ጥቃት ስምንት ሰዎች በቢላዋ ሲወጉ፣ ሰባት ሌሎች ደግሞ ሰውዬው  በረጨባቸው ፈሳሽ ተጎድተዋል። ​ጥቃቱን ፈጽሟል ተብሎ የተጠረጠረው የ38 ዓመቱ ማሳኪ ኦ. በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን፣ በግድያ ሙከራ ወንጀል ምርመራ እየተካሄደበት ይገኛል። እንደ መገናኛ ብዙኃን ዘገባዎች ከሆነ፣ ግለሰቡ ጥቃቱን ሲፈጽም  ጭንብል አድርጎ የነበረ ሲሆን፣ እንደ ክሎሪን/በረኪና ያለ ፈሳሽም ሰራተኞቹ ላይ ረጭቷል። ​በጃፓን እንዲህ ያሉ ከባድ የኃይል ድርጊቶች እምብዛም የተለመዱ አይደሉም። በምሥራቅ እስያዊቷ ሀገር ጃፓን የጦር መሣሪያ ቁጥጥር በጣም ጥብቅ ነው። ሆኖም ግን፣ በቅርብ ዓመታት ውስጥ በሕዝቡ ዘንድ መረበሽን የፈጠሩ በርካታ የቢላዋ ጥቃቶች ተከስተዋል። @Addis_News @Addis_News
Показать все...
11🙏 3🥰 1
የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል የስሙ ትርጓሜ “እግዚእ ወገብር፤ አምላክ ሰው ሆነ፣ ሰው አምላክ ሆነ” ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ገብርኤል የጌታችን መድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መምጣትና ሰው መሆን ለመናገር ተልኮ የምሥራች ዜናን ያበሠረ፤ በዲያቢሎስ የተንኮል ወጥመድ ገብተው ለተሰናከሉት ፈጥኖ ለመርዳት የሚደርስ፣ በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ ለሚኖሩት ሁሉ የብርሃን ፋና ያበራ፣ ሰብአ ሰገልን የመራ መልአክ ነው፡፡ ከቀድሞ ጀምሮ ቅዱሳን ነቢያት ከእግዚአብሔር ተልከው መንፈስ ቅዱስ እንዳናገራቸው ዓለምን ስለማዳን ከጽዮን የሚወጣ ከያዕቆብ በደልን የሚያርቅ ጌታ “ይወርዳል ይወለዳል” በማለት በየወገናቸውና በየዘመናቸው የተናገሩትን የነቢያትን ትንቢት መፈጸሙን የሚያበስረውን የምሥራችን ቃል የተናገረ ነው፡፡ የጨለማ አበጋዝ በሆነ በሰይጣን ተንኮል በሰው ልቦና ውስጥ አድሮ የነበረውን ከእፉኝት መርዝ የከፋ የኀዘን ስሜት ያጠፋ የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ ቅዱስ ገብርኤል ከሌሎች መላእክት ተለይቶ ዘወትር በምንጸልያቸው ጸሎቶች ስሙ የሚጠራ መልአክ ነው፡፡ ይኸውም በዘወትር ጸሎቶች በአቡነ ዘበሰማያት፣ በሰላመ ቅዱስ ገብርኤል፣ በውዳሴ ማርያም፣ በይዌድስዋ መላእክትና በመሳሰሉት ጸሎቶች ዘወትር ስሙ የሚጠራ ነው፡፡ ካህናት አባቶች ቅዱስ ገብርኤል ስእለት ሰሚና ፈጥኖ ደራሽ መልአክ እንደሆነ ይነግሩናል፡፡ ይኽም በክርስቲያኖችም ዘንድ እጅግ ተወዳጅ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ ፈጥኖ ደራሹ መልአክ፣ ስእለት ሰሚው መልአክ ይሉታል፡፡ የአምላክ እናት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ከሌሎች መላእክት ሁሉ በይበልጥ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልን እንደምትወደው በድርሳነ ገብርኤል “ወንድሞቻችን ሆይ፣ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከመላእክት ሁሉ ይልቅ ቅዱስ ገብርኤልን በይበልጥ እንደምትወደው ተመልከቱ፤ የልጅዋን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ከእርሷ መወለድ ያበሠራት እርሱ ነውና” የሚል ተጽፎ ይገኛል፡፡ ከሰባቱ ሊቃነ መላእክትም አንዱ በእግዚአብሔር ፊት የሚቆመው ታማኝ መልአክ ይህ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ በተረዳኢነቱና በአማላጅነቱ፣ ያዘኑትን ለማጽናናት የምሥራች ለመንገር ከእግዚአብሔር ወደ ምእመናን ይላካል፡፡ ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚነግረን አባቶቻችን እንዳስተማሩን በዘመኑ ጣኦት የሚያመልከው ንጉስ ናቡከደነፆር በባቢሎን ምርኮ የወሰዳቸውን የእግዚአብሔር ሰዎች አናንያ፤ አዛርያ፤ ሚሣኤል እጅግ ይወዳቸው ነበር፡፡ ከባቢሎናውያን ይልቅ ጠቢባን የነበሩት ሶስቱ ሕጻናት በትንቢተ ዳንኤል ምዕራፍ ሦስት ሰፍሮ የምናገኘው ታሪካቸው እንደሚነግረን ንጉሱ የጣኦት ምስል አሰራ በገሊላ አውራጃ ያለውን ሕዝብ ጠርቶም ለጣኦቴ ያልሰገደ ወደ እሳት ውስጥ ይጣላል ብሎ አወጀ። የንጉስ ትህዛዝ ነውና ሕዝቡ ሁሉ ለጣኦቱ ሲንበረከክ እነርሱ ግን ቆመው ያዩ ነበር። ናቡከደነፆር እርሱ ላስቆመው ጣኦት አለመስገዳቸውን ሲሰማ ተናደደ፣ ተበሳጨም እሳቱን 7 እጥፍ እንዲነድ አስደረገ ሦስቱንም አስሮ እሣቱን እያሳየ "ከመቃጠል ወይስ ለእኔ ጣኦት መስገድ የቱ ይሻላል?" ቢላቸውም የእግዚአብሔር የሆነ ሰው ምንም ነገር አያስፈራውምና "የምናመልከው አምላካችን ከሚነደው ከእሳቱ እቶኑ ሊያድነን ይችላል፣ ባያድነንም ግን አንተ ላቆምከው ጣኦት አንሰግድም" አሉት፡፡ በዚህ ጊዜ ጉልበት ያላቸው ሠዎች ተፈልገው ሦስቱን ወጣቶች አስረው ወደ እሳት ቶን ውስጥ ጣሏቸው አስረው የጣሏቸውን ወታደሮች የእሳቱ ወላፈን አቃጠላቸው ሠለስቱ ደቂቅን ግን መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወርዶ እሳቱን አበረደላቸው፣ አጠፋላቸው። ከእሳቱ ላይ ሆነውም እግዚአብሔርን አመሰገኑ፡፡ ገዳማውያኑም ቅዱስ ገብርኤል ሆይ ሲሉት ይደርስላቸዋ፤ በረከታቸው አብሮን እንዲሆን ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡ ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ 1000442598391 ወይም አቢሲኒያ ባንክ 141029444 ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957
Показать все...
57👍 6
Фото недоступноПоказать в Telegram
21
በጫማው ውስጥ ጫት ደብቆ ወደ ማረሚያ ቤት ለማስገባት የሞከረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ በሀላባ ዞን ማረሚያ ተቋም ውስጥ የሚገኝን ታራሚ ለመጠየቅ የሄደ ግለሰብ፣ ጫት በጫማው ውስጥ ደብቆ ለማስገባት ሲሞክር እጅ ከፍንጅ መያዙ ተነገረ። አቶ መሳይ ፊቻጎ የተባለው ግለሰብ፣ ለታራሚ በርገና ሀንድኖ እንዲደርስ ግምቱ 1,000 (አንድ ሺህ) ብር የሚሆን ጫት በጫማው ውስጥ በመደበቅ የፍተሻ ጣቢያውን ለማለፍ ሞክሮ ነበር። ይሁን እንጂ በተቋሙ የፍተሻ ኦፊሰር በዋና ሳጅን አሸናፊ አበጋዝ በተደረገ ጥብቅ ፍተሻ ድርጊቱ ሳይሳካ ቀርቷል። የተቋሙ ኃላፊ ኢንስፔክተር ሁሴን ጉንታ እንደገለጹት፣ ግለሰቡ ከጠያቂዎች ጋር በመቀላቀል ደብቆ ለማስገባት የሞከረው ጫት ወደ ታራሚዎች ሳይገባ መከላከል ተችሏል። ኃላፊው አክለውም፦ "ህብረተሰቡ የማረም እና የማነጽ ስራን ከሚያሰናክሉ መሰል ተግባራት ሊቆጠብ ይገባል። ታራሚዎች ከሱስ ነፃ ሆነው ውጤታማ ዜጋ እንዲሆኑ የሁሉንም ትብብር እንሻለን" ብለዋል። ተቋሙ መሰል ህገ-ወጥ ድርጊቶችን ለመከላከል ቁጥጥሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቋል። ምንጭ :- ሀላባ ዞን ቁሊቶ ከተማ ማረሚያ ተቋም @seledadotio @seledadotio
Показать все...
🤣 21 20🥱 2
Фото недоступноПоказать в Telegram
25👍 11🤣 10😢 2👏 1🤔 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
24🤪 3😢 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
👏 25 13🤪 5🔥 2
Фото недоступноПоказать в Telegram